ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በከበባ ውስጥ ያለችው የትግራይ ሁኔታ
የኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ህይወትን የቀጠፈ ሲሆን ሌሎች ሚሊዮኖች ደግሞ ለችግርና ለረሃብ ተጋልጠዋል።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ሲሆን የአቅርቦት እጥረት የጤና ስርዓቱን ለውድቀት ዳርገውታል።
የትግራይ ክልል ለሁለት ዓመት ያህል ከአለም ተቆራርጣ የምትገኝ ሲሆን በከበባም ውስጥ ነው ያለችው።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እገዳ ጥለዋል የሚለውን የማይቀበሉት ሲሆን ህወሃትንም ሲከሱ ይሰማሉ።
ይህየምርመራ ዘገባ እንደሚያሳየው በትግራይ ያለው ከበባ በሰው ልጆች ላይ እያስከተለው ያለው ጉዳት እጅግ አስከፊ መሆኑን ነው።
ቢቢሲ አፍሪካ አይ በአፍሪካ ውስጥ ደም አፋሳሽ ከሆኑት ጦርነቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ጦርነት ምን ያህል ህይወት እየተከፈለበት እንደሆነ መርምሯል።