ሲቲን ከኒውካስል፤ ቶተንሃምን ከዩናይትድ ያፋጠጠው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባለፈው ሳምንት ሲጀመር ኒውካስል አስደናቂ መሆኑን አንስቷል። ይህንን አጀማመር ኢትሃድ ስታዲም ላይ ይደግሙታል?

“ኒውካስል ማንቸስተር ሲቲን ሊያሽነፍ ይችላል” ይላል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን።

“ሲቲ ደግሞ ይህን መሰሉ ፈተና ሲገጥመው ድንቅ አቋሙን ማሳየት ይችልበታል” ብሏል።

ሱቶን ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ ጨምሮ የሊጉን የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

አርብ

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ሼፊልድ ዩናይትድ

ኖቲንግሃም ፎረስት ባለፈው የውድድር ዓመት በሜዳው ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

በተመሳሳይ ዘንድሮም ይህንኑ መድገም እና ጨዋታው ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ሼፊልዶች ካለፈው ሽንፈት በማንሰራራት ለማሸነፍ መጫወት ይኖርባቸዋል።

የስቲቭ ኩፐር ቡድን ከአርሰናል ጋር በነበረው ጨዋታ በርካታ የማጥቃት አማራጮት እንዳሉት ማሳየቱ ይጠቅመዋል።

ግምት፡ 2 – 0

ቅዳሜ

ፉልሃም ከ ብሬንትፎርድ

ፉልሃም ባለፈው ሳምንት በነበረው ጨዋታ ተጋጣሚው ኤቨርተን በርካታ ዕድሎችን ቢፈጥርም ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዞ መመለስ የቻለው ግን ፉልሃም ነው።

ብሬንትፎርድ የተደራጀ ቡድን ሲሆን ባለፈው ሳምንት ከቶተንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ 30 በመቶ የኳስ ቁጥጥር ቢኖረውም በመልሶ ማጥቃት በፈጠረው ዕድል አቻ መለያቱ ተገቢ ነው።

ይህ ጨዋታም በተመሳሳይ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 – 1

ሊቨርፑል ከ ቦርንመዝ

ቦርንመዝ ባለፈው ሳምንት ከዌስት ሃም ጋር ባደረገው ጨዋታ አዲሱ አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ከሚጠበቅባቸው በታች ሆነው ነው የታዩት።

በዚህ ጨዋታ የሊቨርፑል አጥቂዎች ልዩነት ፈጣሪ እንደሚሆኑ እገምታለሁ።

አዲሱ ፈራሚ ዋታሩ ኤንዶም በዚህ ጨዋታ የሚያሰልፉት ይመስላል። በቦታው ላይ ችግር እንዳለባቸው ይታወቃል።

ቦርንመዞችም በአጥቂው ዶምኒክ ሶላንኬ ጎል ያስቆጥራሉ።

ግምት፡ 3 – 1

ሉተን ከ በርንሌይ

ይህ ጨዋታ በኬንልወርዝ ሮድ በሚካሄደው የማሻሻያ ግንባታ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላለፏል።

ዎልቭስ ከ ብራይተን

ዎልቭሶች ሰኞ ዕለት ኦልድትራፎርድ ላይ ድንቅ ሆነው ቢያመሹም ባዶ እጃቸውን ነው የተመለሱት።

አንድሬ ኦናና ለፈጸመው ጥፋት ፍጹም ቅጣት ምት ማግኘት የሚገባቸው የነበረ ሲሆን በርካታ ዕድሎችንም አምክነዋል።

ብራይተኖች ባለፈው ሳምንት ሉተንን ቢያሸንፉም በዚህ ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

በዚህ ጨዋታ ዕድሎቹን የሚጠቀመው ቡድን የሚያሽንፍ ሲሆን ግምቴን ግን ለብራይተን እሰጣለሁ።

ግምት፡ 1 – 2

ቶተንሃም ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ባለፈው ዓመት ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ጥሩ ባይሆንም የአሁኑ የቶተንሃም አጨዋወት ለቀያዮቹ ሴጣኖች የሚመች ነው።

ቶተንሃም በመሠራት ላይ ያለ ቡድን ሲሆን አጥቂው መስመር ግን ውጤታማ አይደለም።

ከዎልቭስ ጋር ጥሩ ሳይሆን ሦስት ነጥብ እንዳገኘው ሁሉ በዚህ ጨዋታም የቴን ሃግ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።

ቶተንሃም በዚህ ጨዋታ እንደሚሸነፍ ብገምትም ቡድኑ ጊዜ ከተሰጠው ውጤታማ ይሆናል።

ግምት፡ 1 – 2

ማንቸስተር ሲቲ ከ ኒውካስል

ሲቲዎች ገና በሙሉ አቋማቸው ላይ ባይደርሱም በርንሌይን በማሸነፍ ሦስት ነጥብ አሳክተዋል።

የኤዲ ሃው ቡድን አዲስ ፈተና የሚደቅን ቡድን ሲሆን ድንቅ ጨዋታ ይሆናል።

ሲቲ በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ሱፐር ካፕ ቢጫወቱም በሜዳቸው በመሆኑ በበላይነት ያጠናቅቃሉ።

ግምት፡ 3 – 1

እሑድ

አስቶን ቪላ ከ ኤቨርተን

አስቶን ቪላ በኡናይ ኤምሬ አሰልጣኝነት ስር ብዙ መሻሻል አሳይተው ብዙ ቢጠበቅባቸውም በኒውካስል የደረሰባቸው ሽንፈት እና ጉዳት ቅስም ሰባሪ ነው።

ኤቨርተኖች ደግሞ ትልቅ ችግር አለባቸው። ከፉልሃም ጋር ጥሩ ቢጫወቱም ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ባለመጠቀማቸው ተሸንፈዋል።

የቡድኑ ውጤታማነት የሚወሰነው በዶምኒክ ካልቨርት-ሌዊን የአጥቂ መስመሩን በመምራቱ ላይ ነው።

ለአስቶን ቪላ ግምቴን የሚሰጥ ሲሆን ኤቨርተን ጎሎችን አለማስቆጠር ደግሞ ይረዳቸዋል።

ግምት፡ 2 – 0

ዌስት ሃም ከ ቼልሲ

ዌስት ሃም በዝውውር መስኮቱ ውጤታማ ካለመሆኑም በላይ ሉካስ ፓኩዌታንም ሊያጣ ይችላል።

ቼልሲ ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል ጋር በሁለተኛው አጋማሽ ጠንካራ ሲሆን የሞሰስ ካሲዬዶ መጨመር ቡድኑን የሚያጠናክር ነው።

ጎሎችን ማስቆጠር የሰማያዊዎቹ ችግር ነው።

ዌስት ሃም በመከላከል መልሶ ለማጥቃት ቢገባም ቼልሲ የተሻለ ጥራት አለው።

ግምት፡ 1 – 2

ሰኞ

ክሪስታል ፓላስ ከ አርሰናል

ከቀደሙት ዓመታት አንጻር ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ላይ አርሰናል ወደ ፓላስ በማቅናት ማሸነፋቸው የቡድኑን መሻሻል ያሳየ ነው።

ባለፈው ሳምንት ከሼፊልድ ዩናይትድ ጋር ፓላስ ጥሩ ቡድን መሆኑን አሳይቷል።

ዩሪየን ቲምበር በጉዳት መለየቱ መጥፎ ዜና ቢሆንም መድፈኞቹ በአጥቂዎቻቸው እገዛ ሦስቱን ነጥብ ያሳካሉ።

ግምት፡ 0 – 2