ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ቨርጅን ጋላክቲክ ለጉብኝት ወደ ጠፈር የሚደረግ በረራ ሊጀምር ነው
በጠፈር ቱሪዝም ላይ የተሰማራው የእውቁ ባለሃበት ሰር ሪቻርድ ብራንሰን ቨርጅን ጋላክቲክ ኩባንያ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለጉብኝት የሚደረገውን የመጀመሪያውን የጠፈር በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ኩባንያው ጋላክቲክ 01 ሲል የጠራውን በረራ ከሰኔ 20 እስከ 23 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ለማድረግ መወጡን ገልጿል።
ይህ ውጥን ይፋ ሲያደርግ የቨርጅን ጋላክቲክ የገበያ ድርሻ ድርሻው 40 በመቶ ተመንድጓል።
ባለፈው ወር የዩኬው ባለሀብት ሪቻርድ ብራንሰን ቨርጅን ኦረቢት የተባለ ሌላ ኩባንያ ትልዕኮዎቹ ከተጨናገፉ ከወራት በኃላ ተዘግቷል።
ቨርጅን ጋላክቲክ ኩባንያ በመጀመሪያ በረራ ሳይንሳዊ ጥናት የማድረግ ተልዕኮ አለው። በዚህ በረራ የሚካተቱት የቡድን አባላት ከጣልያን አየር ኃይልና ከጣልያን ብሄራዊ ጥናት ማዕከል የሚመጡ ተጓዦች ሲሆኑ ‘ማይክሮግራቪቲን’ ያጠናሉ ተብሏል።
ኩባንያው ከዚህ የመጀመሪያ ጉዞ በኃላ ቀጣዩ በረራ ሃምሌ ላይ የሚደረግ ሲሆን ከዚያም በኃላ በየወሩ በረራ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ይህ የጠፈር በረራ 19 ዓመታትን ላስቆጠረውና በቴክኒክ ችግሮች እንዲሁም ተከታታይ አደጋዎች ላጋጠሙት ቨርጅን ጋላክቲክ ጉልህ ለውጥ ይሆናል።
ባለፈው ወር የኩባንያው ‘ዩኒቲ’ ተብሎ የተጠራ የሮኬት አውሮፕላን ከሁለት ዓመታት በኃላ ወደ ስራ ተመልሷል።
ሁለት ፓይለቶችን እና አራት ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረው ሮኬት ከአሜሪካዋ ኒው ሜክሲኮ በርሃ ከተወንጨፎ ተመልሷል።
ይህ በረራ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የንግድ አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት የተደረገ ሙከራ ነው።
ቨርጅን ጋላክቲክ እስካሁን ከምድር 80 ኪሎ ሜትር ከፍ ብለው መብረር ለሚፈልጉ ከ800 በላይ ሰዎች ትኬት ሸጧል።
በዚህ በረራ የሚካተቱ ተጓዦች ምድርን ከላይ ሆነው የሚመለከቱ ሲሀን ለጥቂት ደቂቃዎች የመሬት ስበት በሌለበት ቦታ ደርሰው ስሜቱን ይጋራሉ። ይህ ጉዞ በአንድ ሰው 450 ሺህ የአሜረካ ዶላር ይከፈልበታል።
ቨርጅን ጋላክቲክ የጠረፍ ቱሪዝም ላይ ቢያተኩርም የሰር ሪቻርድ ኩባንያ በቨርጅን ኦርቢት አማካኝነት የሳተላይት ሮኬት የማስወንጨፍ እቅድም ነበረው።
ሆኖም ቨርጅን ኦርቢት ባለፈው ወር በጋጠመው የተልዕኮ መጨናገፍ ምክንያት ተዘግቷል። ይህም በዩኬ የጠፈር ዳሰሳ ትልቅ ለውጥ ሆኗል።
በዚህ ዓመት መግቢያ ላይ ኩባንያው ሳተላይት እንደሚያመጥቅ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆነም የገንዘብ አቅሙን ለማሰደግ ስራዎቹችን አቁሞ ቆይቷል።
ሰር ሪቻርድ ባለው ወር ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ መጠይቅ በግሉ የ1.9 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደገጠመው ገልጿል። ባለሀብቱ የዚህ ኪሳራ መነሻ በኮቪድ 19 የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት የአየር መንገድና የመዝናኛ ንግዶቹ ያጋጠማቸው ኪሳራ እንደሆነ አመላክቷል።
“ሁሉነም ነገር እናጣለን ብዬ ያሰብኩበትም ጊዜ ነበር” ሲልም አክሏል።
ሆኖም ሰውዬው ቢሊዮነር ሆኖ መቆየት ችሏል። ባለፈው ዕሁድ የወጣው የታይምስ ባለጸጎች ዝርዝር ሰር ሪቻርድ ብራንሰን 2.9 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት አለው።