በጣት ቢገፉ የሚወድቁ የሚመስሉትና በመላው ዓለም የሚገኙት አስደናቂ ዓለቶች

ግዙፍ ዓለቶች ናቸው። በየትኛውም ቦታ ሊገኙ ይችላሉ። በጣት ቢገፉ የሚወድቁ ይመስላሉ።

በመላው ዓለም ድንገት የሚከሰቱት ዓለቶች አቀማመጣቸው ልዩ ነው።

በአንድ ወቅት ምን እንደሆኑ እምብዛም አይታወቅም ነበር። አሁን ግን ስለ ርዕደ መሬት ተጨባጭ መረጃ እየሰጡ ነው።

ርዕደ መሬትን መለካት ከማይቻልበት ዘመን አንስቶ ያለው ታሪክ ማሳያ ናቸው።

በኢንሜሪካል ኮሌጅ ለንደን የጂኦሎጂ ባለሙያው ዴለን ሮድ እንደሚለው፣ ስለቀደመው የርዕደ መሬት ታሪክ “ማጣቀሻ የሚሆኑት” እነዚህ ዓለቶች ናቸው።

ይህም ለወደፊቱ ዝግጅት ለማድረግ ይረዳል።

ለርዕደ መሬት ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን ለይቶ ካርታ መሥራት የሚቻለው በዚህ መንገድ ነው።

መሠረተ ልማትና ሕንጻ ከመዘርጋቱም በፊት መረጃው ይጠቅማል።

የኢንሹራንስ መረጃ የሚገኝበትም አንድ መንገድ ነው።

እነዚህ ዓለቶች ከመሬት ስበት በተቃራኒው የቆሙ ይመስላሉ።

መሀንዲሶች ኒውክሌር እንዲሁም ሬድዮአክቲቭ የሆነ ተረፈ ምርት ላይ ምርምር ለማድረግም ይጠቀሙባቸዋል።

አሁን ባሉበት ቅርጽ ከመገኘታቸው በፊት ቋሚ መሬት ላይ ነበር የሚታዩት። በዚህም ‘Precariously balanced rocks’ የሚል ስያሜ አግኝተዋል።

አንዳንዶቹ በመሬት መሸርሸር ነው የተከሰቱት።

በአሜሪካ ዩታ በሚገኘው አርኪስ ናሽናል ፓርክ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓለቶች ይገኛሉ።

አውሎ ነፋስ ወይም ጎርፍ ሲከሰት የሚወድቁ ይመስላሉ።

በሚፈረካከሱበት ጊዜ ባሕር ወይም ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኝ ዓለት ሊሆኑም ይችላሉ።

ሌሎች ተመሳሳይ ዓለቶች በጊዜ ሂደት ይፈጠራሉ።

በስኮትላንድ ኦርከንሊ ደሴት የሚገኘው ‘ኦልድ ማን ኦፍ ሆይ’ የተባለው ዓለት ዝነኛ ነው።

አንዳንዶቹ ዓለቶች ረዥምና ከባድ ናቸው። ሌሎቹ ከሰው ክንድ የማይሰፉ ናቸው።

ለዕይታ ማራኪ ናቸው። ሰዎች ፎቶ ለማንሳትም ይመርጧቸዋል።

ቀድሞ በነበረ ሥልጣኔ ወይም በአማልክት የተሠሩ ይመስላሉ።

በዮርክሽር ‘ብሪማም ሮክስ’፣ በሕንድ ‘ክሪሽናስ በተርቤል’ እና በፊንላንድ ‘ኩማኪቪ’ በሚል ስያሜ ይገኛሉ።

በአሜሪካ በኦሪጎን ተራሮችና በሜይንም አለቶቹ ይታያሉ።

በአንዳንድ አገሮች ለአምልኮ ይውላሉ።

በሚያንማር ቡዲስቶች ወርቃማ ቀለም ቀብተው አለቱን ያከብሩታል። የቡድሃ ፀጉር አለቱ እንዳይወድቅ አድርጎታል ተብሎ ይታመናል።

እነዚህ አለቶች ባሉበት መቆም የሚችሉት በሁለት ምክንያት ነው።

አንዳንዴ በበረዶ ግግር ተገፍተው ባልተለመደ ሁኔታ ቆመው ይገኛሉ። ሌላ ጊዜ ደግሞ መሠረቱ በጊዜ ሂደት ተሸርሽሮ ከላይ ዓለቱ ይገኛል።

የታሪክ መስኮት

ተራራ መውጣት የሚወዱ ዓለቶቹን አዘውትረው ፎቶ ያነሳሉ።

የርዕደ መሬት ተመራማሪዎች ቀድመው የተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦችን ያጠኑባቸዋል።

እአአ በ1990ዎቹ የቅሪተ አካል ተመራማሪዎች በካሊፎርያ እና ነቫዳ ስለነዚህ ዓለቶች ጥናት ሠርተዋል።

በውሃ አካል አቅራቢያ እንደሚገኙ ሲታወቅ፣ ቀድሞ የነበረን የመሬት የንዝረት እንቅስቃሴ ለማጥናት ምክንያት ሆኑ።

ሊወድቁ የተቃረቡ ቢመስሉም ከመሬት ሥር ስላልተሸረሸሩ ሳይወድቁ ይቆያሉ።

በዋሽንግተን የሚገኘው ‘ኦማክ ሮክ’ ወደ 90 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው።

በ1872 የፓስፊክ ሰሜን ምሥራቅ በርዕደ መሬት ተከስቶ ነበር። በወቅቱ ምን ያህል መሬት እንደተንቀሳቀሰ መለኪያ መንገድ አልነበረም። አሁን ይህ ዓለት ምን ያህል ንቅናቄ እንደተፈጠረ ለማጥናት ውሏል።

የሰው ልጅ ርዕደ መሬትን መመዝገብ ከመጀመሩ በፊት ያለውን መረጃ ማግኘት ከባድ ነው።

የጂኦሎጂ ባለሙያዎች ቅድመ ታሪክ ክንውን ለማወቅ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።

በመሬት ስንጥቅ፣ በመሬት መንሸራተት፣ በአውሎ ንፋስና ሌላም ተፈጥሯዊ ክስተት ልኬት ለመሥራት ይሞክራሉ።

ይህንን መረጃ ይዞ በቀጣይ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚከሰትበትን አካባቢ ለመለየት ጥረት ይደረጋል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ያሳለፍነው መስከረም ላይ ባወጣው ጥናት በኒው ዮርክ እና ቨርሞንት የተከሰቱ ዓለቶችን በተመለከተ አስነብቧል።

እነዚህን መነሻ በማድረግም የርዕደ መሬት ካርታ ይሠራል።

ጥንዶቹ አና ሮድ እና ዲለን ሮድ የጂኦሎጂ ባለሙያዎች ናቸው።

የርዕደ መሬት ክስተትን በተመለከተ የተሻለ መረጃ ለማግኘት አስተማማኝ ግምት መስጠት የሚቻልበትን መንገድ ለማግኘት ምርምር ያደርጋሉ።

አካባቢው በሰው አልባ አውሮፕላን በመቃኘት ባለ ሦስት አውታር ማሳያ ያዘጋጃሉ።

እነዚህ ምሥሎች የተለያዩ የርዕደ መሬት ዓይነቶችን በመሞከር ዓለቶቹ በየትኛው የርዕደ መሬት እንደተከሰቱ ይጠቁማሉ።

“በተለያዩ የመሬት ንዝረቶች አማካይነት የተከሰቱ ዓለቶችን ማጥናት እንችላለን። ዓለቶቹ የተከሰቱት በአጭር የመሬት መንቀጥቀጥ ነው ወይስ ዘለግ ባለ የሚለውን ለማወቅ እንሞክራለን” ትላለች አና።

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ዓለቶቹ ተንቀሳቅሰዋል? የሚለው ሌላ የጥናቱ አካል ነው።

ቤሪሊየም 10ን ጨምሮ የያዙት ንጥረ ነገርም ይጠናል።

ዓለቱ ለከባቢ አየር ሲጋለጥ ምን እንደተከሰተ ማወቂያ መንገድ ነው።

በዚህ መሠረት በአሜሪካ ያለው የርዕደ መሬት ካርታ በየጊዜው እንዲሻሻል ይደረጋል።

አንዳንዴ ግምቱ የተጋነነ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ሳን አንደርስ በ10 ሺህ ዓመት አንዴ የሚከሰት ርዕደ መሬት እየተጠበቀ ነበር።

የተከሰተው ግን ውስን መሬት መንቀጥቀጥ ነበር። ከተጠበቀው ንዝረት 65% ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል።

የመሠረተ ልማት ዝርጋታ

የጂኦሎጂ ባለሙያዎቹ ጥንዶች የተገናኙት ዓለት ላይ ምርምር ሲያደርጉ ነው።

የኒውክሌር ማብላያና ግድብን ጨምሮ ሌሎችም መሠረተ ልማቶች ያላቸውን አቅም የሚፈትሹት በዓለቶቹ አማካኝነት ነው።

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በኒውክሌር ማብላያ አቅራቢያ ያለ የርዕደ መሬት እንቅስቃሴን ያጠናል።

መሀንዲሶች ምርምር ሲያከናውኑ እንዴት ዓለቶቹ እንደተከሰቱ ያጠናሉ።

ጥንዶቹ በዲያብሎ ሸለቆ አቅራቢያ ያለ የኒውክሌር ማብላያ ላይ ጥናት ሲሠሩ ከዓለቶች በተገኘ መረጃ ሊደርስ ይችል የነበረ አደጋን በ50 በመቶ መቀነስ የሚያስችል ካርታ አዘጋጅተዋል።

በፈረንሳይ የኒውክሌር ማብላያ እና ውሃን መሠረት ባደረጉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያዎችም ተመሳሳይ ጥናት እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል።

በቀጣይ ሬድዮአክቲቭ የሆነ ተረፈ ምርት የት ሊቀበር ይችላል የሚለውንም መወሰን የሚያስችል መረጃ እንደሚያስገኙ ይታመናል።

በነቫዳ የኒውክሌር ተረፈ ምርት በዩካ ተራራ ሊቀበር ታስቦ የነበረ ቢሆንም በአቅራቢያ ካሉ ዓለቶች በተገኘው መረጃ መሠረት ሐሳቡ ተሰርዟል።

በአካባቢው ያሉ ዓለቶች እስከ 80,000 ዓመታት ድረስ እንደቆዩ ማወቅ ተችሏል።

እነዚህን አስደናቂ ዓለቶች የሚያይ ሰው ምን ያህል ዘመን፣ ምን ዓይነት ክስተት አልፈው እንደቆዩ ሳያስብ አያልፍም።