ትግራይ፡ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ያለኝ የምግብ ክምችት የፊታችን ዓርብ ይጠናቀቃል አለ

የፎቶው ባለመብት, SOULEYMANE AG ANARA
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ያለው የምግብ ክምችት የፊታችን ዓርብ ይጠናቀቃል አሉ።
ዴቪድ ቢዝሊይ የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ የምግብ ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጋቸው ሰዎች እርዳታውን ለማቅረብ በቀን 100 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንዳለባቸው አመልክተዋል።
ኃላፊው በአሁኑ ወቅት ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን የጫኑ 170 ተሽከርካሪዎች አፋር ላይ መቆማቸውን እና መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
ዴቪድ ቢዝሊይ በትዊተር ገጻቸው ሰዎች እየተራቡ ነው ካሉ በኋላ፤ እነዚህ ተሸከርካሪዎች አሁኑኑ መንቀሳቀስ ሊፈቀድላቸው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1
የፌደራሉ መንግሥት የህወሓት አማጺያን በትግራይ እና አፋር አዋሳኝ ድንበር ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ በርካታ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎችን ጭነው ወደ ትግራይ በመጓዝ ላይ የነበሩ መኪኖች ጉዟቸው እንዲገታ ሆኗል ማለቱ ይታወሳል።
የወቅታዊ ጉዳዮች መረጃ አጣሪ በትዊተር ገጹ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ከወሰነባቸው ምክንያቶች አንዱ የሰብዓዊ አቅርቦት ለሕዝብ እንዲደርስ መሆኑን በማስታወስ "ይህ የሰብዓዊ አቅርቦት እንቅስቃሴ ግን በህወሓት ትንኮሳዎች እየተደናቀፈ ነው" ብሏል።
ጨምሮም "ዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ በተለይ በትግራይ የሚሰሩ ተቋማት ህወሓት በአፋር ክልል ላይ የሚያደርሰውን ትንኮሳዎች እንዲያቆም እና የሰብዓዊ እርዳታ ቁሳቁሶችን የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ እንዲገቡ ጫና ማሳደር አለባቸው" ብሏል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2
በተመሳሳይ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ወደ ትግራይ ሊጓጓዝ የተጫነን የእርዳታ እህል የያዙ 170 ከባድ ተሽከርካሪዎች ህወሓት አማካኝነት ጉዟቸው ተገትቶ መቆማቸውን ዛሬ አስታወቁ ሲል የትራንስፖርት ሚንስቴር ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስነብቧል። ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ምግብ እና ውሃ ሊያልቅ ይችላል ብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ወደ 24 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች የተጠለሉባቸው ጣቢያዎችን መድረስ አለመቻሉ እና በስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎቹ ምግብ እና ውሃ አልቆ ሊሆን ይችላል ብሏል።

የፎቶው ባለመብት, Ethiopian News Agency
የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽኑ በማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ የተባሉ መጠለያ ጣቢያዎች እና በአቅራቢያቸው ግጭት መኖሩን ገልጾ ሁለት ስደተኞች ተገድለዋል ብሏል።
መንግሥታዊው የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ የህወሓት አማጺያን መሠረተ ልማቶችን ለወታደራዊ አገልግሎት እያዋሉ በመሆኑ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው ማለቱ ይታወሳል።
በማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ ለአንድ ወር የሚበቃ የምግብ እደላ ከተደረገ ሳምንታት ማለፋቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ባባር ባሎች ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ "ለስደተኞች የተሰጠው ምግብ አልቆ ሊሆን ስለሚችል የረሃብ አደጋ ሊከሰት ይችላል" ያሉ ሲሆን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትም እየቀነሰ ነው ብለዋል።
አብዛኛውን ትግራይ ተቆጣጠሮ የሚገኘው ህወሓት በበኩሉ በክልሉ ስለሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን በመተለከተ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ላይ በትግራይ ያሉ ስደተኞች መፈናቀል እና ተፈጽመዋ የተባሉ ጥቃቶች እጅጉን አሳስቦኛል ብሎ ነበር።
በትግራይ የጤና አገልግሎት አቅርቦት እጅግ የተወሰነ ነው ያሉት ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፋዱላ ቻኢብ ናቸው።
"በትግራይ የጤና አገልግሎት አቅርቦት እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ የተገደበ ነው" ካሉ በኋላ በሺህዎች የሚቆጠሩ መሠረታዊ የጤና አግልግሎት እያገኙ አይደለም ብለዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባዋ ለሞት ሊዳርግ የሚችል በከፍተኛ ሁኔታ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ልጆች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።














