ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የዘንድሮው የትንሳዔ በዓል አከባበር በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በምስል
የፎቶ ባለሙያው ኤድዋርዶ ሶተራስ ቅዳሜና እሁድን በጥንታዊቷ የላሊበላ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በላሊበላ የውቅር ቤተ ክርስቲያናት የትንሳዔን በዓል ሲያከብሩም በፎቶዎች እንዲህ አስቀርቷቸዋል።
ላሊበላ ከዓለት ተፈልፍለው የተሰሩት ውቅር አብያተ ክርስቲያናቷ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆነው ተመዝግበዋል።
ከተማዋ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ለተወሰነ ጊዜ በትግራይ ኃይሎች እጅ የቆየች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በፌደራሉ መንግሥት ቁጥጥር ስር ትገኛለች።