የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ እንዲካሄድ የቀረበው ሃሳብ ተቃውሞ ገጠመው

የዓለም ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ መከናወኑ በሌሎች ስፖርቶች እና በሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ችግር ያስከትላል ይጥላል ሲል ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቃውሞውን ገለጸ።

ፊፋ በየሁለት ዓመቱ የወንዶችን የዓለም ዋንጫ ለማካሄድ የያዘው ዕቅድ ለሌሎች ስፖርቶችና የሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ ሥጋት ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚያምን የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (ኢይኦሲ) ገለጸ።

በየሁለት ዓመቱ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ እና በታላቁ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች መካከል በተመሳሳይ ጊዜ የመደረግ እና መደራረብ ሊፈጥር ይችላል። የኦሊምፒክ የሴቶች የእግር ኳስ ውድድርም ትልቅ ቦታ ያለው ነው።

የአይኦሲ በመግለጫው ከሌሎች ውድድሮች ጋር የሚያጋጥም መደራረብ "የስፖርትን ብዝሃነት እና ልማት" ያዳክማል ብሏል።

አክሎም ተጨማሪ የወንዶች ስፖርት መኖሩ ለሴቶች እግር ኳስ "ተግዳሮቶችን" ይፈጥራል ብሏል።

የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር እና 10 የአውሮፓ ሴቶች ሊጎች በሰጡት የጋራ መግለጫ ዕቅዶቹ "በጣም ጎጂ" ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

የሴቶች የዓለም ዋንጫ ከትልቅ የወንዶች ውድድር ጋር በተመሳሳይ ወቅት ይካሄዳል በማለት በመስከረም ወር ደግሞ የወንዶች ሊጎች የዓለም የእግር ኳስ የበላይ አካል ሃሳብን መቃወማቸውን አረጋግጠዋል።

የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጫዋቾችን ደኅንነት ጨምሮ በሌሎች የስፖርት አካላት የተነሱትን ስጋቶችን እንደሚጋራ ገልጾ፣ የዓለም ዋንጫን ድግግሞሽ በእጥፍ ማሳየቱ "በተጫዋቾች አካላዊ እና አእምሯዊ ጤና ላይ የበለጠ ከባድ ጫና ይፈጥራል" ብሏል።

የኦሊምፒክ የበላይ አካል ከስፖርተኛ ተወካዮች ጋር ሰፊ ምክክር እንዲደረግ የሚደረገውን ጥሪ እንደሚደግፍ ገልጾ ይህ "በግልጽ እንዳልተደረገ" አስታውቋል።