ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አልሻባብ ተጠርጣሪ ጠንቋይ እና ወታደር ገደለ - ሪፖርት
የአልሻባብ አልሞ ተኳሽ ቡድን በደቡብ ጃማሜ ከተማ አንድ የተጠረጠረ ጠንቋይን ጨምሮ ሁለት ሰዎችን መግደሉን ከጂሃዲስት ቡድኑ ጋር ግንኙነት ያለው የሚዲያ ጣቢያ ዘግቧል።
ግድያው የተፈፀመውም በደቡብ ጃማሜ ከተማ ነው።
የአልሻባብ ደጋፊ የሆነው ሶማሌ ሜሞ የተባለው ድረ-ገጽ የግለሰቦቹ በጥይት ሲገደሉ ለመመልከት ብዙ በርካታ ሕዝብ በአደባባይ መሰብሰቡን አስፍሯል።
ከተገደሉት መካከል አንዱ ወታደር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ አስማት ያከናውናል ተብሎ የተጠረጠረ ጠንቋይ ነው።
ጥንቆላ በአልሻባብ ዘንድ በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው።
አልሻባብ በአብዛኛው የመንግሥት ወታደሮችን ፣ ከአገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ የስለላ ድርጅቶች ጋር በመስራት የሚከሰሱ ሰላዮችን ፣ እና በጥንቆላ የተከሰሱትን ግድያ በየጊዜው ያካሂዳል።