ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ኦስካር፡ የእዚህ ዓመቱ የኦስካር ሽልማት ሆሊዉድን ይቀይረው ይሆን?
ከአምስት ዓመታት በፊት 2015 (እአአ) ለ'አካዳሚ አዋርድ' ሽልማት የቀረቡት 20 ዕጩዎች በሙሉ ነጮች መሆናቸውን ተከትሎ፤ የኦስካር ዕዕጩዎቹ እና ተሸላሚዎች ነጮች ብቻ ናቸው በሚል ትችት ገጥሞት ነበር።
የሽልማት ድርጅቱ በማኅበራዊ ሚዲያ የደረሰበትን ጠንካራ ትችት ተከትሎ ማስተካከያዎችን አድርጓል። የዘንድሮው የኦስካር ዕጩዎችም ከመቼውም ጊዜ በላይ ብዝሃነት የተንጸባረቀበት ነው ተብሏል።
በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት ላይ ታሪክ ሊጽፉ ይችላሉ የተባለላቸው የሚከተሉት ዕጩዎች ናቸው።
ምርጥ ዳይሬክተር
ክሎዊ ቻው ምርጥ ዳይሬክተር ሆና የምትመረጥ ከሆነ በዚህ ዘርፍ ሽልማት የተቀዳጀች የመጀመሪያዋ ነጭ ያልሆነች ሴት ትሆናለች።
ይህም ብቻ ሳይሆን ክሎዊ አሸናፊ የምትሆን ከሆነ በ92 ዓመት የወድድሩ ታሪክ ሁለተኛዋ አሸናፊ ሴት እንደምትሆን ይጠበቃል።
ከዚህ ቀደም ካትሪን ቢግሎ ኢራቅ ውስት በተካሄደው ጦርነት ላይ በሚያጠነጥነው 'ዘ ሀርት ሎከር' በተሰኘው ፊልሟ የምርጥ ዳይሬክተርነት ሽልማትን አሸንፋ ነበር።
ቻይናዊቷ ፊልም ሰሪ ክሎዊ ቻው፤ 'ኖማድላንድ' በተሰኘው ፊልሟ 2008 (እአአ) የፋይናንስ ቀውስ በኋላ ሥራዋን ያጣች ሴት በመላው አሜሪካ ጉዞ ስለምታደርግ ሴት ታሪክን ያስቃኛል።
ክሎዊ ቻው ለዘንድሮ የኦስካር ሽልማት ዕጩ ሆና የቀረበችው በምርጥ ዳይሬክርነት ብቻ አይደለም። ቻው 'በምርጥ ፊልም'፣ 'በምርጥ የፊልም ጽሁፍ' እና 'በምርጥ ኤዲቲንግ' ዕጩ ሆና ቀርባለች።
ክሎዊ ቻው ዕጩ ሆና በቀረበችባቸው አራት ዘርፎች አሸናፊ ከሆነች በሽልማቱ ታሪክ ሁለተኛ ሰው ትሆናለች። በተጨማሪም ቀዳሚዋ እንስት በመሆን ታሪክ ታስመዘግባልች።
በሽልማቱ ታሪክ ውስጥ በበርካታ ዘርፎች አሸናፊ በመሆን የዲዝኒ ኢንተርቴይመንት መስራች ዋልት ዲዝኒ ላይ የሚደርስ የለም። ዋልት ዲዝኒ 22 የኦስካር ሽልማቶችን በመውደስ ቀዳሚ ባለሙያ ነው።
1954 (እአአ) ላይ በምርጥ ዘጋቢ ፊልም፣ በምርጥ አጭር ዘጋቢ ፊልም የተባሉትን ጨምሮ በአራት ዘርፎች አሸናፊ ሆኖ ነበር።
ምርጥ ፊልም
ትልቅ ሥፍራ በሚሰጣቸው የኦስካር ዘርፎች ዕጩ ሆና የቀረበች ሴት ክሎዊ ቻው ብቻ አይደለችም።
እንግሊዛዊቷ ተዋናይት እና ጸሐፊ ኤሜራልድ ፌነል 'ፕሮሚሲንግ ያንግ ውመን' በሚለው ፊልሟ በምርጥ ፊልም፣ በምርጥ ዳይሬክተር እና በምርጥ የፊልም ጽሑፍ ዘረፎች ዕጩ ሆና ቀርባለች።
በሦስቱም ዘርፎች ድል ከቀናት፤ ትልቅ ትኩረትን በሚያገኙት ዘረፎች አሸናፊ የምትሆን የመጀመሪያዋ ሴት ትሆናለች።
የኦስካር ሽልማት በማግኘት ታሪክ ሊሰሩ የሚችሉ ደግሞ ፕሮዲዩሰር ሻክ ኪንግ፣ ቻርልስ ዲ ኪንግ እና ራይን ኮግለር ናቸው። ሦስቱ ባለሙያዎች 'ጁዳስ ኤንድ ብላክ ሜሲህ' ከተባሉት ፊልሞች ጀርባ ያሉ ናቸው።
ለሽልማቱ መመረጥ ከቻሉም የመጀመሪያዎቹ ጥቁር የፊልም ባለሙያዎች ስብስብ ይሆናሉ።
ምርጥ ተዋናይ
በዚህ ዓመቱ የኦስካር ሽልማት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስሊም ተዋናይ በምርጥ ትወና በዕጩነት ቀርቧል።
በዚህም ሙስሊሙ ሪዝ አህመድ የመስማት ችግር ያጋጠመው የአንድ ባንድ የከበሮ ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ገጸባህሪን ወክሎ 'ሳውንድ ኦፍ ሜታል' በተሰኘ ፊልም ላይ በመተወን በዕጩነት ቀርቧል።
ሙስሊም ተዋናይ በኦስካር መድረክ ላይ ታሪክ ሲሰራ የመጀመሪያው አይደለም። ከሦስት ዓመት በፊት ማሄርሻላ አሊ የተባለው ሙስሊም ተዋናይ 'ሙንላይት' በተሰኘው ፊልም ላይ በነበረው ተሳትፎ ምርጥ ረዳታ ተዋናይ ተብሎ ተሸልሞ ነበር።
ከዚያም ከሁለት ዓመት በኋላ በተመሳሳይ አንድ በ1960ዎቹ ኮንሰርት ላይ በፒያኖ ተጫዋችንት በግሪክ መጽሐፍ ላይ የቀረበን ገጸ ባህሪን ወክሎ በተጫወተበት ፊልም በድጋሚ ሽልማት አግኝቶ ነበር።
ነገር ግን ከዚያ በኋላ ሌላ ሙስሊም ተዋናይ ለኦስካር ሽልማት ዕጩ ሆኖ እስኪቀርብ እሳካለንብት ዓመት ድረስ ሁለት ዓመታት መጠበቅ ግድ ሆኖ ነበር።
በዚህ ዓመት ሪዝ አህመድ በሽልማቱ አሸንፎ ክብረ ወስን ለማስመዝገብ ከተዘጋጀ ከሌላ ብሪታኒያዊ ተዋናይ ፉክክር ገጥሞታል።
እንደ አብዛኞቹ የምርጥ ተዋናይነት ሽልማት አሸናፊዎች ሁሉ ሰር አንተኒ ሆፕኪንስ ነጭ ተዋናይ ናቸው። የ83 ዓመቱ ተዋናይ በዚህ ዓመት ሽልማት ላይ ከተመረጡ "ዘ ፋዘር' በተሰኘው ፊልም ላይ በነበራቸው ሚና በዕድሜ የገፉ ቀዳሚው ተሸላሚ ሆነው ታሪክ ያስመዘግባሉ።
ሰባት ጊዜ ለሽልማት ታጭታ ያልተሳካላት
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካዊቷ የረዥም ዘመን ተዋናይት ለስምንተኛ ጊዜ በዘንድሮ ኦስካር ሽልማት ላይ ዕጩ ሆኖ ቀርባለች።
ከዚህ ቀደም ሰባት ጊዜ ዕጩ ሆና አንዴም ለማሸነፍ አልቻለችም ነበር። ተዋናይት ግሌን ክሎስ ለ8ኛ ጊዜ ዕጩ ሆና ማሸነፍ ካልቻለች አዲስ ታሪክ ታሪክ ታስመዘግባለች።