ቴክኖሎጂ፡ ስለምን ፌስቡክ እና አፕል አይስማሙም ?

የአፕሉ ቲም ኩክና የፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የአፕሉ ቲም ኩክና የፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ

የኩባንያዎች የንግድ ውድድር ትልልቅና ተፎካካካሪ የሆኑት ኮካ ኮላ እና ፔፕሲን፣ ቦይንግ እና ኤርባስን፣ ማክዶናልድ እና በርገር ኪንግን አንድ የጋራ ነገር እንዲኖራቸው አድርጓል።

ይህም በልጦ ለመገኘት የሚደረግ ፍልሚያ፤ ለዚያም ነው የፌስቡክ እና የአፕል ውዝግብ በጣም ሳቢ የሆነው።

ሁለቱም ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መሆናቸው ላይ ነው ተመሳሳይነታቸው የሚያበቃው። ከሞላ ጎደል ሁሉም የፌስቡክ ገቢዎች የሚገኙት ከማስታወቂያ ሲሆን አፕል ደግሞ በአብዛኛው ከቁሳቁስ እና ከመተግበሪያ ሽያጭ ነው ገቢው።

እንደ እውነቱ ከሆነ ሁለቱ ኩባንያዎች እርስ በርሳቸው አይወዳደሩም፣ ግን ደግሞ አይዋደዱም።ለዓመታት የአፕሉ አለቃ ቲም ኩክ ፌስቡክ ተጠቃሚዎቹን እንደ ምርት በመቁጠር ከማስታወቂያ ገንዘብ ከማግኘቱም በላይ በፍጥነት የግል ሚስጢርን ያባክናል ይላሉ።

የፌስቡኩ አቻቸው ማርክ ዙከርበርግ በበኩላቸው የአፕል ምርቶች ውድ በመሆናቸውና ፌስቡክን ለመተቸት ድብቅ ዓላማ አለው በማለት ይተቻሉ።እንደ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ባለፈው ዓመት አፕል የፌስቡክ ማበልጸጊያ መሣሪያዎችን እስከማቋረጥ ደርሷል።

ባለፈው ሳምንት አዲስ እሰጣ አገባ ተፈጥሮ ግንኙነቶችን የበለጠ የከፋ አድርጎታል፡፡

በቁስል ላይ እንጨት መስደድ

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አፕል ሰዎች መረጃዎቻቸውን ይበልጥ እንዲቆጣጠሩ የሚያደርግ 'አፕ ትራኪንግ ትራንስፓረንሲ' የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ይህም ቀደም ሲል የነበረውን አሠራር በመቀየር ደንበኞች እንደ ፌስቡክ ያሉ መተግበሪያዎቻቸውን እየመረጡ መረጃዎችን እንዲጠቀሙ ያግዛል።

ከፍተኛ ትርፍ ለማግኘት ያለሙ ማስታወቂያዎችን ለሚሸጠው ፌስቡክ ይህ ትልቅ ችግር ነው። ይህም ንግዳቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ በግልፅ ይናገራሉ።

አፕል መተግበሪያዎችን የሚሠሩ እንዲዘጋጁ ጊዜ ለመስጠት የታቀዱትን ለውጦች እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ ላለመተግበር ወስኗል።ጄን ሆቫርት ባለፈው ሳምንት ለውጡ ለምን እንደዘገየ በሚገልጽ ደብዳቤ ላይ ዙከርበርግን ከመውቀስ ወደ ኋላ አላሉም።

"የፌስቡክ ሥራ አስፈፃሚዎች በተቻለ መጠን ብዙ መረጃዎችን መሰብሰብ ዓላማቸው መሆኑን ግልፅ አድርገዋል" በማለት።"ይህም የተጠቃሚዎች ግላዊ ምስጢርን አለማክበር ተስፋፍቶ መቀጠሉን ያሳያል" ብለዋል።

ፌስቡክም ለዚህ ምላሽ ሰጥቷል። "ዋናውን የገቢ ጉልበታቸውን ተጠቅመው ለራሳቸው መረጃ እየሰበሰቡበት ተፎካካሪዎቻቸውም ተመሳሳይ መረጃን እንዳይጠቀሙ በሚባል እየከለከሉ ነው" ብለዋል።

"የሚናገሩት ስለ ግላዊ መረጃ ቢሆንም ዋናው ነገር የገቢ ትርፍ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

ይህም ከፌስቡክ የበለጠ የንግድ አምሳያ አለው በሚል ኩራት ለሚሰማው አፕል በቁስሉ ላይ እንጨት መስደድ ነው።

እስከ 2010 ድረስ የአፕል መስራች የሆነው ስቲቭ ጆብስ ፌስቡክን በግላዊ መረጃ ዙሪያ ማስጠንቀቁ ተዘግቧል። ፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ለመሸጥ መረጃዎችን መጠቀም ይችል ነበር ነገር ግን "ያንን ላለማድረግ መርጠናል" ብለዋል የአፕል የወቅቱ አለቃ ኩክ እ.አ.አ በ 2018።

የሲሊከን ቫሊው ባለሃብት እና የዙክድ መጽሐፍ ደራሲ ሮጀር ማክናሚ የፌስቡክ አድናቂ አይደሉም።"የአፕል አንዱ ባህል ደንበኞቹን ማብቃት ነው። የፌስቡክ ባህል ደግሞ ተጠቃሚዎቹን መበዝበዝ ነው" ብለዋል።"ከታሪክ አኳያ እንኳን ቢታይ አፕል ሌሎች ሰዎችን ለመንቀፍ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ይህን ላለማድረግ መርጧል።

የፌስቡክ አሠራር ምን ያህል አናዳጅ እንደሆነ ይህ ማሳያ ይመስለኛል" ሲሉም ተናግረዋል።ፌስቡክስ ምክንያት አለው? እውነት አፕል ተወዳዳሪዎችን ለማፈን የገበያ የበላይነቱን ለመጠቀም እየሞከረ ነውን?

የአፕል የማስታወቂያ ገቢ በአንፃራዊነት አነስተኛ ቢሆንም ሞርጋን ስታንሊ እንደሚሉት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ይህ ገቢው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያድግ ተተንብይዋል።ስለዚህ የፌስቡክ የተጠቃሚዎች መረጃን በመያዝ ለራሱ ገቢ ማግኛ ለማድረግ እየሞከረ ነው?ይህ እንግዳ ነገር ሊሆን ይችላል።

ማደብዘዝ

አሁን አሁን በጣም ከተለመዱት የአሜሪካ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች አንዱ የአፕል የግላዊ መረጃ ጥበቃ ዘመቻ ነው።"አንዳንድ ነገሮች መጋራት የለባቸውም። አይፎን በዚህ በኩል እንድትጠብቁ ያግዛችኋል" የሚል ነው የማስታወቂያ ዘመቻ አለው።አፕል የግል ምስጢራዊነት ተወዳጅ መሆኑን እና ይህንንም ቀለል አድርጎ ማየት እንደማይገባ ያምናል።

ኢ-ፍትሃዊነትአፕል ግን በሁሉም ዘርፍ ገበያውን በብቸኝነት /ሞኖፖሊ/ እንደተቆጣጠረ ይነገርለታል።አፕ ስቶርን በመጠቀም መተግበሪያ የሚሠሩት ላይ ኢ-ፍትሃዊ ሕግን ይጭናል ከተባለ በኋላ በተከታታይ ሕዊ ሂደት ውስጥ ገብቷል።በተጨማሪም ኩባንያው ተገቢውን የግብር ክፍያን አይከፍልም የሚሉ ክሶች ቢነሱበትም ደርጅቱ ግን ያስተባብላል።

የግላዊነት እና ከምንም ጋር ያለመነካካት ክርክር በእርግጥ ከዙከርበርግ ጋር ይመደባል።እ.አ.አ በ2014 ኩክ ደንበኞቹን እንደ ምርት በመቁጠር ፌስቡክን ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ሲተቹ የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለታይም መጽሔት ምላሽ ሰጥተው ነበረ።

"የሚያበሳጨኝ ብዙዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የማስታወቂያ ንግድ አሠራርን ከደንበኞች ጋር የማይስማሙ እንደሆነ አደርገው የሚያመሳስሉት ናቸው።"

"እንደምታስቡት ለአፕል እየከፈላችሁ ስለሆነ ከእነሱ ጋር እንደምትስማሙ ነው? ከእነሱ ጋር ብትስማሙ ኖሮ ምርቶቻቸውን በጣም ርካሽ ያደርጉ ነበር" ብለዋል። ይህ ምናልባት አንድ አሳማኝ ነጥብ አለው፤ በዚህም አፕል በዓለም ላይ በጣም ሀብታም ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ ነው።

የስልክ ጦርነት

የዚህ የጋራ ውጥረት ሌላው እንግዳ ነገር የሁለቱ ኩባንያዎች አንዱ በአንዱ ላይ ጥገኛ መሆናቸው ነው። አይፎን ላይ ፌስቡክ (ከዋትስአፕ እና ከኢንስታግራም ጋር) የማይገኝ ቢሆን ኖሮ ስልኩ ለብዙ ደንበኞች ዝቅ ያለ ደረጃ ይኖረው ነበር።

በተቃራኒው ደግሞ ሰዎች ፌስቡክን በአይፎን ላይ መጠቀም ባይችሉ ኖሮ ሰዎች ሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ይፈልጉ ነበር?ሁለቱም ኩባንያዎች ጤናማ እና ጠንካራ የሥራ ግንኙነት ቢኖራቸው ትርጉም ይሰጣል የሚሉ በርካቶች ናቸው።

ግን እንደዛ አይደለም። የአፕል ባለሙያ የሆኑት ካሮላይና ሚላኔሲ እንደሚሉት ሁለቱ ኩባንያዎች ዓለምን በተለየ መንገድ ከማየት ባለፈ በመካከላቸው ያለው ጥላቻ ባህላዊና ግላዊ ነው።"በፍልስፍና ረገድ የተለያዩ ናቸው" ይላሉ።"አፕልን እንመልከት።

ፌስቡክ በደንበኞቻቸው ላይ ስላለው ጠባይ የሚያሳስባቸው ከሆነ በአፕል መሳሪያዎች ላይ ለምን ፌስቡክን እንደመተግበሪያ እንዲኖር ይረፈቅዳሉ?"ይህም ወደ ጉዳዩ ጫፍ ይደርሳል።

እስካሁን እኒህ ሁለት ኩባንያዎች የማይስማሙ ናቸው።ይህ የስልክ ጦርነት ነበር ቢሆንም እውነታው ግን ግንኙነታቸው ስሜታዊ ነበር።አፕል አሁን እያቀረበ ያለው መተግበሪያ ግን ከዚህ ጦርነት አለፍ ያለ ነው።

በዚህ ጉዳይ ግላዊ መረጃ ላይ ያላቸው አባዜ ለፌስቡክ ጥሩ አይደለም። አዳዲሶቹ ሕጎች ማኅበራዊ ድረ-አምባውን ይጎዱታል እየተባለ ነው።በትላልቅ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ ከሚኖሩ ተወዳዳሪዎች መካከል የፌስቡክ እና የአፕል ከፊት ሲታይ በጣም አናሳ ሊሆን ይችላል።

ጉግል የፌስቡክ ግልጽ ተወዳዳሪ ሲሆን ማይክሮሶፍት እና ጉግል ደግሞ የአፕል ተቀናቃኞች ናቸው።ግን የግላዊ መረጃ ጉዳይ በፌስቡክ እና በአፕል መካከል የማይጠፋ እሳት አስነስቷል።

እናም እ.አ.አ 2021 ተፎካካሪነቱን ይበልጥ ያቀጣጥለዋል።