ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የኮሮናቫይረስ ስጋት ባጠላበት በርካቶች በአንዴ ተሞሽረሩ
በደቡብ ኮሪያዋ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት ባጠላበት በሺዎች የሚቆጠሩ ጥንዶች አንድ ላይ ተሞሸሩ።
ከመዲናዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ከተማ በተዘጋጀው የሠርግ ስነ-ስርዓት ላይ ሙሽሮች አፍን እና አፍንጫ መሸፈኛ 'ማስክ' አድርገው ታይተዋል።
ቀላል የማይባሉት ሙሽሮችና የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ማስክ በማድረግ ከቫይረሱ እራሳቸውን ለመጠበቅ ሲሞክሩ የታዩ ሲሆን በሽታው ያላሰጋቸው 'ማስክ' ለምኔ ብለዋል።
ከ60 አገራት የተሰባሰቡ ወደ 6ሺህ የሚጠጉ ጥንዶች በዝግጅቱ ላይ ትዳር መስርተዋል።
የዝግጅቱ ታዳሚዎቹ ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የደም ሙቀታቸው ተለክቷል።