ደም የለበሰው የኢንዶኔዥያ ሰማይ 'ማርስ' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል

በጃምቢ ክልል መካር ሳሪ የተሰኘው መንደር

የፎቶው ባለመብት, Eka Wulandari

የምስሉ መግለጫ, የዓለም መጨረሻን የሚተነትኑ ፊልሞች ላይ የሚታየውን የዓለም መጨረሻን ዕጣ ፈንታ የሚመስለውን ጃምቢ በተሰኘው የኢንዶኔዥያ አካባቢ ከሰሞኑ ይታይ የነበረው ሰማይ።

በኢንዶኔዥያ ጃምቢ ክልል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ይታይ የነበረው ደም የለበሰ ይመስል ነበር። የዚህም ምክንያት አብዛኛውን የሃገሪቱን ክፍል የሚሸፍነው ደን የእሳት ሰለባ መሆኑ ነው።

የሰማዩን ፎቶግራፎች ያጋራችው የጃምቢ ክልል ነዋሪ 'ዓይኖቿን እና ጉሮሮዋን ያማት' እንደነበር አሳውቃለች።

በየዓመቱ ኢንዶኔዥያ ውስጥ የሚነሱት እሳቶች ሰማይን የሚሸፍኑ ከመሆናቸውም በተጨማሪ አጠቃላዩን የእስያን ምሥራቅ ክፍል ጭስ ማልበሳቸው የተለመደ ክስተት ነው።

ይህ ያልተለመደ የሰማይ ክስተት 'ሬይሌይ ስካተሪንግ' በሚባል እንደሚታወቅ የሜትሮሎጂ ባለሙያ ለቢቢሲ አሳውቀዋል።

ባለፈው ቅዳሜ እኩለ ቀን አካባቢ የተከሰተውን ክስተት በፎቶ ካሜራዋ ያስቀረቻቸው ኤካ ዉላንዳሪ የምትባል የሜካር ሳሪ ነዋሪ ናት።

ያን ዕለት የነበረው ጭስ "በጣም ክብደት ነበረው" በማለት ገልፃዋለች።

በጃምቢ ክልል መካር ሳሪ የተሰኘው መንደር

የፎቶው ባለመብት, Eka Wulandari

የምስሉ መግለጫ, ፎቶግራፎቹ የውሸት ናቸው ሲሉ የነበሩትን አንሺዋ ተቃውማለች

የ21 ዓመቷ ወጣት ፎቶግራፎቹን በፌስቡክ ላይ ያጋራች ሲሆን፤ ካጋራችበት ሰዓት አንስቶ ከ34 ሺህ ጊዜ በላይ ሲጋራ ቆይቷል።

ብዙ ሰዎች ያነሳቻቸውን ፎቶግራፎች ለማመን እንደተቸገሩ ለቢቢሲ ትናግራለች።

"እነዚህ ፎቶግራፎች ግን የእውነተኛ ናቸው። በስልኬ ነው ያነሳዃቸው" በማለት ጭሱ ሰኞም ጠዋት እንደቀጠለ ትናገራለች።

በጃምቢ ክልል መካር ሳሪ የተሰኘው መንደር

የፎቶው ባለመብት, Eka Wulandari

የምስሉ መግለጫ, የሜካር ሳሪ መንደር ሰማይ ደማቅ ቀይ ሆኖ ነበር።

ኋላም የትዊተር ማህበራዊ ድረ ገፅ ተጠቃሚ ተመሳሳይ ፎቶግራፎችን ሲያጋራ ነበር።

"ይህ ማርስ አይደለም። ጃምቢ ነው" ሲል ዙኒ ሾፊ ያቱን ኒሳ ይጽፋል። አክሎም "እኛ ሰዎች እንደመሆናችን ንፁህ አየር ነው የሚያስፈልገን እንጂ ጭስ አይደለም" ብሏል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

Presentational white space

በኢንዶኔዥያ ሜቴዎሮሎጂ ተቋም በአካባቢው ደመቅ ያሉ ብዛት ያላቸው ምልክቶች ታይተው ነበር።

የሲንጋፖር ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኮህ ቲዬ ዮንግ ክስተቱ 'ሬይሌይ ስካተሪንግ' የሚባል መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ይህም በጭሱ ወቅት በሚፈጠሩ ጥቃቅን ነገሮች የሚፈጠሩ መሆኑን ያስረዳሉ።

"በጭሱ ወቅት 1 ማይክሮሜትር የሚያክሉ ጥቃቅን ነገሮች በብዛት የሚገኙ ሲሆን እነርሱ ግን የምናየውን ብርሃን ቀለም አይቀይሩም" በማለት ለቢቢሲ አክለው ያስረዳሉ።

"ከዚህም በቁጥርም በመጠንም የሚያንሱ ጥቃቅን ነገሮች ልናገኝ እንችላለን እነርሱም ከሰማያዊ ይልቅ ብርሃን ሲያርፍባቸው ቀይ ብርሃን የማንፀባረቅ ዝንባሌ አላቸው" ይላሉ።

ፎቶግራፎቹ በእኩለ ቀን ላይ መነሳታቸው ብርሃኑ ይበልጥ ቀይ መስለው እንዲታዩ ያደረጉ ይሆናል በማለትም ያስረዳሉ።

"ፀሐይ ከአናታችን በላይ ከሆነች ብርሃኑ ቀይ ሆኖ ይታየናል።"

ፕሮፌሰሩም አክለው ይህ ክስተት የአየሩን ሙቀት የመቀየር አቅም እንደሌለው ይናገራሉ።

የዚህ ዓመቱ ጭስ ከሌሎቹ ዓመታት ይልቅ ከባድ ነበር።

በኢንዶኔዥያ እና ማሌዥያ ፀሃያማ ወቅቶች የደን እሳት አደጋዎች የተለመዱ ናቸው።

አንዳንዴም ትላልቅ ድርጅቶችና አንዳንድ አርሶ አደሮች ፀሃያማ ወቅቱን ለመጠቀም ሲሉ ለመትከል እንዲመቻቸው የደኑን ቦታ በማቃጠል ለመውሰድ በሚጥሩበት ጊዜ እሳት ይነሳል።

ደንን እየቆረጡ የማቃጠሉ ዘዴ በብዙ የዓለም ክፍሎች ሰው የሚጠቀምበት ዘዴ ነው ምክንያቱም የታመመን ሰብል በቀላሉ እና ብዙ ገንዘብ በማይፈጅ ሁኔታ ማስለቀቅ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ በመሆኑ ነው።

ሆኖም እነዚህ እሳቶች አብዛኛውን ጊዜ ከሰው ቁጥጥር ውጪ ይሆኑና ለማቃጠል ያልታሰቡትን የደን ስፍራዎች ያያይዛሉ።

በኢንዶኔዥያ ይህ ዘዴ በሕግ የሚያስቀጣ ቢሆንም ለረዥም ዓመታት የሚጠቀሙበት ዘዴ ሆኖ ቀርቷል፤ ብዙዎች እንደውም የመንግሥት ድክመት እና ሙስና ውጤት ነው ይላሉ።