ጄኔራል አደም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ

ጄኔራል አደም መሐመድ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከጄኔራል አደም ሞሐመድ በተጨማሪ ሌፍ/ ጄኔራል ሞላ ኃ/ማርያምን የምድር ኃይል አዛዥ፤ ደመላሽ ገ/ሚካኤልን ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትዊተር ገፁ አስፍሯል።

ጄነራል አደም መሐመድ የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ነበሩ። ጄነራል አደም የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ኃላፊ ሳሉ ደመላሽ ገ/ሚካኤል ምክትላቸው ነበሩ።

ጄኔራል አደም መሐመድ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለአንድ ዓመት ያክል አገልግለዋል።