የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ሱዳን አቀኑ

የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ከሱዳኑ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀምነበር ጋር

የፎቶው ባለመብት, Minstry of foreign Affairs of Ethiopia

በውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ሱዳን አቀና።

የውጨ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳስታወቀው ልዑኩ ትናንት ቅዳሜ ምሽት ካርቱም የደረሰ ሲሆን፤ ዛሬ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ከሱዳኑ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጋር ውይይት አድርገዋል።

አቶ ገዱ ኢትዮጵያ የሱዳንን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ ለሱዳን ህዝብ ያላሰለሰ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ለወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሊውተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን አሳውቀዋል።

ሚንስትሩ ጨምረውም ኢትዮጵያ የኢጋድ ሊቀመንበር እንደመሆኗ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከተቀረው ዓለም አቀፍ ማህብረሰብ ጋር በመሆን በሱዳን ሰላማዊ እና ሁሉን አቀፍ ሽግግር እንዲኖር ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

ሊውተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን በበኩላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የሰጡትን ድጋፍ እና የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት አዲስ አበባ ባቀናበት ወቅት ለተደረገለት አቀባበል አመስግነዋል።

ሊውተኔት ጀነራል አብዱል ምንም እንኳ በሱዳን የመንግሥት ለውጥ ቢኖርም ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያለት መልካም ግነኙነት አይቀየርም ማለታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚንሰቴር አስታውቋል።