ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የጋብቻ ቃልኪዳናቸውን በአደባባይ በማድረጋቸው የታሰሩት ኢራናዊ ጥንዶች በዋስ ተለቀቁ
በሰሜናዊ ኢራን አራክ ከተማ በሚገኝ አንድ የገበያ ማእከል ነው ወንድየው ድንገት የ (ታገቢኛለሽ) ጥያቄን ያቀረበው።
የሴቷ እሽታ ለግብይት ቦታው ላይ በነበሩ በርካታ ሰዎች ጭብጨባና እልልታ ታጀበ የቃል ኪዳን ቀለበትም ታሰረ።
ነገር ግን ጥንዶቹ የእስልምና መርህን ጥሰዋል በሚል ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።
በአደባባይ ሴቶችና ወንዶች አንድ ላይ መታየት ወይም ፍቅርን በአደባባይ መግለፅ በኢራን እስላማዊ ህግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
የአካባቢው ፖሊስ ኮማንደር ሞሃመድ ካላጂ ለኢራኑ ፋርስ ኒውስ እንደገለፁት ጥንዶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት 'በህዝብ ጥያቄ' ነው።
ኮማንደሩ ነገሩ 'በምእራባዊያን የባህል ተፅእኖ ህዝባዊ ጨዋነትን መጣስ ነው' ብለውታል። የመታሰራቸው ምክንያትም ይህው ነው ብለዋል።