ፈረንሳያውያን ልጆቻቸውን እንዳይመቱ የሚከለክል ህግ ወጣ

ልጇን የምትቀጣ እናት

የፎቶው ባለመብት, Thinkstock

ኢትዮጵያ

በሱማሌ ክልል በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ የነበረው ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣት ስራው መቆሙን ኢቢሲ ዘገበ።

ነዳጅ የማውጣት ስራው የቆመውም አልሚው ኩባንያ የነዳጅ ምርቱን ለኢንዱስትሪዎች ለግብዓትነት ለማቅረብ የሚያስችለውን ፍቃድ ከመንግስት እስኪያገኝ ነው ተብሏል።

ኬንያ

የኬንያ መንግስት ታዳጊዎች ያለእድሜያቸው ልጅ እንዲወልዱ እያደረጉ ነው ያላቸውን የልቅ ወሲብ ድረ ገጾችን ሊዘጋ ነው።

በሃገሪቱ በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ ከ15 እስከ 19 ዕድሜ ያላቸው 350 ሺ ታዳጊ ሴቶች አርግዘዋል ተብሏል።

ማዕከላዊ አፍሪካ

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከሚገኙ ህጻናት ሁለት ሶስተኞቹ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ።

በተባበሩት መንግስታት የሕጻናት ድርጅት ዩኒሴፍ እንዳስታወቀው በሃገሪቱ ያለው ግጭት ሚሊዮኖችን አፈናቅሏል።

ናይጄሪያ

በ2015ቱ የናይጄሪያ ምርጫ ላይ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እጃቸውን ያስገቡ እንደነበር የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን ተናገሩ።

ፕሬዚደንቱ ባሳተሙት አዲስ መጽሃፍ ላይ የኦባማ ጣልቃ ገብነት ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት ያለፈና ያልተገባ ነበር ብለዋል።

ፈረንሳይ

የፈረንሳይ ፓርላማ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዳይመቱ የሚከለክል ህግ አጸደቀ።

ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን ስልጣን ከሃይል በጸዳ መልኩ መጠቀም አለባቸው ብለዋል የፓርላማ አባላቱ።

ጀርመን

የጀርመኗ መራሄ መንግስት አንጌላ መርክል የሚበሩበት አውሮፕላን ባጋጠመው ችግር ምክንያት ያልተቀደ ቦታ አረፈ።

ሜርክል የቡድን 20 ሃገራት ስብሰባን ለመሳተፍ ወደ አርጀንቲና እየሄዱ ነበር።

ህንድ

በህንዷ ሙምባይ ከተማ የምትኖር አንዲት የ21 ዓመተ ሴት ከ17 ዓመት ታዳጊ ጋር ትዳር መስርተሻል ተብላ በቁጥጥር ስር ዋለች።

ፖሊስ እንዳስታወቀው የሙሽራው እናት ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ልጄን ያለአግባት ተጠቅማበታለች የሚል ክስ አቅርበዋል።

ኮሪያዎች

ከአስር ዓመታት በላይ ቆይታ በኋላ የደቡብ ኮሪያ ባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሜን ኮሪያን ድንበር አልፎ መግባት ቻለ።

ድንበር የተሻገረው ባቡር ሰሜን ኮሪያ ዘመናዊ የባቡር መስመር እንድትዘረጋ የሚረዳ ቡድን መጫኑ እየተነገረ ነው።