ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣኑን ባቡር በይፋ አስመረቀች
ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን የሆነውን ባቡር አስመረቀች ፤ ባቡሩ የንግድ ከተማ ከሆነችው ካዛብላንካ ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከሏ ታንጌር ለመሄድ የሚወስደውን ጊዜ በግማሽ ይቀንሳል።
በምረቃ ሥነ ስርዓቱም ላይ የሞሮኮው ንጉስ መሃመድ ስድስተኛና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባቡሩን ለመመረቅ ከታንጊያር ከተማ ወደ መዲናዋ ራባት ጉዞ አድርገዋል።
ባቡሩ በሰዓት 320 ኪሎሜትር ወይም 198 ማይል ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህም ከዚህ ቀደም ከካዛብላንካ ወደ ታንጊር ለመሄድ በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር ወይም 124 ማይል ይወስድ የነበረውን በግማሽ ቀንሶታል።
የሞሮኮው አዲሱ ባቡር በደቡብ አፍሪካ መዲና ጆሐንስበርግ ከሚገኘው ኦሊቨር ታምቦ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማዋ የንግድ መናሀሪያ ሳንተን የሚያጓጉዘውን ፈጣን ባቡር በእጥፍ ይበልጠዋል።
ባቡሩ 2.4 ቢሊየን ዶላር (22.9 ቢሊዮን ድርሃም) እንደፈጀና በ7 ዓመታት እንደጠናቀቀ የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።