የአሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት፡ ዓለምን አደኽይቶ አደጋ ላይ ይጥላል

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በቅርቡ ባደረገው የዓለም ምጣኔ ሃብት ግምገማ በአሜሪካ እና በቻይና መካከከል የተጀመረው የንግድ ጦርነት ዓለምን 'አደኽይቶ' አደጋ ላይ ይጥላል በማለት አስጠንቅቋል።

አይኤምኤፍ የዘንድሮ እና የቀጣዩ ዓመት ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ይቀንሳል ሲል ትንበያ ሰጥቷል።

ከቻይና ጋር የተጧጧፈው የንግድ ጦርነት ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያስከትል ይችላልም ብሏል።

"የሃገራት የንግድ ፖሊሲ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው። በርካታ ሃገራት ደግሞ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ናቸው፤ ይህም ሌላ አደጋ ሊያስከትል ይችላል" ሲሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሞሪስ ኦብስፌልድ ይናገራሉ።

በቅርቡ ቻይና የ60 ቢሊየን ዶላር አዲስ የንግድ ታሪፍ በአሜሪካ ምርቶች ላይ መጣሏን አሳውቃለች። አዲሱ ታሪፍ የተጣለባቸው የዶናልድ ትራምፕ ተባባሪ ሃገራት የሚያመነጯቸው የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶችም ይገኙበታል።

ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ቤይጂንግን በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ከማድረግ እንድትቆጠብ አስጠንቅቀዋል።

"ገበሬዎቻችንን፣ ከብት አርቢዎቻችንን እና የኢንዱስትሪ ሠራተኞቻችንን የሚነኩ ከሆነ ከባድና ፈጣን የመልስ ምት ነው በቻይና ላይ የሚደረገው" ብለዋል።

የንግድ ጦርነቱ ለተቀረው ዓለም የሚኖረው አንድምታ ምን ይሆን?

እአአ በ2018 እና 2019 የዓለማችን አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገት 3.7 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ዓለም አቀሩ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ግን እድገቱን 3.9 በሞቶ ላይ አስቀምጦት ነበር።

በአሜሪካ እና በቻይና መካከከል እየተደረገ ያለው የንግድ ጦርነት የሁለቱንም ሃገራት ኢኮኖሚ የወጋ ግሽበት እንደሚያናጋው ይገመታል።

ኦብስፌልድ ዓለም "እየደኽየችና አደገኛ ቦታ" እየሆነች ትመጣለች ይላሉ፤ እንደ ባለሙያው ዕይታ የዓለም መሪዎች በሕብረት በመሥራት የኑሮን እና የትምህርት ደረጃን አሻሽለው እኩልነት እንዲኖር መጣር ይኖርባቸዋል።

አሜሪካ እንደዛተችው ወደ ሃገር ውስጥ በምታስገባቸው ተሽከርካሪዎች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ የምትጥል ከሆነ የንግድ ተዓማኒነት፣ በኢንቨስትመንትና በብድር ዋጋ ላይ ቋሚ ጉዳት እንደሚያደርስ አይኤምኤፍ አሳስቧል።

የእንግሊዝና እንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት የመለየት ጉዳይ

በመጪው የፈረንጆቹ ዓመት የእንግሊዝ ምጣኔ ሃብታዊ እድገት የ1.5 በመቶ እድገት ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።

አይኤምኤፍ እንደሚለው እንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት የመለየት ዕቅዷን በፍጥነት ካልጨረሰች የሃገሪቱ ኢኮኖሚ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል።

የእንግሊዝ ከሕብረቱ መውጣት የለምንም ጥርጥር አኢኮኖሚዋን እንደሚጎዳ ይታመናል።