በታንዛንያ የአንድ ሰፈር ነዋሪዎች የውሃ መስመር አበላሸታችኋል በሚል በቁጥጥር ስር ዋሉ

በታንዛንያ ደቡባዊ ክፍል የምቤዬ ግዛት ፖሊስ የአንድ ሰፈር ሰዎችን በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ ሰዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ለአካባቢው የውሃ አገልግሎት ለመስጠት የተዘረጋውን የቧንቧ መስመር ከጥቅም ውጪ አድርገውታል በማለት ነው።

የእስር ትእዛዙን ያስተላለፉት የግዛቲቱ ፖሊስ ዋና ኃላፊ በበኩላቸው የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን የውሃ መስመር በማበላሸታቸው ምክንያት በቁጥጥር እንደዋሉ ገልፀዋል።

የመገንጠል መብት ለማን? መቼ? በአካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት የደረሰበት የውሃ አገልግሎት መስጫ በብዙ ሺ ዶላሮች ወጪ የተሰራ ሲሆን፤ እስካሁን የአካባቢው ተመራጭን ጨምሮ ብዙ የአካባቢው ነዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ሁላችንም በጉዳዩ ስላልተሳተፍን የምርመራው ሂደት ንጹህ ሰዎችን እንዳያካትት እንሰጋለን እያሉ ነው።

ፖሊስ በበኩሉ ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ መገልገያዎችን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ብሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ይህንን ማድረግ ስላልቻሉ ለዚህ ውሳኔ እንደደረሰ ገልጿል።