ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በሲዳማ ክልል በትራፊክ አደጋ ምክንያት የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በሲዳማ ክልል ቦና ወረዳ አሑድ ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት ቢያንስ 71 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ዋቢ አድርገው እንደዘገቡት አደጋው የደረሰው አይሱዙ የተባለው የጭነት መኪና በርካታ ሰዎችን አሳፍሮ በመሄድ ላይ ሳለ ነው።
መኪናው ለሰርግ የሚጓዙ ሰዎችን አሳፍሮ ጋላና ተብሎ የሚጠራ ወንዝ አካባቢ ያለ መንገድ ስቶ ወደ ወንዙ መግባቱ ተነግሯል።
ኮሚሽኑ እስካሁን ቢያንስ የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል።
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች እያፈላለጉ እና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች እየረዱ እንደሆነ ኮሚሽነሩ አክለዋል።