አርሴናል ከቶተንሃም እና ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

አርሴናል ከቶተንሃም

አርሴናል ለተከታታይ 10 ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ቢዘልቅም ከሰንደርላድ ጋር አቻ ለመለያየት ተገዷል።

"ከቶተንሃም አንጻር አርሴናል የተሻለ ቡድን ቢሆንም አሠልጣኝ ቶማስ ፍራንክ መዘጋጀታቸው የሚጠበቅ ነው" ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታን ክሪስ ሱተን ተናግሯል።

"ቶተንሃም ተናቀቃኙን ለማቆም ጥረት ማድረጉ ባይቀርም መድፈኞቹ የማሸነፊያ መንገድ አያጡም" ብሏል።

ሱተን ይህንን ጨምሮ የአሥሩን የ12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ

ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎረስት

በርንሌይ ከ ቼልሲ

ቼልሲ የኮል ፓልመርን መልስ ቢጠብቅም ጆአኦ ፔድሮ እና ሊያም ዴላፕ በመመለሳቸው የፊት መስመሩ ጠንካራ ነው።

ከበርንሌይ የተደራጀ አቀራረብ አንጻር ይህ ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚደረግበት እገምታለሁ።

ጨዋታው አንድ አቻ እንደሚጠናቀቅ ቢሰማኝም ቼልሲ አንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1- 2

በርንመዝ ከ ዌስት ሃም

በርንመዝ ያፉትን ሁለት ጨዋታዎች ሲሸነፍ ዌስት ሃም ደግሞ አሸንፏል።

ይህ ጨዋታ በርንመዝ የሚያገግምበት ወይስ ዌስት ሃም የማሸነፍ ጉዞውን የሚያስቀጥለበት የሚለውን የሚታይበት ነው።

ጨዋታውን በርንመዝ እንደሚያሽንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 - 0

ብራይተን ከ ብሬንትፎርድ

ብሬንትፎርድ ሊወርዱ ይችላሉ ከተባሉ ቡድኖች አንዱ ቢሆንም ብዙዎችን ያስገረመ ውጤት እያስመዘገበ ነው።

ሆኖም ቡድኑ ወደ ብራይተን በማቅናት ለድል የሚበቃ አይመስለኝም።

ከሜዳ ውጭ ጥሩ ካለመሆናቸውም በላይ ብራይተን ደግሞ በሜዳው ጥሩ የሚባል ቡድን መሆኑን አስመስክሯል።

ግምት፡ 2 - 1

ፉልሃም ከ ሰንደርላንድ

ፉልሃም ጥሩ ተጫዋቾችን ቢይዝም ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች በአምስቱ ተሸንፏል።

ሰንደርላንድ በቡኩሉ የዘንድሮው አስደናቂ ቡድን መሆኑን ደጋግሞ አሳይቷል።

ፉልሃም በሜዳው የተሸነፈው በአርሴናል ብቻ ነው።

ቡድኑ ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ ጫና ውስጥ ይገኛል።

ግምት፡ 1 - 0

ሊቨርፑል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ሊቨርፑል ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች በሰባቱ ተሸንፏል። ባለፈው ዓመት ደግሞ አንፊልድ ላይ በፎረስት ተሸንፏል።

ፎረስት ከሜዳ ውጭ ያለው አቋም ጥሩ አይደለም።

ሊቨርፑል ተፎካካሪ ሆኖ ለመቀጠል ከወዲሁ ነጥብ መሰብሰብ ይገባዋል።

ግምት፡ 3 - 1

ዎልቭስ ከ ክሪስታል ፓላስ

ሮብ ኤድዋርድስ የሚድለስብራ ላፊነታቸውን በመልቀቅ ዎልቭስን በሊጉ ለማቆየት አዲሱን ሹመት ተቀብለዋል።

ፓላስ የተደራጀ ቡድን በመሆኑ ጠንካራ ጅማሮ እንደሚኖራቸው ይገመታል።

ዎልቨስ ባለቁ ሰዓቶች ውጤት ያጣባቸው ጨዋታዎች ቢኖሩም ፓላስ ግን ለዚያም የሚያበቃቸው አይመስለኝም።

ግምት፡ 0 - 2

ኒውካስል ከ ማንቸስተር ሲቲ

አሁን ባላቸው አቋም ከሆነ ሲቲ እንደሚያሸንፍ ብገምትም ስሜቴ የሚነግረኝ ሌላ ነው።

ኒውካስል ከሜዳው ውጭ ነጥብ እየጣለ ይገኛል።

ሲቲ ሊቨርፑልን አሸንፎ ከመምጣቱም በላይ ጥንካሬውን ለማሳየት የሚጠቀምበት ጨዋታ እንደሆነ ደጋፊዎቹ ይገምታሉ።

የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ብዙ መሥራት የሚጠበቅበት ሲሆን ይህንን ጨዋታ በአቻ ውጤት እንደሚያጠናቅቅ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

እሑድ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን

ሊድስ ከ አስቶን ቪላ

ሊድስ ከሰበሰባቸው 11 ነጥቦች ስምንቱን በሜዳው ያገኛቸው ናቸው።

ቡድኑ ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ቢመጣም ደጋፊዎቹ አሠልጣኝ ዳንኤል ፋርክ ላይ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች አሉ።

ሊድስ በቪላ ከተሸነፈ ነገሮች ሊበለሻሹ ይችላሉ።

ቪላ ካለፉት 10 ጨዋታዎች በስምንቱ አሸናፊ ሆኗል። በዚህ ጨዋታም የሚሸነፍ አይመስልም።

ግምት፡ 1 - 1

አርሴናል ከ ቶተንሃም

ቶተንሃም ከሜዳው ውጭ አራት ጨዋታዎችን አነሸንፎ በአንዱ አቻ በመለያየት ጥሩ ውቴት አስመዝገቧል።

ቡድኑ ጥሩ ውጤቶችን ማስመዝገብ ቢችልም የአጥቂ መስመሩ ላይ ጥያቄዎች አሉኝ።

ጨዋታው ጠንካራ ቢሆንም አርሴናል የተሻለ ዕድል እንዳለው ይሰመኛል።

መድፈኞቹ ጋብርኤል ማጋሌሽን በጉዳት ቢያጡም ክርስቲያን ሙስኬራ ቦታውን እንደሚሸፍን እገምታለሁ።

ግምት፡ 3 - 0

ሰኞ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኤቨርተን

ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፉት ጨዋታዎች መሻሻሎችን እያሳየ ይገኛል።

ዴቪድ ሞዬስ ወደ ቀድሞ ክለባቸው ሲመለሱ ጨዋታውን ከባድ ለማድረግ እንደሚሞክሩ ይጠበቃል።

ቡድኑ ጥሩ የአጥቂ መስመር ስለሌው ቀያዮቹ ላይ ጎል ለማስቆጠር ይቸገራሉ።

በብሪያን ምቡሞ እና በማቲያስ ኩኛ የሚመራው የዩናይትድ ጠንካራ የፊት መስመር ቡድኖችን መቅጣት ይችላል።

ግምት፡ 1 - 0