ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
“ልጄ ሁሉ ነገሬ ነበር” - ልጇ በፈረንሳይ ፖሊስ የተገደለባት እናት
ጠዋት እንደሚወዳት ገልጾ ስሟት የወጣው ታዳጊ ልጇ በፖሊስ የተገደለባት ፈረንሳዊት እናት ሐዘኗ መሪር መሆኑን ገልጻለች። ይህንንም አደባባይ ወጥታ የልጇን ግድያ በመቃወም ፍትሕ ጠይቃለች።
ግድያውን በመቃወም የፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስን ጨምሮ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው።ፖሊስ ከ600 በላይ ተቃዋሚዎችን አስሯል።