በሰሜን ኢትዮጵያ ተኩስ አቁሙ ተጥሶ ጦርነት ለምን መልሶ ተቀሰቀሰ?

በጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ትግራይ ውስጥ ተጀምሮ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች የተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ላለፉት አምስት ወራት በተደረገ የተኩስ አቁም ስምምነት ጋብ ብሎ ቆይቷል።

ነገር ግን መንግሥትና የህወሓት አመራሮች ጦርነቱን በውይይት ለመቋጨት ድርድር ይጀምራሉ ተብሎ በሚጠበቅበት በጊዜ ጦርነት እንደ አዲስ መልሶ አግርሽቷል። ለምን?