በዩክሬን የደራው የማህፀን ኪራይ ለእናቶች ምን ያህል ገንዘብ ያስገኛል?

ነፍሰ ጡር ሴት ግቢ ውስጥ ቆማ
የምስሉ መግለጫ, ካሪን
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 6 ደቂቃ

ካሪና የስድስት ወር ነፍሰጡር ናት። ነገር ግን በማህፀኗ ውስጥ ያለው ሕፃን የራሷ አይደለም።

የ22 ዓመቷ ከምሥራቅ ዩክሬን የመጣችው ካሪና የማህፀን አከራይ እና (ሰሮጌት) ናት። ከቻይናዊያን ጥንዶች የእንቁላል እና የዘር ፍሬ የተፈጠረ ሽል ተሸክማለች።

ካሪና ገና በ17 ዓመቷ ነበር በሩሲያ ወረራ የመጀመሪያ ምዕራፍ ወቅት ከተማዋ ባክሙት እጅግ በከባድ ጦርነት በመመታቷ መኖሪያ ቤቷ ወድሟል።

አብዛኛው የከተማዋ ክፍል ወደ ፍርስራሽና አመድ ሲለወጥ፣ እርሷ እና አጋሯ ወደ ኪየቭ ኑሯቸውን ቀየሩ፤ ነገር ግን ቋሚ ሥራ ማግኘት አልቻሉም።

ካሪና አንድ ቀን በሱቅ ሳለች፣ ለዳቦ እና ለአንድ ዓመት ዕድሜ ያላት ልጃቸው ዳያፐር ለመግዛት እንኳን በጣም ጥቂት ገንዘብ ሳይኖራት በክፍያ ማህፀኗን ለማከራየት ወሰነች።

ካሪና እንደምትለው ጦርነቱ ባይሆን ኖሮ ማህፀኗን አታከራይም ነበር። ጦርነቱ ሚሊዮኖች ሥራቸውን እና ንግዳቸውን እንዲያጡ አድርጓል፤ ይህም ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያመጣም ሲሆን የዩክሬን ጠቅላላ አገራዊ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል።

"መጀመሪያ በማህፀን ኪራይ እናት መሆን አበሳጭቶኝ፤ አሳዝኖኝም ነበር። አሁን ግን ተቀብዬዋለሁ" ትላለች ካሪና ታራሴንኮ።

አሁን ከኪየቭ ወጣ ብሎ በሚገኝ የማህፀን ኪራይ ክሊኒክ አማካይነት በተዘጋጀላት አፓርታማ ውስጥ ትኖራለች። ሴት ልጅም አርግዛለች።

ካሪና ማህፀንዋን አከራይታ ለምትሰጠው አገልግሎት 17 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ትገኛለች። ይህም ከዩክሬን አማካይ ደመወዝ ግምት ሁለት እጥፍ ያህል ነው። ነገር ግን ካሪና የዚህን ገንዘብ አብዛኛውን የምታገኘው ከወለደች በኋላ ነው።

ካሪና በመጀመሪያ 21 ሺህ ዶላር እንዲከፈላት ነበር ስምምነቷ፤ ነገር ግን ፀንሳቸው ከነበሩት መንታዎች አንዱ በመሞቱ በውሏ መሠረት ክፍያዋ ቀንሷል።

ምንም እንኳ በመጀመሪያ ጥርጣሪ የነበራት ቢሆንም ካሪና አሁን ሰውነቷ በፈቀደው ልክ ብዙ ሕፃናትን ማህፀኗን በማከራየት ለመውለድ እና ቤት ለመግዛት አቅዳለች።

ነገር ግን ይህ ውሳኔው በቅርቡ ከእጇ ሊወጣ ይችላል።

'ብላክ ፍራይደይ ሽያጭ' በሚል የተፃፈበት የማህቨን ኪራይ ማስታወቂያ

የፎቶው ባለመብት, BioTexCom

የምስሉ መግለጫ, የመብት ተሟጋቾች የማስታወቂያ ዘመቻዎችን በመተቸት ክሊኒኮች ሥነ ተዋልዶን ወደ ንግድ ቀይረዋል ሲሉ ይከሳሉ
Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ከጦርነቱ በፊት ዩክሬን ከአሜሪካ በመቀጠል የዓለም ሁለተኛ የማህፀን ኪራይ ማዕከል እንደሆነች በስፋት ይጠቀስ ነበር።

ምንም እንኳ ግጭቱ በማህፀን ኪራይ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ቢያሳድርም፣ በአሁኑ ጊዜ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት ደረጃ እንደተመለሰ ባለሙያዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ነገር ግን የዩክሬን ፓርላማ አሁን የማህፀን ኪራይ ገበያውን በጥብቅ የሚቆጣጠር እና ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑትን 95 በመቶ የሚሆኑትን የውጭ ወላጆች የሚከለክል ሕግ ለማውጣት እየተነጋገረ ነው።

የቀረበው ሕግ ልጅ መውለድን እንደ ንግድ ሸቀጥ እንዲቆጠር በማድረግ፤ በኑሮ ደካማ እና ተጋላጭ ሴቶችን መጠቀሚያ ያደረገውን ዘርፍ በጥብቅ መቆጣጠር ዓላማው ያደረገ ነው።

የሕጉ ረቂቅ በፓርላማው ውስጥ ሰፊ ድጋፍ አለው። ምንም እንኳ ማህፀንን በማከራየት የሚወለዱ ሕፃናት ከአጠቃላይ የወሊድ ምጣኔው አነስተኛ ቢሆንም፤ የሕጉ ደጋፊዎች በጦርነቱ ምክንያት የወሊድ መጠን በጣም በቀነሰበት በዚህ ጊዜ የዩክሬን ሴቶች ለውጭ ዜጎች ማህፀናቸውን አከራይተው ሕፃናት መውለድ አይገባቸውም ይላሉ።

"በጦርነቱ ምክንያት ተስፋ የቆረጡ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ነው። ክሊኒኮች ደግሞ ይህንን ዕድል ይጠቀሙበታል፤ ምክንያቱም ምዕራባውያን ጥንዶች ሕፃናትን በአነስተኛ ዋጋ ሊገዙ ይፈልጋሉ" ትላለች የሴቶች መብት ተሟጋቿ ማሪያ ዲሚትሪየቫ።

ማሪያ ከሥነ ምግባር አንፃር ሁሉንም ዓይነት የማህፀን ኪራይ የምትቃወም እና የቀረበው ሕግ በቂ አይደለም የምትል ናት። በተጨማሪም ይህ አሠራር በዩክሬን በሙሉ ሊከለከል ይገባል ብላ ታምናለች።

የማህፀን ኪራይ ክሊኒኮችን ደሃ የሆኑ ሴቶችን ዒላማ በማድረግ ትከሳለች፤ ለዚህ በምሳሌነት በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን ትጠቅሳለች።

በዚህ ዓመት ጥር ወር በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የተሠራ እና በአንድ ክሊኒክ የማህፀን አከራይ ሴቶችን ለመመልመል የተለጠፈ ማስታወቂያ፣ አንዲት ሴት ቤቷን ለማሞቅ የሚሆን እንጨት ወይም ለልጆቿ ልብስ ለመግዛት ስትጨነቅ ያሳያል። ይህም በጦርነቱ በርካታ ዩክሬናውያን ያጋጠማቸውን መከራ በማሳት ለመወትወት የተዘጋጀ ነው።

በ2021 በዩክሬን ትልቁ የማህፀን ኪራይ ክሊኒክ የሆነው ባዮ ትክስኮም የሥነ ተዋልዶ ማዕከል በማህፀን ኪራይ ላይ ቅናሽ ማውጣቱን የሚገልጽ የማስታወቂያ ዘመቻ አካሂዶ ነበር።

ቢቢሲ እነዚህ ማስታወቂያዎች የሰዎችን ክብር ሊያወርዱ እንደሚችሉ ሲጠይቅ ማዕከሉ የማህፀን አከራይ ሴቶችን ትኩረት በመሳብ ውጤታማ ነው ብሎ ይከላከላል።

ጥንዶቹ ባለፈው ዓመት ባዮ ቴክስኮምን ተጠቅመው ከ87 ሺህ ዶላር በላይ ከፍለዋል። ይህም በአሜሪካ ሊከፍሉት ከሚችሉት በግማሽ ያነሰ ነው። ጥንዶቹ ከባዮ ቴክስኮም ጋር የነበራቸው ልምድ ጥሩ ነበር።

ቴክኖሎጂን በመጠቀም በለንደን ከማህፀን ውጪ ጽንስ ፈጠሩ፤ ሽሉ ወደ ኪየቭ ተላከ እና በክሊኒኩ ማቀዝቀዣ ውስጥ ተቀመጠ።

ጥንዶቹ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ልጃቸው ሲወለድ ለመገኘት ወደ ኪየቭ አቅንተዋል።

ግን የዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት ሕጋዊ ሰነዶችን ለማጠናቀቅ እና ለልጃቸው ፓስፖርት ለማውጣት በወሰደው ጊዜ ምክንያት ልጃቸው የመጀመሪያውን ሦስት ወራት በሩሲያ ጥቃት ምክንያት በኪየቭ የቦንብ መጠለያ በመግባት እና በመውጣት አሳልፏል።

ሕፃን ልጅን በእቅፏ የያዘች ሴት
የምስሉ መግለጫ, ዌይ ወላጆቹ ስላልወሰዱት በመንግሥት ማሳደጊያ ማዕከል ውስጥ ይገኛል

የተረሱት ልጆች

ልጆች ከተወለዱ በኋላ ወላጆቻቸው ሀሳባቸውን በመቀየራቸው ያለወላጅ የተተዉ ሕፃናትም አሉ።

በዩክሬን ሕግ መሠረት ማህፀን በመከራየት ወላጅ የሆኑ ጥንዶች ሕፃናቱ ከተወለዱ በኋላ ሕጋዊ ኃላፊነት አለባቸው፤ እናም በማንኛውም ምክንያት ሕፃናቱን መተው በሕግ የተከለከለ ነው።

ነገር ግን በተግባር ከራስ ድንበር አልፎ ሕግን ማስከበር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

አሁን አምስት ዓመት የሆነው ዌይ በ2021 ያለ ዕድሜው ሲወለድ ከባድ የአንጎል ጉዳት ተደርሶበታል። ማህፀኗን አከራይታ የወለደችው እናቱ በባዮ ቴክስኮም በኩል ነው።

አሁን በኪየቭ ያለ የመንግሥት የአካል ጉዳተኛ ልጆች መኖሪያ ውስጥ ይገኛል።

ቢቢሲ ማዕከሉን በጎብኘበት ጊዜ ዌይ ከጓደኞቹ ጋር ሙዝ እየበላ ነበር፤ ሁልጊዜ ለምግብ አብረው ይቀመጣሉ።

ዌይ በራሱ መቀመጥ፣ ሰውነቱን መቆጣጠር ወይም በትክክል ማየት አይችልም። እና ሕይወቱን ሙሉ የ24 ሰዓት እንክብካቤ ይፈልጋል።

የጤና ሁኔታ ከተረዱ በኋላ ከደቡብ ምሥራቅ እስያ የመጡ ወላጆቹ ዌይን ለመውሰድ አልመረጡም። ተደብቀው ተመለሱ። መንግሥት እና ባዮ ቴክስኮም እነዚህን ወላጆች ለማግኘት ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራም አልተሳካም።

ዌይን ለማርገዝ የማህፀኗን ያከራየችው እናቱም አልፈለገችም። በዩክሬን ሕግ መሠረት በልጁ ላይ ማንኛውም ሕጋዊ ግዴታ የለባትም።

ከዩክሬን የጤና ሚኒስቴር ባልደረባ የሆነችው ቫሌሪያ ሶሩቻን ሕጉ እንዲቀየር ከሚገፋፉት መካከል ናት። በማህፀን ኪራይ የሚወለዱት "በርካታ" ሕፃናት አይፈለጉም ትላለች፤ መንግሥት ግን ትክክለኛውን አሃዝ አይጠቅስም።

በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ የማህፀን ኪራይን አትቃወምም። ነገር ግን በዩክሬን ያለውን የአስተዳደር ክፍተት በመተቸት እና ለውጭ አገር ዜጎች መከልከልን ትደግፋለች።

የባዮ ቴክስኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ ቶቺሎቭስኪ የተፈጠረውን ክፍተት "አሳዛኝ" ብለው በመግለፅ፤ "ወላጆች ሕፃናቱን ሲተዉ እኛም በከፊል ኃላፊነት ይሰማናል" ይላሉ።

ሕፃናት ሲተዉ ወይንም ሲጣሉ ክሊኒኮች በመንግሥት ለማሳደግ የሚያወጣው ወጪ ለመጋራት ሕጋዊ ግዴታ የለባቸው። እነዚህ ማሳደጊያዎች የመንግሥት እና የግል ገንዘብ ያጣምሩ ድጋፎችን የሚቀበሉ ሲሆን፤ ባዮ ቴክስኮም ለዌይ አንዳችም የገንዘብ ድጋፍ አልሰጠም።

እንደ ዌይ ያሉ ከባድ የአካል ጉዳት ያለባቸው ልጆች የጉዲፈቻ ቤተሰቦችን ማግኘት ያዳግታቸዋል። 15 ቤተሰቦች የዌይን መረጃ አይተዋል። ነገር ግን አንዳቸውም ሕፃኑን ለማሳደግ ፍላጎት አላሳዩም።

ጥንዶች ሕፃን ልጅ ታቅፈው
የምስሉ መግለጫ, ሂማትራጂ እና ራጂቪር ባጅዋ የማህፀን ኪራይ ይሆናል ብለ ንበፍፁም ያላሰብነውን ቤሰብ ሰጥቶናል ይላሉ

"ወላጅ እንድንሆን አድርገውናል"

እንዲህም ሆኖ የንግድ የማህፀን ኪራይ ለሁሉም ወገኖች ጥቅም ሊያመጣ ይችላል ብለው የሚከራከሩ አሉ።

የለንደን ነዋሪ የሆኑት ሂማትራጅ እና ራጅቪር ባጅዋ ለአምስት ዓመት ልጅ ለመውለድ ሞክረው አልተሳካላቸውም። ሁለት ጊዜ ከማህፀን ውጪ በቴክኖሎጂ መፀነስን (የአይቪኤፍ) ጨምሮ ልጅን ለማግኘት ሞክረዋል። ከዚያም ማህፀን ለመከራየት ወሰኑ።

38 ዓመቷ የሆነችው ራጅቪር ልጅ መፀነስን አስቸጋሪ ሚያደርግ የጤና እክል አለባት።

ጥንዶቹ የዩናይትድ ኪንግደም ሕግ የገንዘብ ልውውጥን በመከልከሉ ከሕግ አፈንግጠው ለመጓዝ መርጠዋል። የማህፀን ኪራይ በዩናይትድ ኪንግደም ብዙ ጊዜ በጓደኞች፣ በቤተሰብ ወይም በሌላ የማህፀን ለጋሾችን በሚያገናኙ ለትርፍ በማይሠሩ ድርጅቶች በኩል ይፋዊ ባልሆነ መልኩ ይካሄዳል።

በዩናይትድ ኪንግደም ሕግ መሠረት የማህፀን አከራይ የሆነችው እናት የወላጅነት ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ ለሕፃኑ ሕጋዊ ኃላፊነት አለባት። ይህም ኃላፊነቱን ወደ እውነተኛ ወላጆች ማስተላለፍ ማለት ነው።

ሂማትራጅ እና ራጅቪር በመጀመሪያ ጊዜ በሕፃኑ ላይ ማንኛውም ሕጋዊ መብት እንደማይኖራቸው ሲያውቁ አስጨንቋቸው ነበር። ምንም እንኳ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም የማህፀን አከራይ እናቶች ሀሳባቸውን በመቀየር ሕፃናትን ለመስጠት አሻፈረኝ ያሉባቸው አጋጣሚዎች አሉ።

ጥንዶቹ በዩክሬን ውስጥ የማህፀን ኪራይ እንዴት እንደሚሠራ ሲያቁ በጣም ደስተኞች ነበሩ። ለዚህ አገልግሎት የሚከፈለው ገንዘብ ደግሞ ሌላ ምክንያት ነበር።

ካሪና የእግርዝና ክተትል ስደታርግ
የምስሉ መግለጫ, ካሪና የእግርዝና ክተትል ስደታርግ

ጥንዶቹ ባለፈው ዓመት ባዮ ቴክስኮምን ተጠቅመው ከ87 ሺህ ዶላር በላይ ከፍለዋል። ይህም በአሜሪካ ሊከፍሉት ከሚችሉት በግማሽ ያነሰ ነው። ጥንዶቹ ከባዮ ቴክስኮም ጋር የነበራቸው ልምድ ጥሩ ነበር።

ቴክኖሎጂን በመጠቀም በለንደን ከማህፀን ውጪ ጽንስ ፈጠሩ፤ ሽሉ ወደ ኪየቭ ተላከ እና በክሊኒኩ ማቀዝቀዣ ውስጥ ተቀመጠ።

ጥንዶቹ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ልጃቸው ሲወለድ ለመገኘት ወደ ኪየቭ አቅንተዋል።

ግን የዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት ሕጋዊ ሰነዶችን ለማጠናቀቅ እና ለልጃቸው ፓስፖርት ለማውጣት በወሰደው ጊዜ ምክንያት ልጃቸው የመጀመሪያውን ሦስት ወራት በሩሲያ ጥቃት ምክንያት በኪየቭ የቦንብ መጠለያ በመግባት እና በመውጣት አሳልፏል።

ባለፈው ዓመት ነሐሴ መጨረሻ ከልጃቸው ጋር ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የተመለሱ ሲሆን፣ በመጪው ሰኔ የልጃቸውን የመጀመሪያ ዓመት የልደት በዓል ያከብራሉ።

ጥንዶቹ አዲሱን የዩክሬንን የሕግ ረቂቅ ይቃወማሉ። እነሱ የተጠቀሙት የማህፀን አከራይ ኤጀንሲ "ደስታ እና ሐሴት" እንዳመጣላቸው ይናገራሉ።

"እኛ ይሆናል ብለን ያላሰብነውን ነገር ሰጥተውናል፤ ቤተሰብ አድርገውናል" ይላል የ37 ዓመቱ ሂማትራጅ።

ጥንዶቹ ከማህፀን አከራያቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን፤ ብዝበዛ ተደርጎባታል ብለው አያምኑም።

"ግልፅ ነው ሁልጊዜ የእነሱ ምርጫ ነው። ለእነሱም የመኖሪያ መንገድ ነው። ይህ እነርሱን የሚረዳቸው ከሆነ፣ በመጨረሻ ሁሉም በውጤቱ ደስ ይለዋል ብዬ እምናለሁ" ይላል ባል።

"ማንም እያስገደደን አይደለም"

ካሪና ገንዘብ ተከፍሎ የሚደረገው የማህፀን ኪራይ ሴቶችን መበዝበዣ መንገድ ነው የሚለውን ሃሳብ ውድቅ ታደርጋለች።

"ማንም እያስገደደን አይደለም። ይህ ሰውነቴ ነው፤ ውሳኔዬም የእኔ ነው... ለእነሱ ለሰጠሁት ደስታ ሽልማቴን እቀበላለሁ።"

ካሪና የሕጉን ማሻሻያ ትቃወማለች፤ ይህም ቤት ለመግዛት የያዘችውን ህልም "ሙሉ ለሙሉ ያፈርሳል" ትላለች።

ወደ ሆዷ እየተመለከተች "ይህች ልጅ የእኔ እንዳልሆነች አውቃለሁ። ነገር ግን እወዳታለሁ። ከእሷ ጋር እነጋገራለሁ። ስትታመም፣ ወላጆቿ እየጠበቋት እንደሆነ እነግራታለሁ።

"ብቻ ጥሩ ሕይወት እንዲኖራት እመኛለሁ" ትላለች።