ጥቁር አሜሪካዊቷን የገደለው የፖሊስ አባል የ33 ወራት እስራት ተፈረደበት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አንድ የቀድሞ የኬንታኪ ፖሊስ አባል ብሬና ታይለር የተባለች ጥቁር ሴትን ለሞት ከዳረገው የፖሊስ ዘመቻ ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ የ33 ወራት እስራት ተፈርዶበታል።
ባለፈው ዓመት የፌደራል ዳኞች ብሬት ሃንኪሰን ከልክ ያለፈ ኃይል በመጠቀም የታይለርን መብት በመጣስ ጥፋተኛ ብሎታል።
የፖሊስ አባሉ ለተከሰሰበት ወንጀል ከፍተኛው ቅጣት የእድሜ ልክ እስራት ነው።
ቅጣቱ የተላለፈው የትራምፕ አስተዳደር ዳኛው ለሃንኪሰን የአንድ ቀን ቅጣት እንዲሰጠው ከጠየቀ ከቀናት በኋላ ነው።
ይህ የትራምፕ አስተዳደር አቋም የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለጉዳዩ ካላቸው አቋም ጋር በእጅጉ ይቃረናል ።
ከተፈጠረው ድንገተኛ የፖሊስ ዘመቻ ጋር በተያያዘ በቀጥታ የተከሰሰው እና የተፈረደበት ብቸኛው መኮንን ሃንኪሰን ነው።
ሌላዋ የቀድሞ ኦፊሰር ኬሊ ጉድሌት ከባልደረቧ ጋር በማሴር ለቴይለር ቤት የፍተሻ ማዘዣ ለማግኘት እና ከሞተች በኋላ ድርጊታቸውን ለመደበቅ የእምነት ክህደት ቃል በማጭበርበር ጥፋተኛ መሆኗን ያመነች ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት ቅጣት ይጠብቃታል።
የታይለር እናት ታሚካ ፓልመር እና የቤተሰቡ ጠበቆች ከሰኞ የፍርድ ውሳኔ በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
"ዳኛዋ የምትችለውን ሁሉ አድርጋለች ብዬ አስባለሁ" ያሉት ወይዘሮ ፓልመር ፤ ነገር ግን ትንሽ ቅጣት እንዲጣልበት የተከራከሩትን የፌደራል አቃቤ ህጎችን ተችተዋል።
ወረራ በተፈፀመበት ምሽት ከእርሷ ጋር በአፓርታማ ውስጥ የነበረው የታይለር ፍቅረኛ ኬኔት ዎከር፣ "ለተገኘው ትንሽ ፍትህ አመስጋኝ ነኝ" ብሏል።
ታይለር እ.ኤ.አ. በ 2020 መሞቷን እና የጆርጅ ፍሎይድን የፖሊስ ግድያ ተከትሎ 'የብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ፊት ሆናለች።
እሷ የተገደለችው ሲቪል ልብስ የለበሱ መኮንኖች በቤቷ ውስጥ እሷ እና ፍቅረኛዋ ዎከር በተኙበት ቤታቸውን ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው።
ባለሥልጣናቱ የታይለር የቀድሞ የወንድ ጓደኛ አደንዛዥ ዕፅን ለመደበቅ ቤቷን እንደሚጠቀም ያምኑ ነበር።
ፖሊሶች በሩን ሲያንኳኩ ዎከር አንድ ጥይት ተኩሶ ጆን ማቲንግሊ የተባለውን አንዱን እግሩ ላይ መታው። ዎከር እንደተናገረው መኮንኖቹ ፖሊስ መሆናቸውን እንዳላወቀ እና እንደ ቦታቸውን ሰብረው የገቡ ሌቦች እንደሆኑ አስቧል።
ሦስቱ መኮንኖች ተኩስ በመመለስ 32 ጥይቶችን ወደ አፓርታማው ተኩሰዋል።
ሃንኪንሰን 10 ጊዜ ወደ አፓርታማው የተኮሰ ሲሆን፣ በችሎቱ ወቅት ባልደረቦቹን ለመጠበቅ ሲል እንደሆነ ተናግሯል።
የትኛውም የሃንኪሰን ጥይት ማንንም አልመታም፣ ነገር ግን አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት፣ የአምስት ዓመት ሕጻን እና አንድ ወንድ ተኝተው ወደነበሩበት ጎረቤት ቤት ገብተዋል።
ዐቃቤ ሕግ ሃንኪሰን በግዴለሽነት እርምጃ ወስዷል እና "ከዋና ዋና ገዳይ ኃይል ሕጎች ውስጥ አንዱን ጥሷል፤ የሚተኩሱበትን ሰው ማየት ካልቻሉ ቃታውን መሳብ አይችሉም" ብለዋል።
ከፍርድ ቤቱ ውጭ፣ ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተቃዋሚዎች የታይለርን ስም እየጠሩ ጎዳናዎችን ዘግተዋል። የቴይለር አክስት ቢያንካ ኦስቲንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በፖሊስ ተይዘዋል ።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
በዚህ ጉዳይ ላይ የፍትህ ሚኒስቴር እንዴት ተሳተፈ?
እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2024 መጀመሪያ ላይ ሃንኪሰን በአንድ የዜጎች መብት ጥሰት ተከሷል።
የባይደን ተሿሚ ጄኔራል ሜሪክ ጋርላንድ "የእሱ ገዳይ ኃይል መጠቀሙ ሕገ ወጥ ነበር እና ታይለርን ለጉዳት ዳርጓል" ሲሉ በመግለጫ ተናግረዋል።
ሃንኪንሰን ከተፈረደበት ከቀናት በኋላ ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ ምርጫ አሸንፈዋል።
ይህ የፖለቲካ ለውጥ ማለት የቅጣት አስተያየት የሚመጣው ክሱን ከመሰረተው የባይደን አስተዳደር ሳይሆን በትራምፕ ከሚመራው የፍትህ ክፍል ነው።
ባለፈው ሳምንት ሃንኪሰን አንድ ቀን በእስር ቤት እንዲያገለግል የቀረበው ምክረ ሃሳብ የታይለር ቤተሰብን ጨምሮ አንዳንዶቹን አስደንግጧል።
"በሕግ እኩል ፍትህን የሚያምን አሜሪካዊ ሁሉ ሊቆጣ ይገባል" ሲሉ የቤተሰቡ ጠበቆች ተናግረዋል። "አንድ ቀን ብቻ በእስር ቤት እንዲቆዩ ምክረ ሃሳብ ማቅረብ ነጭ የፖሊስ መኮንኖች የጥቁር አሜሪካውያንን የዜጎች መብት ያለምንም ተጠያቂነት ሊጣሱ እንደሚችሉ የማያሻማ መልዕክት ያስተላልፋል።"
የፍትህ ሚኒስቴሩ የቅጣት ውሳኔውን ባቀረበበት ወቅት ሃኪሰን ገዳይ በሆነው ወረራ ወቅት "የማሰር ትዕዛዝ በመፈጸም" ውስጥ የተሳተፈ ቢሆንም ታይለር ላይ አልተኩስም "[ስለሆነም] ለሞቷ ተጠያቂ አይደለም" ሲል ተከራክሯል።
በተጨማሪም የፍትህ ሚኒስቴሩ ተጨማሪ የእስር ጊዜ "በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ኢ ፍትሃዊ ይሆናል" ብሏል።
በተለምዶ፣ የቅጣት አስተያየቶች በጉዳዩ ላይ በተሳተፉ ጠበቆች ወይም የቅጣት አወሳሰን ጥያቄዎችን በሚመለከቱ የፍትህ ሚኒስቴር ሠራተኞች ይፈርማሉ።
በዚህ ጉዳይ ላይ የሲቪል መብቶች ዲፓርትመንትን እንዲመሩ በትራምፕ የተሾሙት ሃርሜት ድሂሎን የቅጣት አስተያየቱ ላይ ፈርመዋል።
የትራምፕ ፍትህ ክፍል ምን ለውጦች አድርጓል?
ወደ ዋይት ሐውስ ከተመለሱ በኋላ ትራምፕ የባይደን የስልጣን ዘመን ፖሊሲዎችን በተለይም በፍትህ ክፍል ውስጥ ቅድሚያ መስጠት ለውጦችን አድርገዋል።
በግንቦት ወር የፍትህ ዲፓርትመንት የታይለርን ጨምሮ በፖሊስ አባላት የተፈጸሙ ግድያዎችን ላይየተነሳውን ውዝግብ ተከትሎ በሉዊስቪል እና በሚኒያፖሊስ የፖሊስ መምሪያዎች ላይ የቀረቡትን ክሶች ውድቅ የማድረግ ሂደት ጀመረ።
እንደ ሜምፊስ እና ፎኒክስ ባሉ ሌሎች ከተሞች የፖሊስ ህገ-መንግስታዊ ጥሰት ላይ የተደረገው ምርመራም አብቅቷል።
በባይደን የስልጣን ዘመን፣ የፍትህ ክፍል በ12 የክልል እና የአካባቢ ህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ላይ የሲቪል ምርመራዎችን ከፍቷል።
ከእነዚህ ውስጥ በአራቱ ውስጥ በሉዊስቪል ፣ ሚኒያፖሊስ ፣ ፊኒክስ እና በሌክሲንግተን ፣ ሚሲሲፒ - መምሪያው ስልታዊ የፖሊስ ጥፋቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን አውጥቷል።















