ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
“በብስክሌት ውድድር በአፍሪካ አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ እፈልጋለሁ” ፡ ኪያ ሮጎሮ
ከዩኒቨርስቲ ትምህርት ብስክሌትን የመረጠው ኢትዮጵያዊ ብስክሌተኛ በሩዋንዳ እየተካሄደ ባለው የብስክሌት ውድድር እየተሳተፈ ነው። በውድድሩ የተሻለ ውጤት አስመዝግቦ በትልልቅ የብስክሌት ክለቦች ዐይን ውስጥ መግባት ይፈልጋል። በተወዳጁ ቱር ደ ፍራንስ መሳተፍ ደግሞ የመጨረሻ ግቡ ነው።