የዝውውር ጭምጭምታዎች፡ ሳንቾ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል፤ ጉማሬሽ ፈላጊው በዝቷል

እንግሊዛዊውን የአል-ኢትፋቅ አማካይ ጆርዳን ሄንደርሰንን ለማስፈረም አያክስ ፍላጎት እንዳለው ታውቋል። የ33 ዓመቱን ተጫዋች ለማስፈረም ከፕሪሚየር ሊግ እና ከቡንደስ ሊጋ ቡድኖች ፉክክር ይገጥመዋል ሲል ኢኤስፒኤን ዘግቧል።

የማንቸስተር ዩናይትዱ ጄደን ሳንቾ በውሰት ቦርሲያ ዶርትሙንድን ሊቀላለቅ ከጫፍ ደርሷል። የጀርመኑ ክለብ ተጫዋቹን የመግዛት አቅም ስለሌለው በክረምት ወደ ማንቸስተር እንደሚመለስ የዘገበው ሚረር ነው።

ስካይ ስፖርት ቶተንሃም ሊያስፈርመው ያቀደውን ራዱ ድራጉሲንን ለማስፈረም ባየር ሙኒክ እንቅስቃሴ ጀምሯል። የሚፈልገውን ክለብ የመመረጥ ኃላፊነት አሁን በ21 ዓመቱ የጄኖዋ እና ሮማኒያ ተከላካይ ላይ ወድቋል ሲል ዘግቧል።

የ25 ዓመቱ ፈረንሳዊ አጥቂ ክሊያን ምባፔ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን ለእሱ ምርጥ ክለብ በመሆኑ ከፈረንሳይ ሻምፒዮኖቹ ጋር እንዲቆይ እንደሚፈልጉ የክለቡ ፕሬዝዳንት ናስር አል-ኼላፊ መናገራቸውን አአርኤምሲ ስፖርት ዘግቧል።

በተመሳሳይ ፒኤስጂ የ28 ዓመቱን ጀርመናዊ አማካይ ጆሹዋ ኪምሚችን ከባየር ሙኒክ ለማስፈረም እየሰራ መሆኑን ስካይ ጀርመን አስነብቧል።

ኒውካስል ዩናይትድ የ26 ዓመቱ ብራዚላዊውን አማካይ ብሩኖ ጉመሬሽን ለማስረፈም ፒኤስጂ የሚያቀርበውን ማንኛውንም ጥያቄ ውድቅ እንደሚያደርግ ዘ አይ ዘግቧል።

ፉልሃም ባለፉት ሳምንታት በቼልሲ፣ ኤሲ ሚላን እና ባርሴሎና ክትትል ሲደረግበት የነበረውን የ25 ዓመቱ የኤዜድ አልካማሩን አጥቂ ቫንጄሊስ ፓቭሊዲስ እየተከታተለ እንደሚገኝ ኢቭኒንግ ስታንዳርድ ጠቁሟል።

የሌስተር ሲቲው አለቃ ኤንዞ ማሬስካ የ28 ዓመቱን ጣሊያናዊ አማካይ ስቴፋኖ ሴንሲን ከኢንተር ሚላን ለማዘዋወር ጥረት በማድርግ ላይ መሆናቸውን ስካይ ስፖርት ኢታሊያ ዘግቧል።

ባርሴሎና በውሰት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ካስፈረመው በአጥቂው ጆአዎ ፊሊክስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ዙሪያ ንግግር ማቆሙ ተሰምቷል። ተጫዋቹ እያሳየ በሚገኘው የብቃት መውረድ ምክንያት የስፔኑ ክለብ በ24 ዓመቱ ፖርቹጋላዊው ተጫዋጭ ላይ ጥርጣሬ አድሮበታል ያለው ስፖርት ነው።

ቶተንሃም የሚድልስቦሮውን አማካይ ሃይደን ሃክኒን ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር ለመቀላቀል ተዘጋጅተዋል። የ21 ዓመቱ ተጫዋች ማንቸስተር ሲቲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል እየተከታተሉት ያስነበበው ኢቭኒንግ ስታንዳርድ ነው።