የዓለም ጤና ድርጅት በመጪው ክረምት በዩክሬን የሚሊዮኖች ህይወት ስጋት ላይ ይወድቃል አለ

የዓለም ጤና ድርጀት በመጪው የክረምት ወቅት በዩክሬን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ ይወድቃል ሲል አስታውቋል።

በዩክሬን ከሚገኙ የሃይል መሰረተ ልማቶች ግማሽ የሚሆነው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ ሲሆኑ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር መቆራረጣቸው የዓለም ጤና ድርጀት የአውሮፓ ሃላፊ ዶክተር ሃንስ ሄንሪ ክሉግ ገልጸዋል።

በመጪው ክረምት ሳቢያ በአንዳንድ የዩክሬን አከባቢዎች የቅዝቃዜው መጠን ከ ‘ኔጌቲቭ’ 20 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች እንደሚወርድ ትንበያ ተሰጥቷል።

ሩሲያ ዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተችበት ጊዜ ጀምሮ 703 የጤና ተቋማት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን የዓለም ጤና ድርጅት ያሰባሰበው መረጃ አመላክቷል።

ባለፈው ሳምንት ሩሲያ የኃይል መሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ሰላማዊ ዜጎች የሚጠቀሙባቸው ህንጻዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን ድብደባዎቹ በጦርነቱ ከተመዘገቡት ከባድ ጥቃቶች መካከል ተመድበዋል።

በጦርነት አውድማዎች ስኬት የራቃት ሩሲያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መስል ጥቃቶችን እየሰነዘረች ሲሆን የክርምቱን መቃረብ ተከትሎ ጥቃቶቹ እያስከተሉ ያሉት ውጤት መታየት ጀምሯል።

“በቀላሉ ለመግለጽ መጪው ክረምት የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ይሆናል” ሲሉ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪዮቭ መግለጫ የሰጡት ዶክትር ክሉግ ተናግረዋል።

የዩክሬን የጤና ስርዓት “በጦርነት ውስጥ እስካሁን የጨለማ ጊዜያትን እየተጋፈጠ ነው” ያሉት ሃላፊው ጦርነቱን ማቆም ከሁሉም የተሻለው መፍትሄ ነው ሲሉ አክለዋል።

በጦርንቱ ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሆስፒታሎች እና ሌሎች የጤና ተቋማት ባጋጠማቸው የነዳጅ፣ ውሃ እና ኤሌክትሪክ እጥረት በሙሉ አቅማቸው አግልግሎት መስጠት እንደተሳናቸውም ሃላፊው ጠቁመዋል።

የወሊድ ክፍሎች የጨቅላ ህጻናት ማቆያ፤ የደም ባንክ ማዝቀዣ እና የጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍሎች ‘ቬንትሌተር’ ይፈልጋሉ ያሉት ዶክተር ክሉግ እነዚህ ሁሉ የኤሌክትክትሪክ አቅርቦት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ሶሰት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከጦርነት በመሸሽ ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ተመድ አስታውቋል።

ሰዎች በቅርቡ የኤች አይ ቪ መድሃኒት እንደሚያልቅባቸው ጠቁመው ነገሩ “እጅግ አሳስቦኛል” ብለዋል።

የዶንስቴክ ግዛት አብዛኛው ክፍል በሩሲያ ቁጥጥር ሰር የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ወደ ዩክሬን በተመለሱም ይሁን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባሉ ስፍራዎች የሰብዓዊ እርዳታ መስመር እንዲከፈት ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ ስርጭት እንደ አዲስ ማገርሸት ስጋትን ጭሯል።

ሃላፊው “ማጠናከሪያውን ትተነው ባለው ዝቅተኛ የክትባት ምጣኔ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን ኮቪድን ለመቋቋም ያላቸው የበሽታ መከላከል አቅም ዝቅ ያለ ነው ወይም ሙሉ በሙሉ የለም” ብለዋል̏

ይህ የተመድ ማሳሰቢያ የተሰማው በዩክሬን በረዶ እየጣለ ባለበት እና ከፍተኛ ቅዝቃዜ ባለበት ወቅት ነው።

በኪዬቭ የእግረኛ መንገዶች፣ የመጫወቻ ስፍራዎችና የመንግድ ላይ መቀመጫዎች በበሮዶ የተሸፈነ ሲሆን በከተማዋ ጎደናዎች ላይ የሚታዩት ጥቂት ሰዎች ናቸው።

በረዶ እየታየ ቢሆነም ክረምቱ ግን ገና አልገባም። የክረምቱን መግባት ተከትሎ በሀገሪቱ ቅዝቃዜው አሁን ካለውም እንደሚጨምር ይጠቃል።

ዛፖሪዚሃዚሃ የተባለው እና የዩክሬንን የኤሌክትሪክ አቅርቦት 25 በመቶ የሚሸፍነው የኒውክሌር ማመንጫ ሃይል ማመንጨት አቁሟል።