የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የድምጽ ቆጠራ አሁናዊ ውጤቶች

ማክሰኞ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ኬንያውያን ለምርጫ ወጥተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ለፕሬዝዳንትነት አራት ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን፣ መራጮች ለፕሬዝዳንት፣ ለግዛት አስተዳዳሪዎች፣ ለሕግ አውጪዎች፣ ለብሔራዊ እና ለግዛት ምክር ቤቶች አባላት ድምጽ ሰጥተዋል።
ቢቢሲ የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጊዜያዊ የድምጽ ቆጠራ ውጤትን የሚያመለክተውን አሃዝ የሚወስደው ምርጫውን ከሚያስፈጽመው ኮሚሽን ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ ነው።
ኮሚሽኑ የማጣራት ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ እና በዚህ ገጽ ላይ የሚገኘውን አሃዝ ወቅታዊ በማድረግ በኩል መዘግየት ሊኖር ይችላል። በኬንያ የምርጫ ሕግ መሠረት የፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን የመጨረሻው ውጤት የሚያሳውቀው የምርጫ ኮሚሽኑ ነው።
*የተሻሻለ አሁናዊ ውጤቶችን ለመመልከት ገጹ እንደገና ማስጀመርን አይዘንጉ።














