ኮሮናቫይረስ ፡ ዱባይ ውስጥ ሥራ አጥተው የተቸገሩ ወገኖቿን የምትመግበው ኬንያዊት

ዋንጌቺ ዋሩይሬ

የፎቶው ባለመብት, Courtesy

ኬንያዊቷ በዩናይትድ አረብ ኤምሬተስ በኮሮናቫይረስ ምከንያት ሥራ ፈትተው ለተቀመጡ ኬንያውያን ምግብ እየሰራች በነጻ እንደምትመግብ ተሰምቷል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት ዋንጌቺ ዋሩይሬ ለዱባይ ታክሲ ሹፌር ነበረች።

ዋሩይሬ "የተወሰነ ወራት በዝቅተኛ ክፍያ ከሰራሁ በኋላ በዋናው አየር መንገድ የሚገኘው አንደኛው ተርሚናል በወረርሽኙ ምክንያት በመዘጋቱ የተነሳ በጥቅምት ወር ላይ ሥራ ፈታሁ" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።

የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ዋሩይሬ፣ በርካቶች በወረርሽኙ ምክንያት ስራ አጥተው መቸገራቸው ስትመለከት፣ ቢያንስ የሚበሉትን በነጻ በመስጠት ጭንቀታቸውን ለማቃለል ማሰቧን ገልጻለች።

የዋሩይሬ ባለቤት ሥራ አለመፍታቱን ገልጻ እርሱ በሚገዛላት አስቤዛ፣ ሥራ ፈትተው ቤታቸው ለተቀመጡ የአገሯ ልጆች ምግብ በማዘጋጀት በፌስ ቡክ ገጿ ላይ በማጋራት አቅራቢያዋ የሚኖሩ መጥተው እንዲወስዱ መጠየቅ ጀመረች።

ዋረያሬ በሳምንት ሁለቴ ከ 20 እስከ 25 ሰው እንደምትመግብ ትገልጻለች።

ከዚህ ቀደም በመንግሥት ብርቱ አሽከርካሪነቷ ታይቶ 'ምርጥ የዱባይ ታክሲ አሽከርካሪ' ተብላ ተሸልማ ነበር።

ዋንጌቺ ዋሩይሬ

የፎቶው ባለመብት, Courtesy