ዶናልድ ትራምፕ ለማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን ከለላ አነሱ

የፎቶው ባለመብት, AFP
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን የተወሰነ ሕጋዊ ከለላ የሚያነሳ ፊርማቸውን አኖሩ። ይህ የፕሬዝዳንቱ ፊርማ ተቆጣጣሪዎች ፌስቡክና ትዊተር ላይ ክትትል በማድረግ ህጋዊ ርምጃ እንዲወስዱ እድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።
ፕሬዝዳንቱ ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት ማህበራዊ ሚዲያዎች " ቁጥጥር የማይደረግበት አቅም" ነበራቸው ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ግን ህጋዊ ተግዳሮቶች ይገጥሙታል ተብሏል።
የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ወይም የፍትህ አካሉ እነዚህ ተቋማት ያላቸውን የህግ ከለላ ለማንሳት ሊሳተፉ ይገባል።
ትራምፕ የማህበራዊ ሚዲያዎችን የወግ አጥባቂዎችን ድምጽ በተደጋጋሚ ያፍናሉ ሲሉ ይወነጅሏቸዋል።
ረቡዕ እለት ትዊተርን የፕሬዝዳንቱ ሰሌዳ ላይ ከተጻፈው ሐሳብ ሥር "የትራምፕ መልዕክት እውነታነት ሊጤን ይገባዋል" የሚል ምልክት ካደረገ በኋላ ምርጫ ላይ ጣልቃ ይገባል ሲሉ ወንጅለውታል።
ድርጅቱ መልዕክቶቹ ዳግም ሊፈተሹ እንደሚገባ የሚገልጽ መልዕክት የሚያስቀምጥባቸው ተጠቃሚ የሐሰት ወይም ያልተረጋገጠ ሐሳብ ሲጽፍ መሆኑን ገልጿል።
ትዊተር ሐሙሰስ እለት የቻይናው መንግሥት ቃል አቀባይ ኮሮናቫይረስ መነሻው አሜሪካ ነው የሚል ጽሁፍ መለጠፋቸወን ተከትሎ " ስለኮቪድ-19 ያለውን መረጃ እውነታነት ያጣሩ" የሚል ማስጠንቀቂያ ለጥፎበታል።
ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተከታይ አላቸው።














