ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን የኃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ዘገባውም እንደሚያስረዳው ጥያቄውን ያቀረቡት እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው።

ፓርቲያቸው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የርዕሰ መስተዳድሩን ጥያቄ የተቀበለው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ምክንያታቸውንም ፓርቲያቸው ለክልሉ ምክር ቤት ያቀርባል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአምስት አመታት ያህል ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል።

በምትካቸውም ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾመዋል።