ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ

ለዘመናዊው የመፀዳጃ መቀመጫ ፈጠራ ሊመሰገን የሚገባው በለንደን የነበረ ሰዓት ሠሪ ነው።

በ18ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረው ይህ ቀላል የሆነ የታጠፈ ቱቦ ለዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች ችግር ምላሽ ያስገኘና አስፈላጊው ክፍል ነው።

ከግኝቱ ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላም እስካሁን መደበኛ የሆነው የዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች የሌሏቸው ሰዎች ቁጥር ከሁለት ቢልዮን በላይ ይሆናሉ። ሰዓት ሠሪው ቴክኖሎጂውን ቢያመጣውም ለሁሉም ማዳረስ ግን እስካሁን ችግር ሆኖ ቀጥሏል።

እንዴት መጣ

አሌክሳንደር ካሚንግ የመፀዳጃ ቤት መሃንዲስ ብቻ አልነበረም። ብዙ የፈጠራ ሥራዎቹ የተለዩ ነበሩ።

የአየር ጫናን ሊመዘግብ የሚችል የተራቀቀ መሣሪያ ለመሥራት በእንግሊዙ ንጉስ ጆርጅ 3ኛ ተቀጥሮ ነበር። ጥናታዊ ምርምሮችን ለማካሄድ የሚጠቅመውን ማይክሮቶም የተሰኘ እንጨት በስሱ የሚቆርጥ መሣሪያ በመስራትም የመጀመሪያው ነበር።

ዓለምን የቀየረው የአሌክሳንደር ፈጠራ ግን ከምህንድስና ሙያው ጋር አይገናኝም ነበር። ለውጡን ያመጣው እጥፋት የነበረበት ቱቦ ነው።

እ.አ.አ በ1775 አሌክሳንደር የ 'S' ን ቅርጽ ለያዘው ቧንቧ የፈጠራ ባለቤትነት ሆኖ ተመዘገበ። ይህም በዘመናዊ መንገድ ዉሃ የሚለቀውን የመፀዳጃ መቀመጫ ለመፍጠር መንገድ ከፈተ። ከዚህም ጋር አብሮ የሕዝብ ንጽህና ተከተለ።

ቀላል ዘዴ

ከዚህ ቀደም የዉሃ መልቀቂያው ዘዴ ሽታ ያስከትል ነበር። ጠበቅ ያለ የማፈኛ ዘዴ ካልተፈጠረለት በስተቀር ዉሃ ከተለቀቀ በኋላ በቧንቧው በኩል ወደ ጉድጓድ የዉሃ ሽንትና ሰገራ ቢያስወግድም የጉድጓዱን ሽታ ግን ወደ ላይ ይመልስ ነበር።

የአሌክሳንደር መፍትሔ ደግሞ ቀላል ነበር እሱም ቧንቧውን ማጠፍ ነበር። ዉሃ እጥፋቱ ላይ ስለሚከማች ወደ ላይ የሚመለሰውን ሽታ ይገድብ ነበር። ዉሃው በተለቀቀ ቁጥር ደግሞ ይታደሳል።

አሁን ያለው ቧንቧ እንደፈረንጆቹን ፊደል ቀድም ተከተል ቅርጹ ከ 'S' ወደ 'U' ቢዘዋወርም በመፀዳጃ ቤት ዉሃ የመልቀቅ ግንዛቤው ግን አልተቀየረም።

ግኝቱ ቢኖርም በሥራ ላይ ለማዋል ግን ረዥም ዓመታትን ፈጅቷል። እ.አ.አ በ1851 በለንደን ታላቅ ኤግዚብሽን ከዓለም አቀፍ ግኝቶች ጋር ለሕዝብ ቀረበ። በመፀዳጃ ቤት ዉሃ መልቀቅ በለንደን አዲስ ከመሆኑ የተነሳም ለሕዝቡ ታላቅ የደስታ ምንጭ ምክንያት ሆኖ ነበር ።

በዚህ መልኩ የተሠሩ መፀዳጃ ቤቶችን ለመጠቀም በእንግሊዝ ሀገር አንድ ሳንቲም ያስከፍል ነበር። እስከ ዛሬ ለዉሃ ሽንት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ ሲፈለግ 'አንድ ሳንቲም ልከፍል ነው' ይባላል።

ዘመናዊው የቧንቧ ሥራ ባሰገኘላቸው አዲስ ፈጠራ ለመደነቅና ለመተንፈስ ብለው በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የለንደን ነዋሪዎች ተሰልፈው ነበር።

ከዓለም የጤና ድርጅት በተገኘው መረጃ መሠረት እ.አ.አ በ1980 አንድ አራተኛ የሚሆነው የዓለም ህዝብ ብቻ የዘመናዊ የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ የነበረ ሲሆን ከ170 ዓመታት በኋላሁለት ሶስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ተጠቃሚ መሆን ችሏል።

ኢኮኖሚ ላ የሚስከትለው ወጪ

ይህ ማለት ከሁለት ቢልዮን ሕዝብ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የዘመናዊ መፀዳጃ ቤት አገልግሎት የላቸውም።

ይህ ዘዴ ጤናማ በሆነ መልኩ ''የሰውን ቆሻሻ ከሰው ግንኙነት ያርቃል'' እንጂ የቧንቧውንና የቱቦውን ችግር አያስወግድም።

እንደዚህ አይነት የቆሻሻ ማስወገጃ አገልግሎት ያላቸው የዓለም ሕዝቦች ግማሽ እንኳን አይሞሉም።