Unit 1: How do I...
Select a unit
- 1How do I...
- 2Unit 2
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 6
Listen to find out how to talk about where you live in English.
ያዳምጡና ስለሚኖሩበት አካባቢ እንዴት እንደሚያወሩ ይከታተሉ።
Activity 1
How do I talk about where I live?
እነዚህን አረፍተ ነገሮች በቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
A) I live in a town called Cambridge. It’s in England. How about you?
B) Where are you from?
C) I live in Glasgow. It’s a city in the West of Scotland.
መልሱን በጽሁፉ ወይም ከንግግሩ ውስጥ ይፈልጉ።
መልስዎን ለማጣራት ያዳምጡ። በመቀጠል ከጽሁፉ ጋር ያመሳክሩ።

ዘሩባቤል
ሰላም! እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። እኔ ዘሩባቤል እባላለሁ። አብሮኝ ቶም አለ።
Tom
Hi everybody! Welcome to the programme!
ዘሩባቤል
ዛሬ ስለሚኖሩበት ቦታ እንዴት እንደሚያወሩ እንማራለን። የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ሄለን እና ሁለተኛው ተናጋሪ ሃሪ ስለሚኖሩበት አካባቢ ሲያወሩ እናዳምጥ። የሚጠሩት ሃገር ትኛው ነው? የአካባቢያቸውስ ስም ምንድነው? ሁሉም በአንድ ጊዜ ባይገባዎት አይጨነቁ። ቡሃላ ላይ እናግዞታለን።
Helen
Where do you live?
Harry
I live in a town called Cambridge. It’s in England. How about you?
Helen
I live in Glasgow. It’s a city in the West of Scotland.
ዘሩባቤል
በትክክል ኣዳመጡ? ሃሪ የመጣው ከ Cambridge, England ነው።
I live in a town called Cambridge. It’s in England.
ዘሩባቤል
Helen የመጣችው ከ Glasgow, Scotland ነው።
I live in Glasgow. It’s a city in the West of Scotland.
Tom
OK! So let’s take a look at the language used when asking and answering the question ‘Where do you live?’
ዘሩባቤል
ለጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው ‘where’ ሲሆን፤ ሰዎች የት እንደሚኖሩ ‘live’ ለመጠየቅ ጥቅም ላይ ውሏል። ‘You’ የተጠቀምነው ስለሰውዬ ለማውራት ሲሆን፤ ‘do’ ደግም አያያዥ ግስ ነው። በተጨማሪ ስለ አንድ ቦታ ሰም ስንናገር ‘a’ አንጠቀምም።
I live in Glasgow.
ዘሩባቤል
ስለመጣንበት አካባቢ ስናወራ ግን ‘a’ መጠቀም እንችላለን። ለምሳሌ ትንሽ መንደር ‘a town’ ወይም ‘a city’ ትልቅ ከተማ ማለት እንችላለን።
I live in a town.
I live in Glasgow. It’s a city.
ዘሩባቤል
ሃሪን በድጋሚ ያዳምጡት። በደንብ የጠበቁት ቃላት የትኞቹ ናቸው?
I live in a town called Cambridge.
Tom
In this sentence, the word ‘town’ and the name of the place, ‘Cambridge’, are stressed. Listen again.
I live in a town called Cambridge.
Tom
The first half of the sentence is unstressed and sounds like this.
‘I live in a…’
‘I live in a…’
Listen again, and then repeat.
I live in a…
I live in a town called Cambridge.
ዘሩባቤል
አንድን ቦታ ለመግለጽ ‘in the’ ተጠቅመን በማስከተል ደግሞ ‘North’, ‘South’, ‘East’ ወይም ‘West’ እንጠቀማለን።
It’s in the West of Scotland.
ዘሩባቤል
ያስተውሉ! ‘Of’ የምንጠቀመው የሃገር ዌእም የቦታ ስም ለመግለጽ ነው። አስታውሱ!
Tom
Listen again. Which words are stressed in the sentence?
It’s in the West of Scotland.
ዘሩባቤል
ወይም ደግሞ የሃገሩን ስም ሳንጠቅስ በአጭሩ እንዲህ ማለት እንችላለን።
Tom
It’s in the West.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! ብዙ ነገር ስለተመለከትን እስቲ በድጋሚ ንግሮቹንና ጥያቄዎቹን እናዳምጥ።
Hi, where do you live?
ዘሩባቤል
Bath ከምትባል ከተማ እንደ መምጡ ለመናገር ምን ይላሉ?
Tom
I live in a city called Bath.
ዘሩባቤል
እርሶም እንደዛው ነው ያሉት? ማዳመጦን ይቀጥሉ።
Where’s that?
ዘሩባቤል
ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋል! በደቡባዊ እንግሊዝ ለማለት ምን ይላሉ? ‘Of’ መጠቀሞን አይዘንጉ።
Tom
It’s in the South of England.
ዘሩባቤል
Well done! አሁን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ። በእንግሊዝኛ እርስዎስ? ይበሉ።
I live in a city in the South of England. It’s called Brighton.
ዘሩባቤል
Great! ውጤታማ ምልልስ ነበር።
Tom
Yes! Remember that you can practise today’s language with all your friends and family!
ዘሩባቤል
ትክክል! ንግግሩን ለማስቀጠል የሚያስፈልጎትን ቃላት የምንምርበትን ቀጣዩን ዝግጅታችንን መከታተል አይዘንጉ።
Bye, everyone!
Tom
Bye! See you next time!
Learn more!
1. አንድን ሰው ስለሚኖርበት አካባቢ እንዴት ነው የምጠይቀው?
አንድን ሰው ስለሚኖርበት አካባቢ ለመጠየቅ በመጀመሪያ ‘where’ መጠቀም አለብን። ይህ ስለ ቦታ እያወራን እንደሆነ ያሳያል። ጥያቄውን የምናሟላው ‘live’ በማስገባትና በመቀጠል አያያዥ ግስ የሆነውን ‘do’ በመጠቀም ነው። ቅደም ተከተሉ ይህን ይመስላል።
Where do you live?
2. የምኖርበትን አካባቢ እንዴት ነው የምገልጸው?
በመጀመሪያ ‘I live in...’ እንላለን
ስም፡
የመኖሪያ አካባቢዎን ሰም ይናገሩ። ስለ ሃገረዎ መናገረም ይችላሉ።
ያስተውሉ ከስም በፊት ‘a’ ወይም ‘the’ አንጠቀምም።
I live in Glasgow, Scotland.
የምኖረው በትንሽ መንደር ወይም በትልቅ ከተማ ነው ማለት እንችላለን። ከነዚህ ቃላት ጋር ግን ‘a’ መጠቀም እንችላለን።
I live in a city (ትልቅ ከተማ).
I live in a town (ከተማ).
I live in a village (ትንሽ መንደር).
3. የመኖሪያ አካባቢዬን አቅጣጫ እንዴት ነው የምገልጸው?
አቅጣጫ ስንገልጽ፤ North (ሰሜን), South (ደቡብ), East (ምስራቅ) እና (ምዕራብ) እንጠቀማለን።
It’s in the North.
I live in the North.
ከአንድ ቦታ እያነጻጸርን ስናወራ ደግሞ ‘It’s in the’ + North/South/East/West + of + የቦታውን ወይም የሃገር ስም መጥቀስ አለብን።
It’s in the North of England.
It’s in the West of Scotland.
ስለምኖርበት አካባቢ የማወራው እንዴት ነው?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
ከ ‘town’ እና ‘city’ ጋር አናባቢ እንጠቀማለን።Question 1 of 3
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
አንዱ ዓረፍተ ነገር የጎደለ ቃል አለው።Question 2 of 3
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
‘North’ ከማለታችን በፊት፤ ‘the’ መጠቀም አለብን።Question 3 of 3
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
Answer these questions and tell us on our Facebook group!
ጥያቄዎቹን ይመልሱና በፌስቦክ ቡድናችን ላይ መልስዎን ይንገሩን።
Where are you from?
Do you live in a city, a town or a village?
Are you from the North, East, South or West of your country?
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ጠቃሚ ቋንቋዎችን ለመማርና የማዳመጥ ክህሎትዎን በልምምድ ለማዳበር ቀጣዩን How do I… ዝግጅታችንን ይከታተሉ።
Session Vocabulary
I live in a...
የምኖረው
city
ትልቅ ከተማ
town
ከተማ
village
ትንሽ መንደር
North
ሰሜን
South
ደቡብ
East
ምስራቅ
West
ምዕራብ