Unit 1: How do I...
Select a unit
- 1How do I...
- 2Unit 2
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
Session 4
Listen to find out how to talk about your morning routine in English.
ስለ ማለዳ ክንውኖችዎ በእንግሊዝኛ እንዴት ማውራት እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
How do I talk about my morning routine?
እነዚህን ድርጊቶች በሚጠበቁበት ቅደም ተከተል መሰረት ያስቀምጧቸው እና ከዚያ መልሶችዎን ያመሳክሩ።
• get up
• have a shower
• have breakfast
• wake up
መልሶችዎን ለማጣራት ማዳመጥዎን ይቀጥሉ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያወዳድሩት።

ዘሩባቤል
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በደህና መጡ። አዘጋጆች እኔ ዘሩባቤል እና ፊል ነን።
Phil
Hello, everybody. Welcome!
ዘሩባቤል
በዚህ ክፍል ዘወትር ማለዳ ስለሚያደርጓቸው ክንውኖች እናወራለን። የተወሰኑ ሰዎች ማለዳ ላይ ስለሚያደርጉት ክንውን ሲያወሩ በማዳመጥ እንጀምር። ሁሉም ነገር ባይገባዎት ብዙም አይጨነቁ፤ በኋላ እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ግን እያንዳንዱን ክንዋኔ በስንት ሰዓት እንደሚያደርጉት ለማወቅ ያዳምጡ። የሚያግዞት ሁለት ሐርጎች እናቀብልዎት፤ ‘get up’ መነሳት ማለት ሲሆን ‘wake up’ ደግሞ መንቃት ማለት ነው።
I wake up at 6 o’clock.
I get up at 7 o’clock.
I have a shower at 7 o’clock.
I have breakfast at 8 o’clock.
ዘሩባቤል
እያንዳንዱን ነገር ስንት ሰዓት ላይ እንደሚያደርጉ ልብ አሉ? ካላሉ ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፥ ስለእያንዳንዳቸው እናወራልን። ስለዚህ የመጀመሪያው ሰው ‘I wake up at…’ ነው ያሉት ። ሰዓቱን ሰምተዋል?
Phil
It was 6 o’clock. When you want to say the time, you have to use the word ‘at’ to mention the time. So, for example, I can say ‘I wake up at 5 o’clock’. Let’s practise. Listen and repeat.
I wake up at 6 o’clock.
ዘሩባቤል
በመቀጠል ተናጋሪው ‘I get up at…’ አሉ። ሰዓቱን ሰምተዋል? አዎ፥ ‘at 7 o’clock’ ነው። ‘wake up’ እና ‘get up’ የተለያዩ ትርጓሜዎች እንዳላቸው አይዘንጉ። ‘wake up’ ከእንቅልፍ ሲነቁ ሲሆን ‘get up’ ደግሞ ከነቁ በኋላ ከአልጋ ላይ ሲነሱ ነው።
Phil
Let’s practise saying the sentence. Listen and repeat.
I get up at 7 o’clock.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ፤ ቀጣዩ ተናጋሪ ‘she has a shower’ ነው ያሉት። ይህስ ስንት ሰዓት ላይ እንደሆነ ሰምተዋል? በድጋሚ ከጧቱ አንድ ሰዓት ላይ ነበር።
Phil
We use the action word ‘have’ with shower.
ዘሩባቤል
አዎ፥ ድርጊት ገላጩን ቃል ‘take’ ከገላ መታጠብ ጋር አብረን መጠቀም እንችላለን። ‘Have’ አንድን ነገር ማከናወን ወይንም ማስተናገድን ለመግለፅ ይጠቅማል።
Phil
Yes, let’s practise. Listen and repeat.
I have a shower at 7 o’clock.
ዘሩባቤል
በጣም ጥሩ! የመጨረሻው ተናጋሪ ቁርስ መብላታቸውን ገልጸዋል። ‘have breakfast’ሲሉ ‘to eat’ ማለት ነው፤ ይሄም ሌላኛው የ ‘have’ ጥቅም ነው። ፊል ‘have’ ከመጠጦች ጋርም መጠቀም እንችላለን?
Phil
You absolutely can. We can use ‘have’ to talk about eating and drinking. So I can say ‘I’m having a sandwich’ and ‘I’m having a coffee’.
ዘሩባቤል
በጣም ጠቃሚ ቃል ነው። ስለዚህ እኛስ ለምን ‘have a practice’?
Phil
Yes, let’s practise. Listen and repeat.
I have breakfast at 8’clock.
ዘሩባቤል
እሺ፥ የተማርነውን ለምን እንለማመድም? ከእንቅልፍ መንቃትን የሚገልፀውን ሐረግ በመጠቀም ስንት ሰዓት ላይ እንደምንነቃ በመግለፅ ለምን እንጀምርም? ሁለት ሰዓት በማለት እንለማመድ። በኋላ ላይ ለንፅፅር የፊልን ምላሽ ይሰማሉ።
Phil
I wake up at 8 o’clock.
ዘሩባቤል
አሁን ደግሞ ከአልጋ ላይ መነሳት የሚል ትርጉም የሚሰጠውን ሐረግ እንጠቀም። ያንን የሚያደርጉት በየትኛው ሰዓት ነው? በኋላ ላይ ለንፅፅር የፊልን ምላሽ ይሰማሉ።
Phil
I get up at 9 o’clock.
ዘሩባቤል
አሁን ደግሞ ሁለቱን የተለያዩ የ ‘have’ ትርጉሞች እንለማመድ፤ አንደኛው የሆነ ነገር ማድረግ ማለት ሲሆን፥ ሌላኛው ደግሞ መብላት ማለት ነው። ያስታውሷቸዋል? ከገላ መታጠብ ‘shower’ እና ከቁርስ ‘breakfast’ ጋር የተያያዙ ናቸው። ሁለቱን አረፍተ ነገሮች ይበሉና እንደቀደመው ጊዜ መልስዎን ከፊል መልስ ጋር ያነፃፅሩ።
Phil
I have a shower at 9 o’clock.
I have breakfast at 9 o’clock.
ዘሩባቤል
Did you say the same?
Phil
I think you did very well, and I hope you had fun listening to today’s lesson. Now, I’m going to have a coffee.
ዘሩባቤል
እኔም! በ‘wake up’ እና በ‘get up’ መካከል ያለውን የትርጉም ልዩነት ያስታውሱ፤ እናም ስለጊዜ ሲያወሩ ‘at’ መጠቀሞን አይርሱ፤ አብረውን ስለቆዩ እናመሰግናለን። መልካም ጊዜ።
Phil
Goodbye!
Learn more!
1. በ 'wake up' እና 'get up' መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
'Wake up' አንድ ሰው እንቅልፉን አቁሞ መንቃቱን የሚያመላክት ቃል ነው። 'Get up' አንድ ሰው ቀኑን ለመጀመር ከአልጋ ላይ መንሳቱን የሚጠቁም ቃል ነው። ስለዚህም መጀመሪያ ከእንቅልፍ እንነቃ እና ከዚያ ከአልጋ ላይ እንነሳለን።
2. 'Have' የተባለው ቃል 'have a shower' እና 'have breakfast' በሚሉት ሐረጎች ውስጥ ተመሳሳይ ትርጉም ነው የያዘው?
'Have' ነገሮችን ስለማድረግ ለማውራት ያገለግላል።
• have a shower
• have a look
• have a good time
• have a practice
(remember that 'practise' is a verb and 'practice' is a noun)
'Have' አንድ ነገርን ስለመብላት ወይንም ስለመጠጣት ለማውራት ይጠቅማል.
• have a meal
• have a sandwich
• have a coffee
• have a drink
3. 'At' ሁልጊዜ ከጊዜ ጋር እጠቀማለሁ?
ሁሌጊዜም በቀን ውስጥ ስላለ ውስን ጊዜ ስናወራ 'at' እንጠቀማለን።
• I get up at seven thirty.
• I have a shower at half past 8.
How do I talk about my morning routine?
4 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
'Get' የተባለው ቃል ከአንድ ነገር በላይ ወይንም ከፍ ብሎ የሚል ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን፤ከእንደዚህ አይነት ቃላትጋር አንድ ላይ አብሮ መሄድ አለበት።Question 1 of 4
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
ቅደም ተከተሉን ያስቡ።Question 2 of 4
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
ይህንን ቃል ስለተወሰነ ጊዜ ስናወራ መጠቀም አለብን።Question 3 of 4
ሓገዝ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ኣመት
ቁርስ ስለመብላት ለማውራት ይህንን ቃል መጠቀም አለብን።Question 4 of 4
Excellent!Great job!ሕማቕ ዕድል!ዘመዝገብኩምዎ ነጥቢ ...:
What time do you get up in the morning?
What do you have for breakfast?
Answer these questions and tell us on our Facebook group!
እነዚህን ጥያቄዎች በፌስቡክ ቡድናችን ይመልሱልን።
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ አጠቃቀሞችን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ How do I... ክፍላችን ይጠብቁን።
Session Vocabulary
wake up
መንቃትget up
መነሳትhave a shower
ገላን መታጠብhave breakfast
ቁርስ መብላትat 7 o’clock
አንድ ሰዓት ላይ