บทเรียน 1: How do I...
เลือกบทเรียน
- 1How do I...
- 2Unit 2
- 3Unit 3
- 4Unit 4
- 5Unit 5
- 6Unit 6
- 7Unit 7
- 8Unit 8
- 9Unit 9
- 10Unit 10
- 11Unit 11
- 12Unit 12
- 13Unit 13
- 14Unit 14
- 15Unit 15
- 16Unit 16
- 17Unit 17
- 18Unit 18
- 19Unit 19
- 20Unit 20
- 21Unit 21
- 22Unit 22
- 23Unit 23
- 24Unit 24
- 25Unit 25
- 26Unit 26
- 27Unit 27
- 28Unit 28
- 29Unit 29
- 30Unit 30
- 31Unit 31
- 32Unit 32
- 33Unit 33
- 34Unit 34
- 35Unit 35
- 36Unit 36
- 37Unit 37
- 38Unit 38
- 39Unit 39
- 40Unit 40
บทเรียนย่อย 5
Listen to find out how to talk about your abilities in English.
በእንግሊዝኛ ስለችሎታዎችዎ እንዴት ነው ማውራት እንደሚችሉ ለማወቅ ይሄንን መሰናዶ ያዳምጡ።
แบบฝึกหัด 1
How do I talk about my abilities?
የእነዚህ ቃላት ተቃራኒዎች ምን እንደሆኑ ያውቃሉ? ሰንጠረዡን ይሙሉ።
good |
|
well |
|
መልሶችዎችን ለመፈተሽ ይሄንን ያዳምጡ። ከዚያም ከታች ካለው ፅሁፍ ጋር ያመሳክሩ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን፤ እንኳን ወደ How do I… ዝግጅታችን በሰላም መጡ። አስተናጋጃችሁ እኔ ምህረተስላሴ እና ሳም አብረናችሁ ነን።
Sam
Hello! Welcome!
ምህረተስላሴ
ዛሬ እንዴት ስለችሎታዎቻችን እንደምናወራ እንማራለን። አራት ሰዎች ስለ እግር ኳስ 'football' ችሎታቸው ሲናገሩ እናዳምጥ። ንግግራቸውን ካልተረዱት አያስቡ፤ ቆየት ብለን እናግዝዎታለን። ለአሁኑ ከተናጋሪዎቹ የትኛው ጎበዝ ኳስ ተጫዋች እንደሆነ ለመገንዘብ ይሞክሩ።
1. I play football quite well, yeah.
2. I'm pretty good, but my sister's better. She's very good at football!
3. I'm really bad at football, to be honest.
4. I play football very badly.
Sam
Who was the best at football, did you hear it?
ምህረተስላሴ
ጎበዟ ኳስ ተጫዋች የሁለተኛው ተናጋሪ እህት ናት። ታዲያስ ሳም፤ እርሷ ከሁሉም መብለጧን ያወቅነው እንዴት ነው?
Sam
Let's listen again to two of the people.
ምህረተስላሴ
Ok! ሰዎቹ 'good' ጥሩ እና 'bad' መጥፎ የሚሉ ቃላትን ተጠቅመዋል። በድጋሚ ሲያዳምጡ ከ'good' ወይም 'bad' በፊት የሚመጣው ግስ ምን እንደሆነ ያስተውሉ።
I'm pretty good…
She's very good at football!
I'm really bad at football…
ምህረተስላሴ
እሺ፤ ስለዚህም 'good' እና 'bad' ቅፅሎች ናቸው። ስለዚህም ብዙ ጊዜ የ 'be' ግስን እንጠቀማለን ማለት ነው።
Sam
Yes, they said 'she is' and 'I am'. But we naturally say 'she's' and 'I'm' when speaking. Now listen again – what little word do you hear before 'football'?
She's very good at football!
I'm really bad at football…
ምህረተስላሴ
ተናጋሪዎቹ የተጠቀሙት ቃል 'at' ነው። እርስዎ ጎበዝ ወይም ደካማ ስለሆኑበት ተግባር ሲናገሩ ከ 'good' ወይም ከ 'bad' ጋር 'at'ን ይጠቀማሉ።
Sam
Quick practice! Repeat after me:
She's very good at football!
I'm really bad at football.
Shall we listen to the two other people?
ምህረተስላሴ
አዎ። ተናጋዎቹ 'good' እና 'bad'ን ሳይሆን፤ ችሎታቸውን የሚገልፁ ግሶችን ተጠቅመዋል። በድጋሚ ያዳምጡ።
I play football quite well, yeah.
I play football very badly.
ምህረተስላሴ
የተጠቀሙት 'play' የሚለውን የአሁን ጊዜ አረፍተ ነገር ነው። 'cook' ማብሰል፣ 'dance' መጨፈር ወይንም 'speak English' እንግሊዝኛ መናገር የመሳሰሉ ግሶችን መጠቀም ይችላሉ።
I play football quite well, yeah.
I play football very badly.
ምህረተስላሴ
ቃላቱ 'well' በጥሩ ሁኔታ እና 'badly' በመጥፎ ሁኔታ ነበሩ። 'very' በጣም የሚለውን ቃልም ሰምተዋል። ይህም ቀደም ብለን ከሰማነው ከ 'really' እጅግ በጣም ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው። 'Quite' በእጅጉ ደግሞ ቀድሞ ከሰማነው ጋር ከ 'pretty' ደህና ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ነው ያለው። እነዚህን ቃላት ከ 'good' እና 'bad' እንዲሁም ከ'well' እና 'badly' ጋር መጠቀም ይችላሉ።
Sam
Let's practise the pronunciation. Repeat after me:
I play football quite well.
I play football very badly.
Which is absolutely true! I'm terrible at football.
ምህረተስላሴ
አሁን የተማሩትን የሚለማመዱበት ጊዜ ነው። በጣም ጎበዝ ባይሆኑም ጥሩ የሆኑበትን እንቅስቃሴ ያስታውሱ። ከ 'good' በፊት የምንጠቀማቸው ተግባሩን ሊገልፁልን የሚችሉ ሁለት ቃላት እንዳሉ ያስታውሱ። እስኪ አረፍተ ነገሩን ይመስርቱ። ከዚያ በኋላ ሳም ጎበዝ የሆነችበትን ተግባር ስትነግርዎ መልስዎን ከሷጋ ያነፃፅሩ።
Sam
I'm quite good at cooking.
ምህረተስላሴ
Great! አንድ ነገር ላይ 'I'm pretty good at…' ሊሉም ይችላሉ።
አስከትለው የማይችሉትን ነገር ይናገሩ። መልስዎንም ከሳም መልስ ጋር ያነፃፅሩ።
Sam
I'm very bad at dancing!
ምህረተስላሴ
አሁን በሚገባ መስራት የሚችሉትን እንቅስቃሴ ይምረጡ። እዚህ ላይ ግስ መጠቀምን ያስታውሱ።
Sam
I speak English well.
ምህረተስላሴ
Yes, Sam, you are quite good at English.
Sam
Thank you!
ምህረተስላሴ
በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲካኑ፤ ለሌላ የ How do I… ዝግጅት በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!
Sam
Yes, so you'll be excellent at English! Bye, everyone!
Learn more!
1. ቅፅሎችን እና ስሞችን በመጠቀም እንዴት ስለችሎታዎቼማውራት እችላለሁ?
‘Good’ እና ‘bad’ የመሳሰሉትን ቅፅሎች ችሎታዎቻችንን ለመግለፅ እንጠቀምባቸዋለን። እነዚህን የበለጠ ጠንካራ ማድረግ ከፈለጉ ‘excellent’ እጅግ በጣም ጥሩ እና ‘terrible’ እጅግ መጥፎን መጠቀም ይችላሉ። ከእነዚህ ጋር ‘be’ መጠቀምን ያስታውሱ።
subject + be + adjective
She’s good.
We’re terrible.
አንድን ውስን ተግባር ለመጥቀስ ሲፈልጉ፤ ከስም (ወይም በ‘–ing’ ከሚያልቅ ቃል በፊት ‘at’ን መጠቀምን አይርሱ
subject + be + adjective + at + noun/ gerund
I’m bad at French.
He’s excellent at (playing) football.
2. ግሶች እና የግስ ገላጮችን በመጠቀም ስለችሎታዎቼ እንዴት ማውራት እችላለሁ?
ችሎታዎን ለመግለጽ እንደ 'play'፣ 'cook'፣ 'dance'፣ 'speak' ያሉ ቃላትን ከተጠቀሙ በኋላ ‘well’ ወይንም ‘badly’ን በማስከተል ስለችሎታዎችዎ ማውራት ይችላሉ።
I speak French badly.
He plays football very well.
3. ችሎታዎቼ ጠንካራወይም ደካማመሆናቸውን እንዴት መግለፅ እችላለሁ?
‘Good’ እና ‘bad’ እንዲሁም ‘well’ እና ‘badly’ የሚከተሉትን በመጠቀም የበለጠ ግልፅ ማድረግ ይችላሉ
በጣም
በጣም
ደህና
ደህና
ከሚያብራሩት ቃል በፊት ሁሌም ይመጣሉ
You’re very good at dancing.
You dance really well.
ስለችሎታዎቼ እንዴት ማውራት እችላለሁ?
4 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ
คำใบ้
‘Good at’ አንድ ላይ እንደሚመጡ ያስታውሱQuestion 1 of 4
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ
คำใบ้
‘Quite’ ከ ‘good’ በፊት እንደሚመጣ ያስታውሱ።Question 2 of 4
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ
คำใบ้
ከ’speak’ በኋላ ቋንቋውን ይጥቀሱ።Question 3 of 4
ช่วยเหลือ
แบบฝึกหัด
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ
คำใบ้
‘Really’ የተባለው የግስ ገላጭ ‘badly’ን እያብራራ ነው፤ ስለዚህም ቀድሞት ይመጣል።Question 4 of 4
Excellent!เยี่ยม!แย่หน่อย!คุณทำคะแนนได้:
Come to our Facebook group to tell us what you’re good and bad at!
ወደ ፌስቡክ ገጻችን ብቅ ይበሉና በምን ዓይነት እንቅስቃሴዎች ላይ ጥሩ እና መጥፎ እንደሆኑ ይንገሩን።
Join us for our next episode of How do I…, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ቋንቋ ለመማርና እና የማዳመጥ ክህሎትዎን ለማዳበር በቀጣዩ የ How do I… ዝግጅታችን ይጠብቁን።
Session Vocabulary
football
እግር ኳስto play (football)
እግር ኳስ መጫዎትcooking
ማብሰልto cook
ማብሰልdancing
መጨፈርto dance
መጨፈርto speak (a language)
አንድ ቋንቋ መናገር