ታዋቂው ከያኒ ራሱን «ለትርፍ የማይሰራ ተዋናይ» ማድረጉን ይፋ አደረገ

እንግሊዛዊው የሆሊውድ ተዋናይ ማይክል ሺን ራሱን «ለትርፍ የማይሰራ ተዋናይ» ለማድረግ መወሰኑን ይፋ አደረገ።
እ.ኤ.አ በ 2019 የአለም የቤት አልባ ሰዎች ዋንጫ ጨዋታዎችን ለመደገፍ ሲል በአሜሪካ እንዲሁም በእንግሊዝ ያሉ ሁለት መኖሪያ ቤቶቹን መሸጡ ይታወሳል።
ተዋናዩ በስራው የሚያገኘውን ቀጣይ ገቢዎችንም ሌሎች ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ እንደሚያውለው ተናግሯል።
«ትልቅ ገንዘብ በእንዲህ ያሉ ስራዎች ላይ ማዋሌ የሚሰጠው ትልቅ ነጻነት አለ። ምክኒያቱም ተመልሼ እንደማገኘው ስለማውቅ። በሂደት ራሴን ወደ ማህበራዊ ኢንተርፕራይዝ ወይም ለትርፍ ወደማይሰራ ከያኒነት ቀይሬአለሁ» ሲል ሺን ገልጿል።
ዘ ቢግ ኢሹ ከተባለው ሚዲያ ጋር ባደረገው ቆይታም የቤት አልባ ሰዎች ዋንጫ ጨዋታዎችን በ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ለመደገፍ ስለሄደበት መንገድ አብራርቷል።
«ይህንን ጨዋታ ለመደገፍ ቃል ገብቼ የነበረ ቢሆንም ብዙ ነገሮች ገና ሳይሰሩ ገንዘቡ ግን አለቀ። ውሳኔ መወሰን ነበረብኝ። በርግጥ ጥዬ መውጣት እችል ነበር፤ ነገር ግን እንደዛ ማድረግ አልፈልኩም። ከዛም ያለኝን ገንዘብ በሙሉ ጫወታው እንዲካሄድ አዋልኩት። ቤቶቼን ስሸጥ አስፈሪ እና እጅግ አስጨናቂ ውሳኔ ነበር። ገና ለረጅም ግዜ ዋጋ ያስከፍለኛል። ነገር ግን ገቢ ማግኘቴን ከቀጠልኩ ይህ ነገር አያጠፋኝም ወደሚለው ድምዳሜ ላይ ደረስኩ» ሲልም ተናግሯል።
ዘ ሰታር ኦፍ ጉድ ኦምኒስ፣ ዘ ዳምንድ ዩናይትድ እና ኒክሰን 50 ሺህ ፓውንድ በ አምስት አመት የዌልስ ተማሪዎች በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገብተው እንዲማሩ ለማስቻል ለመክፈል ቃል ገብተዋል።
ሺን ለዚህ ሁሉ መነሻ ነጥቡ ለ72 ሰዓታት የቆየው ዘ ፓሽን የተሰኘው ፊልም ቀረጻ ሲሆን ይህም በትውልድ ከተማው ዌልስ ውስጥ እ.ኤ.አ 2011 የተቀረጸ ነበር።
«መኖራቸውን እንኳን የማላውቃቸውን ተቋማት ተወልጄ ባደኩበት ከተማ እንዳሉ ተረዳሁ። ወጣቶችን ለማገዝ የተቐቐሙ ትንንሽ ተቐማትን አግኚቼም ነበረ። ከጥቂት ወራት በኋላ ተመልሼ በመምጣት ተቐማቱ የገንዘብ ምንጮቻቸው ምን ምን እንደሆኑ ለማወቅ ጥረት ሳደርግ ጭራሹን ከስራ መውጣታቸውን ሰማሁ» ሲል ሺን ተናግሯል።
«የአንድን ህጻን ልጅ ህይወት የሚያሻሽል ይህንን ስራ ለመስራት የሚያስፈልግ ትንሽ ገንዘብ መሆኑን በመረዳቴ ለማገዝ ፈለኩኝ። ድጋፌም ቀጣይነት እንዲኖረው ስለፈለኩኝ ነው ተመስሼ ወደ ትውልድ ቀዬዬ የሄድኩት» ሲልም ሺን አክሏል።












