ቶፊክ ማክሉፊ፣ 33
ቶፊክ ማክሉፊ የመካከለኛ ርቀት ሯጭ ነው (በ800 እና በ1,500 ሜትር ውድድሮች)
ቶፊክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስምንት ዓመት በፊት በተካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ በ1,500 ሜትር ወርቅና በሪዮ ኦሊምፒክ ደግሞ ሁለት የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

አፍሪካውያን ሯጮች በተለይም ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን አትሌቶች በመካከለኛ እና በረጅም ርቀት የሩጫ መስኮች በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የበላይ ናቸው።
ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከዚህ በፊት በውድድሩ ውስጥ ያልነበሩ ስፖርቶችን በማካተት በዚህ ሳምንት መካሄድ ይጀምራል።
በዚህም መሰረት አምስት የስፖርት አይነቶች በውድድሩ ውስጥ እንደተካተቱ ታውቋል፤ እነሱም የውሃ ላይ ሸርተቴ (ሰርፊንግ)፣ ተራራ መውጣት (ክላይምቢንግ)፣ ቤዝቦል፣ ስኬት ቦርዲንግ እና ካራቴ ሲሆኑ የተወሰኑ አፍሪካውያን በእነዚህ ዘርፎቹ ይወዳደራሉ።
አርብ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም የቶኪዮው ኦሊምፒክ ሲጀምር በተለያዩ ስፖርት ውድድሮች የሚሳተፉ በርካታ አፍሪካውያን ሲኖሩ ኢትዮጵያም በኦሊምፒክ ስሟ በሚጠራባቸው ዘርፎች የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ልካለች።
ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ በርካታ አገራት በተለያዩ ዘርፎች በውድድሩ ይሳተፋሉ ከእነዚህ መካከል በቶኪዮው ኦሊምፒክ ላይ ትኩረት ከተደረገባቸው መካከል ከስኬታማዎቹ እና ከአዲሶቹ መካከል የተወሰኑትን ወድድር ዘርፎቹ እንዲህ አቅርበናል።

ቶፊክ ማክሉፊ የመካከለኛ ርቀት ሯጭ ነው (በ800 እና በ1,500 ሜትር ውድድሮች)
ቶፊክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስምንት ዓመት በፊት በተካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ በ1,500 ሜትር ወርቅና በሪዮ ኦሊምፒክ ደግሞ ሁለት የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

ዋሊ ቢዳኒ አልጄሪያዊ ክብደት አንሺ ሲሆን ከዚህ ቀደም በለንደንና በሪዮ ኦሊምፒኮች ተሳትፏል።

አዚናይዴ ላርሎስ የእጅ ኳስ ተጫዋች ስትሆን የአንጎላ ብሔራዊ የእጅ ኳስ ቡድን አባል ናት።
ከዚህ በፊት በተደረጉ ሦስት የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች።

ናይጄል አሞስ ቦትስዋናዊ ሯጭ ሲሆን ለንደን ላይ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር ላይ በወንዶች የ800 ሜትር የብር ሜዳሊያ አግኝቶ ነበር።
የዚህ ዓመቱ የቶኪዮ ውድድር ሦስተኛው የኦሊምፒክ ተሳትፎው ይሆናል።

የቡርኪናፋሶ ዜጋው ሁግስ ፋብሪስ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም አትሌቲከስ ሻምፒዮና ላይ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

የቡሩንዲ ዜጋ የሆነችው ፍራንሲን ኒዮንሳባ በሪዮ ኦሊምፒክና በዓለም ሻምፒዮና በሴቶች የ800 ሜትር ሩጫ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ሼክ ሲሴ ከአራት ዓመት በፊት ሪዮ ላይ በተካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ለኮትዲቯር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በማስገኘት ታሪክ ሰርቷል።
በተጨማሪም በቴኳንዶ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ለመሆንም በቅቷል።

ኮትዲቯራዊቷ ማሪ-ጆዜ ታ ሉ የ100 እና የ200 ሜትር ሯጭ ናት።
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በሴቶች የ100 ሜትር ሩጫ የነሐስ ሜዳሊያ ያገኘች ሲሆን፤ በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ ደግሞ በ100 እና 200 ሜትር ውድድሮች ላይ አራተኛ ሆና ጨርሳለች።

ሃይዲ ሞርሲ የዘመናዊው ፔንታትሎን አትሌት ስትሆን፤ በዋነኝነት በዋና እና በፈረስ ግልቢያ ትወዳደራለች።
በቶኪዮው ውድድር ስትካፈል ሁለተኛዋ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ተሳትፎዋ ይሆናል።

አዝሚ ሚሄልባ ግብጻዊ የተኩስ ተወዳዳሪ ሲሆን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ሦስተኛው የኦሊምፒክ ውድድር ተሳትፎው ይሆናል።
በግንቦት ወር በተደረገው የዓለም የተኩስ ውድድር ላይ ተሳትፎ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል።

ጊያና ፋሩክ ግብጻዊት የካራቴ ተወዳዳሪ ስትሆን የቶኪዮው ኦሊምፒክ የመጀመሪያዋ የኦሊምፒክ ውድድር ይሆናል።
ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ በዓለም የካራቴ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ተሳትፋ አንድ የወርቅ እና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

የ27 ዓመቱ ኤርትራዊ ብስክሌተኛ መርሃዊ ቅዱስ ከሁለት ዓመት በፊት ቱርክ ውስጥ በተካሄደ ውድድር ሦስተኛ ለመውጣት ችሏል።
በዚህ ዓመትም በኤርትራ የብስክሌት ሻምፒዮና ላይ በተናጠል አሸናፊ ሲሆን በአጠቃላይ ደግሞ ሁለተኛ ለመሆን ችሏል። በዚህ ዓመት በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሲወዳደር የመጀመሪያው የኦሊምፒክ ተሳትፎው ነው።

አማኑኤል ገብረእግዚአብሔር በኦሊምፒክ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው። ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የአፍሪካ የጎዳና ላይ የብስክሌት ሻምፒዮና ላይ አንደኛ ወጥቶ አሸንፏል።

ኤርትራዊቷ ሞሳና ደበሳይ ከሁለት ዓመት በፊት በተደረጉ የአፍሪካ የጎዳና ላይ የብስክሌት ውድድሮች አሸናፊ ሆናለች።
ወንድሟ መክሰብ ደበሳይም የብስክሌት ተወዳዳሪ ነው።

ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ጊደይ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ክብረ ወሰን ባለቤት ስትሆን በቅርቡም የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን አሻሽላለች።
ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10 ሺህ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸንፋለች።

ሰለሞን ባረጋ ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ሯጭ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።
በኦሊምፒክ መድረክ ላይ ለመሳተፍ የቶኪዮ የኦሊምፒክ ውድድር የመጀመሪያው ነው።

ኢትዮጵያዊው ሯጭ ዮሚፍ ቀጀልቻ በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ሲሳተፍ የቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመሪያው ነው።
ዮሚፍ ከሦስት ዓመት በፊት የዓለም የቤት ውስጥ ሩጫ ሻምፒዮና ላይ በ3 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ለማሸነፍ ችሏል።
ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10 ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

ኢትዮጵያዊው የማራቶን ሯጭ ሌሊሳ ዴሲሳ ከሁለት ዓመት በፊት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል።

ሹራ ቂጣታ ኢትዮጵያዊ የማራቶን ሯጭ ነው።
ባለፈው ዓመት ለንደን ላይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ታዋቂውን ኬንያዊ ሯጭ ኢሉድ ኪፕቾጌን በመቅደም የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል።

ኢትዮጵያዊቷ የመካከለኛ ርቀት ሯጯ ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ ዓመት የካቲት ላይ ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደ የሴቶች የ1,500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰን ለመስበር ችላለች።
ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች።

ጋምቢያዊቷ የአጭር ርቀት ሯጭ ጊና ባስ ከሁለት ዓመት በፊት ሞሮኮ ላይ በተካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በ200 ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፋለች።
በዚህ ዓመት በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ስትወዳደር ሁለተኛዋ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ነው።

ኬንያዊው ጦር ወርዋሪ ጁሊየስ የጎ ሪዮ ላይ በተደረገው ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ የብር ሜዳሊያ ለማግኘት ችሎ ነበር።
ዩቲዩብ ላይ ያሉትን የስፖርቱን ቪዲዮዎች በመመልከት ችሎታውን ያዳበረው ጁሊየስ 'ሚስተር ዩቲዩብ' በሚል የቅጽል ስም ይታወቃል።

ኬንያዊቷ የማራቶን ሯጭ ብጂድ ኮስጌይ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የቺካጎ ማራቶንን እንዲሁም ላለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ደግሞ የለንደን ማራቶንን ለማሸነፍ ችላለች።
ብሪጂድ ኮስጌይ ከሁለት ዓመት በፊት በቺካጎው ማራቶን ላይ ስታሸንፍ የሴቶች የማራቶን ክብረ ወሰንን ሰብራለች። የቶኪዮው ኦሊምፒክ የመጀመሪያዋ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ነው።

ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ታዋቂ የረጀም ርቀት ሯጭ ነው።
ኪፕቾጌ ከሦስት ዓመት በፊት በርሊን ላይ በተደረገ ውድድር የወንዶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በእጁ አስገብቷል።
በሪዮ ኦሊምፒክ ላይም በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል።

ቢያትሪስ ቼፕኮች የወቅቱ የመሰናክል ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ናት።
የረጅም ርቀት ሯጯ ቢያትሪስ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ በ3ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ኬንያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ ፌዝ ኪፕዬጎን ከአራት ዓመት በፊት ሪዮ ላይ በተደረገው ኦሊምፒክ በ1500 ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
ቀደም ሲል በተካሄዱ ሁለት የዓለም ሻምፒዮናዎች ላይ ተወዳድራ የብር ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች።

ሞሮኳዊቷ ቦክሰኛ ከዲጃ ማርዲ በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ የተሳተፈች ቢሆንም ድል አልቀናትም ነበር።
ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የሴቶች የዓለም የቦክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፋ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ሞሮኳዊቷ ሯጭ ራባብ አራፊ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዳይመንድ ሊግ ላይ በሴቶች የ1500 ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፋለች።
የዚህ ዓመቱ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሁለተኛዋ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ነው።

ራምዚ ቡካያም የዳበረ ልምድ ያለው የውሃ ላይ ሸርተቴ ስፖርተኛ ነው።
በኦሊምፒክ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረገው የውሃ ላይ ሸርተቴ [ሰርፊንግ] ስፖርት አገሩን በመወከል ተሳታፊ ይሆናል።

ሞሮኳዊው ሱፊያን ኤል ባካሊ ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ3ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።
ብራዚል ሪዮ ውስጥ በተካሄደው ኦሊምፒክ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፏል።

የሞዛምቢክ ዜጋ የሆነችው ማሪያ ማቻቭ ለመጀመሪያ ጊዜ በጀልባ ውድድር [ሴይሊንግ] በቶኪዮው ኦሊምፒክ ትወዳደራለች።

ሞዛምቢካዊቷ የጀልባ ውድድር [ሴይሊንግ] ስፖርተኛ ዴዚ ናሃኩይል በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ስትሳተፍ የቶኪዮው የመጀመሪያዋ ነው።
ከሁለት ዓመት በፊት በአፍሪካ የጀልባ ቀዘፋ ሻምፒዮና ላይ አሸናፊ ሆናለች።

ለሞዛምቢካዊቷ የጀልባ ላይ ውድደር [ሴይሊንግ] ስፖርተኛ ዴኒስ ፓሩክ የቶኪዮው ኦሊምፒክ የመጀመሪያዋ የኦሊምፒክ ውድድር ተሳትፎዋ ነው።
ከሁለት ዓመት በፊት ዴኒስ ከማሪያ ጋር በመሆን በአፍሪካ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፋ አሸንፋለች።

ናሚቢያዊው ማይክ ዲክማን አገሩን በጀልባ ቀዘፋ ስፖርት በኦሊምፒክ ውድድር ላይ በመወክል የመጀመሪያው ነው።

ናሚቢያዊቷ የ400 ሜትር ሯጭ ቢያትሪስ ማሲሊንጊ ከ20 ዓመት በታች አስካሁን ከተመዘገቡት ፈጣን ሰዓቶች መካከል ሦስተኛውን አስመዝግባለች።
ቢሆንም ግን በተፈጥሮ ባላት ከፍ ያለ የቴስቴስትሮን መጠን ምክንያት በዘርፉ በኦሊምፒክ ላይ እንድትወዳደር ባይፈቀድላትም፤ በሌሎች ስፖርቶች ላይ ተሳታፊ ትሆናለች።

ናሚቢያዊቷ ሯጭ ክርስቲን ምቦማ በዚህ ዓመት በተደረገ የ400 ሜትር ውድድር ከ20 ዓመት በታች የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች።
ቢሆንም ግን በተፈጥሮ ባገኘችው ከፍ ያለ የቴስቴስትሮን መጠን ምክንያት በዘርፉ በኦሊምፒክ ላይ እንድትወዳደር ባይፈቀድላትም፤ በሌሎች ስፖርቶች ላይ ተሳታፊ ትሆናለች።

ኒጀራዊቷ የትራክና የመስክ ሯጭ አሚናቱ ሴይኒ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ተሳትፋለች።

ናይጄሪያዊቷ ብለሲንግ ኦካግባሬ የአግድመት ዝላይና የአጭር ርቀት ስፖርተኛ ነው።
የወቅቱ የ100 ሜትር ሩጫ ውድድር ክብረ ወሰንን ይዛ ቆይታ ባለፈው ሰኔ ላይ ደግሞ የእራሷን ክብረ ወሰን አሻሽላዋለች።
የርቀቱን የናይጄሪያና የአፍሪካ ክብረ ወሰንን የያዘች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለዓለም ክብረ ወሰን የምትጠበቅ ሯጭ ናት።

አልዛቤት አንያናቾ በቴኳንዶ ውድድር ናይጄሪያን በኦሊምፒክ ውድድር ላይ በመወከል በታሪክ ሁለተኛዋ ስትሆን ባለፉት 16 ዓመታት ውስጥ ደግሞ የመጀመሪያዋ ናት።

ዲቫይን ኦዱዱሩ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ውድድር ላይ የተሳተፈው ከአምስት ዓመት በፊት ሪዮ ላይ ነበር።
በሪዮው ኦሊምፒክ የአጭር ርቀት ሯጩ ኦዱዱሩ ለሩብ ፍጻሜ ውድድር ያለፈ ብቸኛው ናይጄሪያዊ ነበር።

ናይጄሪያዊቷ አትሌት ቶቢ አሙሳን ከሦስት ዓመት በፊት አውስትራሊያ ውስጥ በተካሄደው የኮመንዌልዝ ጨዋታዎች ላይ በ100 ሜትር የመሰናክል ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፋለች።
ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የሪዮው ኦሊምፒክ ላይ አሙሳን የሩብ ፍጻሜ ላይ ደርሳ ነበር።

ኤሴ ብሩሜ ሰባት ሜትርና ከዚያ በላይ መዝለል ከቻሉ ሦስት አፍሪካውያን ሴቶች መካከል አንዷ ናት።
ናይጄሪያዊቷ ስፖርተኛ በመጀመሪያ በኦሊምፒክ ውድድር ላይ የተሳተፈችው ሪዮ ላይ ሲሆን እዚያም የአምስተኛ ደረጃን አግኝታለች።
ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የነሐስ ሜዳሊያ ለማግኘት ችላለች።

ናይጄሪያዊው አሎሎ ወርዋሪ ቹክዉቡካ ኢኔክዌቺ ከሦስት ዓመት በፊት በተካሄደው የኮመንዌልዝ ጨዋታዎች ላይ የብር ሜዳሊያ ለማግኘት ችሏል።
በዓለም ሻምፒዮና ላይ ለፍጻሜ በመድረስ ብቸኛው ናይጄሪያዊ በመሆን ስምንተኛ ደረጃን አግኝቷል።

ናይጄሪያዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ኡሾሪትሴ ኢትሴኪሪ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ በ100 ሜትር ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

ናይጄሪያዊቷ ኤስተር ቶኮ ከሁለት ዓመት በፊት አፍሪካ ውስጥ በተደረገ ውድድር የነሐስና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።
ኤስተር አገራቸውን ከሚወክሉ የጀልባ ቀዘፋ ተወዳዳሪዎች መካከል መቀመጫዋ ናይጄሪያ ሲሆን ቶኪዮ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ትሳተፋለች።

አዮሚዴ አገሯን ወክላ በኦሊምፒክ ላይ ስትቀርብ የመጀመሪያዋ ሴት ናይጄሪያዊት ናት።
ቀደም ሲል ሞሮኮ ላይ በተካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ በውድድሩ አራት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

ሮድኒ አገሩን በቶኪዮው ኦሊምፒክ ወክሎ ይቀርባል።
ይህ ኦሊምፒክ ከሪዮው ቀጥሎ ሁለተኛው ተሳትፎው ነው። ከሁለት ዓመት በፊት በአገሩ የዓመቱ ኮከብ ስፖርተኛ ተብሎ ተመርጧል።

ዋይዴ ቫን ኒርኪርክ በሪዮው ኦሊምፒክ በ400 ሜትር ውድድር ለደቡብ አፍሪካ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።
በዚያ ውድድር ላይ የውድድሩን ባለክብረ ወስን አሜሪካዊውን ማይክል ጆንሰንን በማሸነፍ አዲስ የዓለምን ክብረ ወስን አስመዝግቧል።

ቻድ ለ ክሎስ በዋና ውድድር በርካታ ሜዳሊያዎችን ያገኘ ሲሆን፤ ይህም በለንደን ኦሊምፒክ ላይ ወርቅ እንዲሁም በሪዮው ኦሊምፒክ ደግሞ ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን ይጨምራል።

አካኒ ከሦስት ዓመት በፊት በተካሄደው የኮመንዌልዝ ጨዋታዎች ላይ በ100 ሜትር ውድድር ለደቡብ አፍሪካ የወርቅ ሜዳሊያን አስገኝቷል።
በሁለት ዓመት በፊት ደግሞ በዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ሆኗል።

ካትሊን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ውድድር ቶኪዮ ላይ ትሳተፋለች።
ደቡብ አፍሪካዊቷ የጅምናስቲክ ስፖርተኛ ካትሊን ከጥቂት ዓመታት በፊት በተካሄዱት የአፍሪካ ሻምፒዮና ላይና በዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ተሳትፋ አሸንፋለች።
በቶኪዮው ኦሊምፒክ ላይ በመቅረብ በኦሊምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ ትወዳደራለች።

ኤሪን ደቡብ አፍሪካን ወክላ በዘርፉ የምትወዳደር ብቸኛዋ አፍሪካዊት ስትሆን፤ ውድድሩ በቶኪዮው ኦሊምፒክ ውስጥ አዲስ ከተካተቱ ስፖርቶች መካከል አንዱ ነው።
ባለፈው ዓመት በአፍሪካ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ተሳትፋ አሸንፋለች።

ሄንሪ ሹማን የትራይትሎን [ዋና፣ ብስክሌት፣ ሩጫ] ተወዳዳሪ ሲሆን በኮመንዌልዝ ጨዋታዎች ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ለማሸነፍ ችሏል።
በሪዮ ኦሊምፒክ ላይም በዘርፉ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

ቦይፔሎ በዚህ የውድድር ዘርፍ ላይ በኦሊምፒክ የምትሳተፍ የመጀመሪያዋ ደቡብ አፍሪካዊት ስትሆን፤ በዚህ ኦሊምፒክ ላይ የምትሳተፍ በእድሜ ትንሿ አፍሪካዊትም ናት።

ብሊትዝቦክስ ተብሎ የሚታወቀው የደቡብ አፍሪካ የራግቢ ቡድን በሪዮው ኦሊምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።
ቀደም ሲልም በራግቢ የዓለም ዋንጫ የሁለተኛነት ደረጃን አግኝቷል።

ቱኒዚያዊው የረጅም ርቀት ዋናተኛ ኡሳማ ሜሉሊ ቤይጂንግ እና ለንደን ላይ በተካሄዱት የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።

ቱኒዚያዊቷ የነጻ ትግል ስፖርተኛ ማርዋ አምሪ በሪዮው ኦሊምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት በዘርፉ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ለመሆን በቅታለች።

ኢንስ ቡባክሪ በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ ለአገሯ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ጃኮብ ኪፕሊሞ ኡጋንዳዊ የረጀም ርቀት ሯጭ ሲሆን ባለፈው ዓመት በዳይመንድ ሊግ የ3000 ሜትር ውድድርን አጠናቋል።
ከሪዮ ውድድር በመቀጠል የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሁለተኛው የኦሊምፒክ ተሳትፎው ነው።

ኡጋንዳዊው ሯጭ ሮናልድ ሙሳጋላ በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ በ1500 ሜትር የወንዶች ውድድር ላይ ተወዳድሮ ነበር።
ከሁለት ዓመት በፊት ለንደንና ፓሪስ በተካሄዱ የዳይመንድ ሊግ ላይ በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል።

ጆሽዋ ኡጋንዳዊ የረጅም ርቀት ሯጭ ሲሆን በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘ ሲሆን ባለፈው ዓመት ሞናኮ ላይ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ በ5 ሺህ ሜትር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

ኡጋንዳዊቷ የመሰናክል ሯጭ ፔሩት ቺሙታይ ሪዮ ላይ በተካሄደው ኦሊምፒክ ተወዳድራ ነበር።
እንዲሁም በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ3000 ሜትር የመሰናክል ሩጫ ተወዳድራ አምስተኛ ወጥታለች።

የዛምቢያ ሴት እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ኮፐር ኩዊንስ ወይም ሺ-ፖሎፖሎ በሚል ቅጽል የሚጠሩ ሲሆን የቶኪዮው ኦሊምፒክ የመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፏቸው ነው።

ስኮት ቪንሰንት ቶኪዮ ላይ በሚደረገው ውድድር የመጀመሪያው የኦሊምፒክ ተሳትፎ ነው። የዚምባብዌ የጎልፍ ተወዳዳሪው ከሁለት ዓመት በፊት ጃፓን ውስጥ በተካሄደው ውድድር ላይ የአራተኛ ደረጃን አግኝቷል።

ዲ'ታይገርስ በመባል የሚታወቁት የናይጄሪያ ቅርጫት ኳስ ቡድን በቶኪዮው ኦሊምፒክ በመሳተፍ ብቸኛው የአፍሪካ ቡድን ነው።
ዲ'ታይገርስ በመባል የሚታወቁት የናይጄሪያ ቅርጫት ኳስ ቡድን በቶኪዮው ኦሊምፒክ በመሳተፍ ብቸኛው የአፍሪካ ቡድን ነው።
የአፍሪካ ሻምፒዮናዎቹ የናይጄሪያ ቅርጫት ኳስ ቡድን ዲ'ታይገርስ በቶኪዮው ኦሊምፒክ የአፍሪካ ብቸኛ ወኪል ናቸው።

ዘ ፐርልስ' በመባል የሚታወቁት የአንጎላ የሴት እጅ ኳስ ቡድን አባላት በዚህ ዓመት በተካሄደው የአፍሪካ ሴቶች የእጅ ኳስ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፈዋል።
በሪዮው ኦሊምፒክ ላይ ሩብ ፍጻሜ ደርሰው የነበሩት 'ዘ ፐርልስ' ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ሥነ ዘዴ
እነዚህ የአፍሪካ ስፖርተኞች የተለያዩ የአህጉሪቱን ክልሎች ይወክላሉ ተብለው ነው የቀረቡት። የተመረጡትም በኦሊምፒክ ተሳትፏቸው፣ ባገኙት ሜዳሊያ ብዛት እና ከሚወዳደሩበት የተለየ የስፖርት አይነት አንጻር ነው።
ተሳታፊዎች
የአርትኦት ዝግጅት፡ ንኬቺ ኦግቦና፣ ፕሪንሰስ አቡሜሬ እና ሙቶኒ ሙቺሪ። ዲዛይን፡ ኦላኒዬ አዴቢምፔ እና ሚሊሰንት ዋቺራ። የድረ ገጽ ዝግጅት፡ ፒዩሪቲ ቢሪር። ተጨማሪ፡ ሳሊ ሞራሌስ እና ሴሌስቲን ካሮኔይ
ምስሎች፡
ጌቲ ኢሜጅስ፣ የዓለም ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን፣ ኤኤፍፒ፣ ናይጄሪያን ኒውስ፣ የናይጄሪያ የውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን፣ መክሰብ ደበሳይ፣ የሞዛምቢክ የውሃ ቀዘፋ ቡድን፣ ጊያና ፋሩክ፣ ኢፒኤ፣ ፕሬስፎከስ/ኒውስ ፒክስ እና ፒኤ፣ ኤርዊዘርየት ትዊተር፣ ብሩስ ቫይን እና ኦሊምፒክ፣ ክላይምብ ዛምቢያ፣ ዲደብሊው እና የሞዛምቢክ ቡድን።