ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው ለውጦችና ከፊቷ የተደቀኑ ተግዳሮቶች

ደቡብ ኢትዮጵያ ጨንቻ ውስጥ ቅመማ ቅመም የሚሸጡ ሴቶች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አገሪቷ ብሔራዊ ምርጫን ለማካሄድ ቀናት ነው የቀሯት።

ቢቢሲ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም አገሪቷ ያለፈችባቸው መሰረታዊ ለውጦችንና የተደቀኑባትን ከፍተኛ ተግዳሮቶችን ዳስሷል።

Short presentational grey line
የሕዝብ ብዛት

በምርጫ የሚያሸንፈው ቀጣዩ መንግሥት በሕዝብ ብዛቷ በአፍሪካ ሁለተኛና በዓለም 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችውን የ115 ሚሊዮን ሕዝብ ባለቤትን ያስተዳድራል።

የአገሪቱን የሕህዝብ ቁጥርን በምናይበት ወቅት ከስልሳ ዓመት በፊት ከነበረው በአምስት እጥፍ የጨመረ ቢሆንም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ግን የሕዝብ ቁጥር እድገት በተወሰነ መልኩ መቀነስ አሳይቷል።

በአውሮፓውያኑ 2050 የአገሪቷ የሕዝብ ቁጥር ሦስት ሚሊዮን ጭማሪ ያሳያል ተብሎ የተተነበየ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን በሕዝብ ቁጥር ከዓለም ስምንተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል።

Short presentational grey line
ምጣኔ ሀብት

ኢትዮጵያ በዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ለውጥ ካሳዩ አገራት መካከል አንዷ ናት። የሕዝብ ቁጥር እድገቷም ከምጣኔ ሀብት መመንደግ ጋር መሳ ለመሳ ሄዷል።

ምንም እንኳን በአገሪቱ ውስጥ በአውሮፓውያኑ 2002 እና 2003 ድርቅ ተከስቶ የከፋ ሁኔታ ቢያጋጥምም ከዚያ በኋላ ግን የዜጎች አማካኝ ገቢ በ600 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ይህ ከፍተኛ ለውጥና ጭማሪ ግን በአገሪቷ በተመሳሳይ መልኩ አልተሰራጨም።

ለምሳሌ በመዲናዋ አዲስ አበባ እድገት ማለት የከተሜነት መስፋፋት እንዲሁም ቀላል ባቡር አገልግሎቶች የመሳሰሉ የመሰረተ ልማቶች መሻሻል የታየበት ነው።

ሌሎች የአገሪቷን ክፍሎች ብናይ አንዳንዶች ከምጣኔ ሀብት እድገቱ ተጠቃሚ እንዳልሆኑ የሚወቅሱ ያሉ ሲሆን ይህም ሁኔታ በአገሪቷ ውስጥ ለሚፈጠሩ ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች መቀጣጠል ምክንያትም ነበሩ።

Short presentational grey line
የህጻናት ሞት

በኢትዮጵያ ውስጥ የታየው ለውጥ በጤና ዘርፉም ላይ ይንጸባረቃል።

ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል።

ከህፃናት ሞት በተጨማሪ በወሊድ የሚሞቱ እናቶችም ቁጥር አሽቆልቁሏል።

Short presentational grey line
ብሔር

ኢትዮጵያ ከስልሳ በላይ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አገር ናት። በእነዚህ ብሔሮች መካከል ያለውም ግንኙነት የአገሪቷን መፃኢ እጣ ፈንታ ወሳኝ ነው።

በኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ትልቁ ብሔር ኦሮሞ ለረዥም ዘመናት ከአገሪቱ ምጣኔ ሀብትም ሆነ ፖለቲካዊ መድረኮች እንድንገለል ተደርገናል በማለትም ይወቅሳሉ።

ከአምስት ዓመት በፊትም አገሪቷን ያናወጡ ተቃውሞዎች ከኦሮሞ ብሔር ለመጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት መንገድ ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በብሔር በተከፋፈለችው አገር ብሔራዊ አንድነት ማምጣት ዋነኛ ፍላጎታቸው ነበር። በዚህ አንድነትም ውስጥ በልዩነቶች መድመቅ ይቻላል የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርብ ያጋጠሙ ፈተናዎች ለዚህ ራዕያቸው አደጋ ሆነው ተጋርጠዋል።

Short presentational grey line
ክልሎች
1px transparent line

ኢትዮጵያ የብሔር ፌደራሊዝም ሥርዓትን የምትከተል ሲሆን በአስር ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ተዋቅራለች።

በሕገ መንግሥቱም መሰረት ብሔሮች የራሳቸውን ክልል መመስረት እንፈልጋለን ካሉ በሕዝበ ውሳኔ መሰረት የሚወሰን ይሆናል።

ሲዳማ በሕዝበ ውሳኔው መሰረት ክልል የሆነችው ባለፈው ዓመት ሲሆን በደቡብ ምዕራብም 11ኛ ክልል ለመመስረት ጳጉሜ 1/2013 ዓ.ም ሕዝበ ውሳኔ ይደረጋል።

የፌደራሊዝም ሥርዓቱ በዋነኝነት የተዋቀረው ለዘመናት የቆውን ጠንካራ የማዕከላዊው መንግሥትን ቁጥጥር በማስቀረት ክልሎች ሰፋ ያለ ሥልጣን እንዲኖራቸውና በፌደራል መንግሥቱና በክልሎች መካከል ሚዛናዊ ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ነው።

ነገር ግን በማዕከላዊ መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል የነበረው ግንኙነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መጥቶ ከሰባት ወራት በፊት ጦርነት ተቀስቅሷል።

ይህም በተወሰነ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አገሪቷን ወደ አሃዳዊ ሥርዓት ለመመለስ ይሞከራሉ በሚልም ነበር መሻከሮች የተከሰቱት።

Short presentational grey line
ትግራይ ክልል
1px transparent line

በትግራይ ክልል የቀጠለው ውጊያ ሰብዓዊ ቀውሶችን አስከትሏል። በዚህም ከ60 ሺህ በላይ የክልሉ ነዋሪዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት በአገር ውስጥ ለመፈናቀል ተገደዋል።

በክልሉ ውስጥ ሰላማዊ ዜጎች የተጨፈጨፉ ሲሆን እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በቅርቡ በነበረ የምግብ ሁኔታ ግምገማ ከ350 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የረሃብ ቋፍ ላይ መሆናቸውን አንድ ሪፖርት አመላክቷል።

የፌደራል መንግሥቱ በህወሓት ይመራ የነበረውን አስተዳደር በጊዜያዊ የክልል አስተዳደር ተክቷል። አሁንም ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ ምርጫ አይካሄድም።

ጦርነቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ብሔራዊ አንድነትን ለመፍጠር የያዙትን ራዕይ ላይ ችግር ፈጥሯል።

Short presentational grey line
ግጭት
1px transparent line

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችም እንዲሁ ግጭቶች ተከስተዋል።

በአገሪቱ የብሔር ግጭቶች በአንዳንድ ቦታዎች ከመሬት ይገባኛልና የድንበር ጉዳዮች ጋርም የተያያዙ ናቸው።

ከጥቂት ወራት በፊት በኦሮሞና በአማራ መካከል ያለውን የብሔር ግጭትም ለማስቆም መንግሥት በተወሰነው የአማራ ክልል አስቸኳይ አዋጅ ደንግጓል።

በቅርብ ወራትም በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ከድንበር ጋር በተያያዘ በተከሰተ ግጭት የ100 ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲሁ በርካታ ጥቃቶች ይፈፀማሉ። በታኅሣሥ ወር ከነበረ ጥቃት የተረፉ ሰዎች እንደሚናገሩት የጉሙዝ ተወላጆች ሌሎች ብሔሮችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እንደፈፀሙ ነው።

መንግሥት እነዚህን ጥቃቶች ለማስቆም በተደጋጋሚ የፌደራል ሠራዊቱን በበርካታ ቦታዎች አሰማርቷል።

ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምርጫውን ካሸነፉ ያሉትን ግጭቶች ለማስቆምና መረጋጋት ለማምጣት በርካታ ሥራ ይጠብቃቸዋል።