በልብስዎ ቀለም እና በጣትዎ የ’V’ ምልክት በማሳየትዎ የሚታሰሩባት ቤላሩስ

ቀይ ጫማ ያደረገ እግር

የፎቶው ባለመብት, TUT.BY

የቤላሩስ ባለሥልጣናት የተቃዋሚዎችን ቀይ እና ነጭ ባንዲራ የሚውለበለቡትን ብቻ ሳይሆን በእነዚህን ቀለሞች የተሠሩ ካልሲዎችን ያደረጉትንም ሰዎችን እየቀጡ ነው፡፡

ወደ መንጃ ፈቃድ ትምህርት ቤት የምታቀና አንዲት ሴት በዋና ከተማዋ ሚኒስክ ውስጥ በአራት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡ ያልተፈቀደ ልብስ ለብሰሻል በሚል መያዟ ተነገራት፡፡

ምክንያቱ ምን ይሆን? የተከለከለውን ባንዲራ የሚመስል በቀይ መስመሮች ያሉት ነጭ ካልሲዎችን በልበሷ ነበር፡፡

የድል ምልክት የሆነውን የ'V' ምልክት ለሚያልፉ ተሽከርካሪዎች አሳይተሻል ተብላለች። ተመሳሳይ ምላሽ የሰጧት አሽከርካሪዎችም ከባድ የገንዘብ ቅጣት ተላለፈባቸው።

ቀይ መስመር ያለው ነጭ ባንዲራ በ20 ኛው ክፍለዘመን የቤላሩስ ብሔረተኞች ባንዲራ ሆኖ ለአጭር ጊዜ አገልግሏል፡፡

በኋላም የሶቪዬት ኮሚኒስቶች መዶሻ እና ማጭድ ባለው በቀይ እና አረንጓዴ ባንዲራ ተክተውታል፡፡ ባንዲራው በድጋሚ በፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሽንኮ እአአ በ 1995 እንደገና ተዋወቀ። በዚህ ጊዝ ግን ከኮሚኒስት ውድቀት በኋላ በመሆኑ መዶሻውን እና ማጭዱን ቀንሶ ነበር የቀረበው፡፡

ናታሊያ ሲቮቶቫ-ሴዱሽኪና 2,320 906 ዶላር እንድትቀጣ ተፈረደባት ፡፡

ያልተፈቀዱ የተቃውሞ ሰልፎችን በሚከለክሉ ህጎች መሰረት ነው ክስ ተመሰረተባት፡፡ በወቅቱ አጭር ጂንስ በመልበሷ የተከሰሰችበትን ካልሲዎችና ቀይ ቱታ በቀላሉ የሚታዩ ነበሩ፡፡

ካልሲዎቹን የገዛችበት የበይነመረብ ሱቅ ተመሳሳይ ቀለም ያለው ምርት መሸጥ ቢያቆምም ተመሳሳይ ነጭ ካልሲዎችን በጥቁር መስመር እየሸጠ ይገኛል።

ሲቮቶቫ-ሴዱሽኪና በረንዳዋን በቀይ እና በነጭ ሪባን በማስጌጧ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባታል፡፡

ባለፈው ዓመት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ወደ ሚንስክ አደባባዮች ወጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ ሉካሼንኮ በነሐሴ ወር በተካሄደው ምርጫ አጭበርብረው በድጋሚ ተመረጥኩ ማለታቸው ነበር ሰልኞቹን ያስቆጣው፡፡

ሰልፎቹን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስና ሃይል ተጠቅሞ በሺህዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ አስሯል፡፡ ብዙ የፖሊስ የጭካኔ እርምጃዎች የተሰነዱ ሲሆን ሉካሼንኮ ከሩሲያ ውጭ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተገልለዋል፡፡

ዋናዎቹ የተቃዋሚ መሪዎች በስደትም ሆነ በእስር ቤት ያሉ ተቃዋሚ መንግሥታት ተቃዋሚዎች በአብዛኛው ሞተዋል፡፡

በዚህ አመት ከ 2700 በላይ ሰዎች በፀረ-ሉካሼንኮ እንቅስቃሴ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

በሌሎች ፀረ-ተቃዋሚ ክሶች፡

* በሞጊሌቭ ነዋሪ የሆኑት ማሪያ ቮይኖቫ ፊርማዋ የ"ፅንፈኛውን" መፈክር እንዲመስል አድርገዋል በሚል 115 ዶላር ተቀጥታለች፡፡

* በተመሳሳይ በሞጊሊቭ ኦልጋ ክሊምኮቫ እና ሰርጌይ ስኮክ አሌክሳንደር ሉካሼንኮን በመሳደብ ጥፋተኛ ተብለው የሦስት ዓመት እስር ተላልፎባቸዋል ክሊምኮቫ እና ስኮክ በሚንስክ ውስጥ በፍርድ ሂደት ላይ

* አንድሬ ፓርኮሜንኮ በረንዳ ላይ በቀይ እና በነጭ ያስቀመጠው "የወረቀት ባነር" ተቃዋሚዎችን ይደግፋል በሚል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ግለሰቡ ቀለሞቹ አዲስ ቤት ሲቀየር ቴሌቪዥን ያመጣበት ካርቶን ቀለም መሆኑን እና በቅርቡ ወደ ቤቱ ስለገባ እንዳላስወገደው አስታውቋል፡፡

* ዩሊያ ያኩቦቪች በሚንስክ ውስጥ የፖለቲካ ሃሳብ ለማስተላለፍ መንገድ ዘግታለች በሚል ሁለት ዓመት ተፈርዶባታል፡፡ መንገዱ የተዘጋው ቀይ መብራት በመብራቱ ነው ስትል አስተባብላለች፡፡