ትግራይ ፡ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ዶ/ር ሙሉ ነጋ

የፎቶው ባለመብት, ETIOTUBE

የምስሉ መግለጫ, ዶ/ር ሙሉ ነጋ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና በሚኒስትሮች ምክር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደርን በተመለከተ በወጣው ደንብ መሰረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንደተሾሙ አመልክተዋል።

በዚህም መሠረት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በክልሉ በሕጋዊነት ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የክልሉን መንግሥት ሥራ አስፈጻሚ መዋቅሮች የሚመሩ ኃላፊዎችን መልምለው ይሾማሉ ብለዋል።

ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ከሚያዚያ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተሹመው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ከዚህ ቀደምም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በሥራ ኃላፊነት ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በፌደራል መንግሥቱና አሁን ክልሉን እያስተዳደረ ባለው ህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ወታደራዊ ግጭት መሸጋገሩን ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ የትግራይ ክልልን በተመለከተ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወሳል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

በዚህም መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በክልሉ ላይ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ከደነገገ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

ይህንንም ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባና ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወስኗል።

በወቅቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል በክልሉ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ የፌዴራሉን ሰላምና ጸጥታ ማናጋት ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊት በመፈጸሙ ሕገ መንግሥቱን ማስከበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ነበር።

አሁን ወደ ጦርነት የተሸጋገረው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መስተዳደር በኩል የነበረው ቅራኔ እየተባባሰ የመጣው ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደማይካሄድ ከታወቀ በኋላ በትግራይ የተናጠል ምርጫ በመደረጉ ሳቢያ ነው።

ይህንንም ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫውን ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ መወሰኑን ተከትሎ ማዕከላዊው መንግሥት ከክልሉ መስተዳደር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያካሂድና የበጀት ድጋፍ እንዳይሰጥ ከወሰነ በኋላ ነገሮች እየተካረሩ መሄዳቸው ይታወሳል።

ይህ ጦርነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው እስካሁን የደረሰው የጉዳት መጠን በይፋ ያልተነገረለት ጥቃት በትግራይ ልዩ ኃይል በሰሜን ዕዝ ላይ መፈጸሙን ከገለጹ በኋላ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ነው።

ይህንንም ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገ ሲሆን የተወካዮች ምክር ቤትም ውሳኔውን ተቀብሎ ማጽደቁ ይታወሳል።

በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ውስጥ ጣልቃ እንዲገባና ክልሉን የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወስኗል።