የቡሩንዲው ፕሬዝዳት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በድንገት አረፉ

ቡሩንዲ ፕሬዝደንት

የፎቶው ባለመብት, AFP

የቡሩንዲወ ፕሬዝደንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ከሳምንታት በፊት በተደረገ ምርጫ ፓርቲያቸው ማሸነፉ የተነገረላቸው የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ በድንገት ነው ህይወታቸው ያለፈው።

የቡሩንዲ መንግሥት እንዳስታወቀው የፕሬዝደንት ኑኩሩንዚዛ ህይወት ያለፈው "በልብ ድካም" ነው ሲል ከአገሪቱ መንግሥት ስለፕሬዝዳንቱ ሞት የወጣው መግለጫ አመልክጠወል።

የ55 ዓመቱ ንኩሩንዚዛ ባሳለፍነው ቅዳሜ ጤንነት ስላልተሰማቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ተደርገው ጤናቸው መሻሻል አሳእቶ ነበር።

ነገር ግን ሰኞ ዕለት የልብ ችግር እንደገጠማቸውና ነፍሳቸውን ለማትረፍ ጥረት ተደርጎ ሳይሳካ በመቅረቱ ማረፋቸው ተገልጿል።

ንኩሩንዚዛ ለ15 ዓመታት ቡሩንዲን በፕሬዝዳንትንት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ነሐሴ አጋማሽ ላይ መንበራቸውን በእሳቸው ይሁንታ ለፕሬዝዳናትነት ቀርበው ለተመረጡት አጋራቸው ያስረክባሉ ተብሎ ነበር።

እአአ ከ2005 ጀምሮ ቡሩንዲን የመሩት ንኩሩንዚዛ በቅርቡ በተደረገው ምርጫ እንደማይሳተፉ አሳታውቀው የፓርቲያቸው አባል እና እርሳቸው የመረጡት እጩ ምርጫውን ካሸነፈ በኋላ፤ በቡሩንዲ ፖለቲካ ውስጥ ቁልፍ ሚና ይዘው ይቆያሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ከሳምንታት በፊት በተካሄደው ምርጫ ኢቫሪስቴ ዳየሺሚዬ 68 በመቶ ድምጽ በማግኘት ፕሬዝደንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸው ታውጇል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ አዲስ ለተመረጡት ፕሬዝደንት ነሐሴ 14 ሰልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ነበር።

ንኩሩንዚዛ ለ15 ዓመታት በስልጣን ላይ ሲቆዩ በየአምስት ዓመቱ በሚካሄዱ ሦስት ምርጫዎች ላይ ተሳትፈዋ። ከአምስት ዓመታት በፊት በተካሄደው ምርጫ ላይ ንኩሩንዚዛ እንደሚሳተፉ ከሳወቁ በኋላ በቡሩንዲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር።

በዚህም ሳቢያ ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ 1200 ሰዎች መሞታቸው እና ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉት ደግሞ ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸው ይነገራል።