ወጣቶቹ ሴቶች ከመኪና መለዋወጫ ለኮቪድ-19 ህሙማን መተንፈሻ ሰሩ

ወጣቶቹ

አፍጋኒስታን ውስጥ ያለ አንድ ወጣት ሴቶች ብቻ ያሉበት ቡድን የመኪና መለዋወጫዎችን በመጠቀም በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ለመርዳት የሚያገለግለውን የመተንፈሻ መሳሪያ [ቬንትሌተር] እየሰሩ ነው።

አሳሳቢ እየሆነ የመጣው ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማከም ጥቅም ላይ የሚውለውን የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ሰርተው የሚጨርሱ ሲሆን ዋጋም በጣም ዝቅተኛ ነው።

ለዓመታት በጦርነት ስር የነበረችውና አርባ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት አፍጋኒስታን 400 ቬንትሌተር ብቻ ነው ያላት።

እስካሁንም በአገሪቱ ከ7,650 በላይ የኮሮናቫይረስ ህሙማን የተመዘገቡ ሲሆን 178 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሞተዋል። የአገሪቱ ባላስልጣንት ወረርሽኙ ሊከፋና ደካማውን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት ሊያሸዕመደምደው ይችላል ብለው ሰግተዋል።

"በምንሰራው የመተንፈሻ መሳሪያ አንድ ሰው እንኳን ማዳን ከቻልን ትልቅ ነገር ነው" ስትል የቡድኑ አንድ አባል የሆነችው የ17 ዓመቷ ናሂድ ራሂሚ ለቢቢሲ ተናግራለች።

"የአፍጋኒስታን ባለህልሞች" በሚል ስም የሚጠሩት ወጣት ሴቶቹ የሚገኙት በአገሪቱ ውስጥ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ በሽተኛ በተገኘባት የሄራት ክፍለ ሃገር ውስጥ ነው።

ክፍለ ሃገሯ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተመታችው ኢራን ጋር የምትዋሰን በመሆኗ በአፍጋኒስታትን ከፍተኛ የወረርሽኙ ስጋት ያለባት ናት።

ወጣት ሴቶቹ እድሜያቸው በ14 እና 17 ውስጥ ሲሆን የመጀመሪያውን የሙከራ ምርታቸውን የሰሩት የቶዮታ ኮሮላ ሞተርንና ሌላ ክፍል ደግሞ ከሆንዳ ሞተርሳይክል ላይ በመውሰድ ነው።

ወጣቶቹ ሴቶች

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ወጣቶቹ እንደሚሉት የሚሰሩት ቬንትሌተር መደበኛው የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በማይገኝባቸው ሆስፒታሎች ውስጥ ለሚገኙ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ጊዚያዊ መፍትሔ ይሰጣል ብለው ያምናሉ።

በወረርሽኙ ሳቢያ በዓለም ላይ በተፈጠረው ከፍተኛ የቬንትሌተር ፍላጎት ምክንያት የመሳሪያው እጥረት አጋጥሟል። በዚህ የተነሳም 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያወጣ የነበረው መሳሪያ አሁን ወደ 50 ሺህ ዶላር ከፍ በማለቱ ከአብዛኞቹ ድሃ አገራት አቅም በላይ ሆነወል።

ነገር ግን ህሙማንን ለመርዳት ቀን ከሌት የሚጥሩትን የህክምና ባለሙያዎችን ለማገዝ እየጣሩ እንደሆነ የሚናገሩት ወጣቶቹ፤ የሚሰሩት ቬንትሌተር ዋጋው 600 መቶ ዶላር በታች ነው።

ታዳጊ ሴቶቹ እንደሚሉት በበሽታው ምክንያት መደብሮች ዝግ በመሆናቸው ለሚሰሯቸው ቬንትሌተሮች የሚያስፈልጉ እቃዎችን ለማግኘት ችግር ገጥሟቸዋል።

የቡድኑ መስራችና ከዚህ ቀደም በታይም መ፥ጽሔት ተጽዕኖ ፈጣሪ ተብለው ከተመረጡ አንድ መቶ ሥራ ፈጣሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው ሮያ ማህቡብ እንደመትለው የሰሯቸውን ቬንትሌተሮች በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ለአገልግሎት ያቀርባሉ።

"የቬንትሌተሮቹ የመጀመሪያ ደረጃ ምርት ከቀናት በፊት ሆስፒታል ውስጥ ተሞክሯል። ቡድኑ በሁለተኛው የምርት ደረጃ ላይ እየሰራ ነው። ይህ ካለቀ በኋላ ምርቶቹ ለገበያ ይቀርባሉ" ብላለች።

ከሰላሳ ከመቶ በታች ሴቶች የትምህርት ዕድል ያገኙ ሴቶች ብቻ ባሉባት በአፍጋኒስታን ውስጥ የወጣቶቹ ሥራ ሴቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ በማሳየት ሌሎችን የማነቃቃት ዓላመ አለው።

የወጣቶቹ ሥራ በአፍጋኒስታን መንግሥት ተቀባይነትን በማግኘት ድጋፍ ያገኘ ሲሆን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒም ባለስልጣናት ሥራውን እንዲከታተሉና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲሰጣቸው በማዘዛቸው ለቡድኑ አባለት ትልቅ መነቃቃትን ስጥተወል።

የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴርም ለወጣት ሴቶቹ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑም ተነግሯል።

የሚሚስቴር መስራያ ቤቱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ወጣቶቹ የሚያመርቱት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ አስፈላጊውን ሳይንሳዊ የመርት ሂደትና ፍተሻ እንዲያልፍ ተደርጎ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል።

ኮሮና
Banner