ኮሮናቫይረስ የአውሮፕላን ጉዞን ይለውጠዋል ተባለ፤ በምን መልኩ?

ከአገር አገር የሚደረግ ሽርሽር በእጅጉ ይቀንሳል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከአገር አገር የሚደረግ ሽርሽር በእጅጉ ይቀንሳል

ተጓዦች ከጉዞ በፊት የደም ምርመራ እንዲያደርጉ ማስገደድ፤ በአየር ማረፊያዎች ሰዎች ሊጠጋጉ የሚችሉባቸውን ስፍራዎች በመስታውት መከፋፈል አልያም ከበረራ በፊት ሰዎች በሳኒታይዘር እጆቻቸውን እንዲያጸዱ ማድረግ ገፍተው የሄዱ እርምጃዎች ሊመስሉ ይችላሉ።

ይሁን እንጂ ቀላል የማይባሉ አየር መንገዶች ተጓዦች ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ እያደረጉ እንደሆነ እንዲሰማቸው ለማድረግ ለመተግበር እያሰቡት ያሉ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች ናቸው።

ምንም እንኳ በመላው ዓለም ከአገልግሎት ውጪ ቆመው የሚገኙት የመንገደኖች ማመላለሻ አውሮፕላኖች መቼ በረራ ማድረግ እንደሚጀምሩ ባናውቅም፤ ከኮረናቫይረስ ስርጭት በኋላ የሚኖረው ከአንድ አገር ወደ ሌላ የሚደረገው ጉዞ ምን መልክ እንደሚኖረው መገመት ይቻላል።

Short presentational grey line

በአየር ማረፊያዎች

ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በአየር መንደኞች ውስጥ 'ማኅብራዊ ርቀትን መጠበቅ' የሚለው የትንቃቄ እርምጃ መቀጠሉ አይቀርም። በፍተሻ ቦታዎችም ሆነ የጉዞ ቅድም ሁኔታዎችን ሲያሟሉ [ቼክ ኢን ሲያደርጉ] ከ1-2 ሜትር ርቀት መጠበቅ ግድ ይሆናል።

በአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ አንዳንድ አየር ማረፊያዎች ከዚህ በተጨማሪ፤ ተጓዦች እጆቻቸውን ለ20 ሰከንድ በሳሙና እንዲታጠቡ እና በሳኒታይዘር እንዲያጸዱ እያደረጉ ይገኛሉ።

የሆንግ ኮንግ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊ ሙሉ የሰውንት ክፍል ከጽረ-ተዋሲያንስ የሚያጸዳ ማሽን አስተክሏል። ማሽኑ ጸረ-ተዋሲያንን በመርጨት በ40 ሰከንድ ውስጥ በሰውነት እና ልብስ ላይ ያሉ ቫይረሶችን እና ባክቴሪያዎችን ይገድላል ተብሏል።

ሙሉ የሰውንት ክፍል ከጽረ-ተዋሲያንስ የሚያጸዳ ማሽን በሆንግ ኮንግ አየር ማረፊ

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, ሙሉ የሰውንት ክፍል ከጽረ-ተዋሲያንስ የሚያጸዳ ማሽን በሆንግ ኮንግ አየር ማረፊ

ከዚህ በተጨማሪም አየር ማረፊያው በጨረር አማካኝነት ቫይረሶችን እየተዘዋወረ የሚገድል ሮቦት በሥራ ላይ አንደሚያውል አስታውቋል።

ሌሎች አየር ማረፊያዎች ደግሞ የሰውነት ሙቀት ልኬት ለሁሉም ተጓዦች ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ኢሚሬትስ አየር መንገድ ደገሞ ተጓዦች ከዱባይ ከመሳፈራቸው በፊት በደም ናሙና ውስጥ ኮቪድ-19 መኖር አለመኖሩን በ10 ደቂቃ ውስጥ ውጤት የሚለይ መሳሪያ ያድላል።

Short presentational grey line

አውሮፕላን ውስጥ

ወደ አውሮፕላን ዘልቀው ሲገቡ የለመዱትን የበረራ አስተናጋጆች ፈገግታን ላትመለከቱ ትችላላችሁ። ምክንያቱም የበረራ አስተናጋጆቹ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ስለሚያጠልቁ።

ምናልባት እርሰዎም የመረጡት አየር መንገድ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሊሆን ይችላል።

አየር መንገዶች ተጓዦች ከመሳፈራቸው በፈት የመመገቢያ ጠረጴዛዎች፣ የእቃ መጫኛ ሰንዱቆችን፣ መጸዳጃ ቤቶች እና መቀመጫ ወንበሮችን በጸረ-ተህዋሲያን እንዲጸዱ ይደረጋሉ።

ከኮሮናቫይረስ በኋላም አንዳንድ አየር መንገዶች ጠበቅ ያለ ርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል። በኮሪያ አየር መንገድ ቢሳፈሩ ሙሉ ጋዋን፣ ጓንት እና የፊት ጭንብል ያደረጉ የበረራ አስተናጋጆች በረራዎች ምቹ እና ቀላል ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ ይመለከታሉ።

ከኮሮናቫይረስ በኋላ በሚኖሩት ጥቂት ወራት የአየር መንገድ ቲኬቶች ዋጋ የሚቀመሱ አይሆንም እየተባለ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ማኅበራዊ ርቀትን ለመጠበቅ ሲባል በመንገደኖች መካከል አንድ ክፍት ወንበር ስለሚተው ነው። የዚህን ወጪ ለማካካስ ደግሞ አየር መንዶች የቲኬት ዋጋዎች ላይ ማስተካከያ ስለሚያደርጉ ነው።

Short presentational grey line

ሌላ ምን አዲስ ነገር ይፈጠር ይሆን?

ከኮሮናቫይረስ ዘመን በኋላ ለጉዞ ሻንጣቸውን የሚሸክፉ ሰዎች ቁጥር እንደሚቀንስ ይጠበቃል። ለዚህም 'ለቫይረሱ ተጋላጭ ልሆን እችላለሁ' ከሚለው ስጋት በተጨማሪ ሌሎች ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበራ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት ከተሳተፉ ሰዎች 60 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሌላ አገር ለሽርሽርም ሆነ ለሥራ የምጓዘው የኮሮናቫይረስ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ከሁለት ወራት በኋላ ነው ብለዋል።

ቦይንግ እንደሚለው ከሆነ አየር መንገዶችም ወደተለመደው የበረራ አገልግሎት በቀርቡ አይመለሱም። የኮሮናቫይረስ ተጽእኖም በኢንዱስትሪው ላይ እስከ 2023 ይዘልቃል።

ኮሮና
Banner