ኮሮናቫይረስ፡ የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለባቸው አገራት ያሉ ሙስሊሞች ረመዳንን እንዴት እያሳለፉ ነው?

በኔፓል፤ ካትማንዱ በወረርሽኙ ሳቢያ መንግሥት የጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ተከትሎ አንድ ሙስሊም በረመዳን የመጀመሪያው ቀን ብቻውን ሰግዷል።

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, በኔፓል፤ ካትማንዱ በወረርሽኙ ሳቢያ መንግሥት የጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ተከትሎ አንድ ሙስሊም በረመዳን የመጀመሪያው ቀን ብቻውን ሰግዷል።

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት ያሳለፉትን እርምጃዎች ተከትሎ መስጊዶች በመዘጋታቸውና መሰባሰብ በመከልከሉ ምክንያት በዓለም ላይ ያሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ዘንድሮ ረመዳንን በተለየ መንገድ እያሳለፉ ነው።

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው የረመዳን ወር፤ 1.8 ቢሊየን የዓለማችን ህዝቦች ጎህ ሲቀድ ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከሲጋራ እንዲሁም ከግብረ ስጋ ግንኙነት የሚታቀቡበት ነው።

በዚህ ወቅት ቤተሰብና ወዳጆች ሰብሰብ ብለው ማፍጠር፣ በሕብረት ማምለክና መስገድ የተለመደ ነው።

ይሁን እንጅ በዚህ ዓመት ይህንን የተቀደሰ የፆም ወር ብቻቸውን በቤታቸው እንዲያሳልፉ ተገደዋል።

በእየሩሳሌም የሚገኘው አል አቅሳ መስጊድ ግቢ ከባለፈው ወር አጋማሽ ጀምሮ ተዘግቷል፤ ለረመዳንም አይከፈትም። የእስልምና ቅዱስ ከተማ ተብላ የምትጠራዋ የሳዑዲ አረቢያዋ መካም በቫይረሱ ተጠቅታለች። ለመሆኑ ረመዳን በተለያዩ አገራት እንዴት እያለፈ ነው?

በመካ የሚገኘው ታላቁ መስጊድ በረመዳን ወቅት በአማኞች ይሞላ ነበር፤ አሁን ግን ባዶውን ቀርቷል።

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, በመካ የሚገኘው ታላቁ መስጊድ በረመዳን ወቅት በአማኞች ይሞላ ነበር፤ አሁን ግን ባዶውን ቀርቷል።
በኒዮርክ፤ አንድ ኢማም አዛን ለማድረግ ወደ መስጊዱ ሲገቡ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በኒው ዮርክ፤ እኝህ ኢማም በባዶ መስጊድ ውስጥ ብቻቸውን አዛን አድርገዋል።
በፓኪስታን ላሆር ደንበኞች ምግብ ለመግዛት ርቀታቸውን ጠብቀው ሲጠባበቁ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, በፓኪስታን ላሆር ደንበኞች ለማፍጠሪያ የሚሆኑ ምግቦችን ለመግዛት ርቀታቸውን ጠብቀዋል።
ወና በሆነው የጃማ መስጊድ ደጅ ላይ አንድ ግለሰብ ሲያፈጥሩ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በህንድ የእንቅስቃሴ ገደቡን ተከትሎ በተዘጋው የደልሂ ጃማ መስጊድ ደጅ አንድ ግለሰብ ብቻቸውን ቁጭ ብለው አፍጥረዋል።
ሙስሊም ሴት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲሁም ጓንት አድርጋ ስትሰግድ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በእየሩሳሌም የሚገኙ ሙስሊሞች የጁመዓን ሶላት ጎዳና ላይ ሰግደዋል።
ኮሮና