ደቡብ አፍሪካዊው 32 ሴቶችን በመድፈር 32 የተለያየ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት 32 ሴቶችን አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰው ደቡብ አፍሪካዊ 32 የተለያየ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።
"ደርባን የፍጥነት መንገድ ላይ የሚደፍረው ግለሰብ" በሚል ስም የሚጠራው ግለሰቡ፤ ሥራ አጥ ሴቶችን 'ሥራ አገኝላችኋለሁ' በሚል ማታለያ በመቅረብ ጥቃት እንደፈጸመባቸው የፒንታውን ማጊስትሬት ፍርድ ቤት አስታውቋል።
ሞሰስ ማቪላ የተባለው ግለሰብ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ሲፈረድ ፍርድ ቤት ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፤ 'እጅግ አስቀያሚ ነህ' ብለው የሰደቡትም ነበሩ።
በፍርድ ቤቱ፤ "አንተ ያለርህራሄ ይህንን ሁሉ በደል ከፈጸምክ በኋላ ፍርድ ቤቱ እንዲምርህ አትጠብቅ" ተብሏል።
ከእድሜ ልክ እስራቱ በተጨማሪ ሁለት ሴቶችን ለመድፈር በመሞከሩ 20 ዓመትና በስርቆት የ15 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
ካሪንዳ ጃግሞሀን የተባለች ጋዜጠኛ በግለሰቡ ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች ጥቂቱ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹ የሚያሳይ ቪድዮ ትዊት አድርጋለች።












