ማንነታቸው ያልታወቀ 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ

ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ።

ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለፁት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት የታጠቁ ወታደሮች ተልዕኮና ማንነታቸው ባይታወቅም ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ አመልክተዋል።

ከሁለት ቀናት በፊት ከሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የተጠረጠረው አንቶኖቭ አውሮፕላንና አሳፍሯቸው የነበሩት 40 የታጠቁ ወታደሮች በመቀሌው የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መያዛቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የክልሉ ባለስልጣን በአካባቢው ለሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ገልፀዋል።

ምንጮቹ ጨምረው ወታደሮቹ አንቶኖቭ ተብሎ በሚታወቀው ግዙፍ አውሮፕላን በአሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ በድንገት ያረፉት በስህተት መሆኑን ገልፀው፤ የክልሉ ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረው እንደሚገኝ ተናግረዋል።