ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የኢሬቻ አከባበር በምሥል
የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።
የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን፣ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር መቆየቱን የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፤ በቢሾፍቱ ከተማ ደግሞ የሆራ ሃር-ሰዲ በዓላት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በታደመበት ይከበራሉ።
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን መገባደድ ተከትሎ ለፈጣሪ ምሥጋና የሚያቀርብበት እንዲሁም መጪው ዘመን በጎ እንዲሆን ፈጣሪን የሚለምንበት ነው።
ዛሬ በአዲስ አበባ እየተከበረ ያለውን የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በምሥል እንደሚከተለው አጠናቅረናል።