ስለ2025ቱ የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዋንጫ እስካሁን ምን እናውቃለን?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images/Backpage Pix
የ2025ቱ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ (ዋፍኮን) ከጥቂት ቀናት በኋላ ይጀመራል።
ውድድሩን ሞሮኮ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ ታስተናግዳለች።
በውድድሮች መደራረብ ምክንያት ለአንድ ዓመት ተገፍቶ የሚጀመረው ውድድር በአዘጋጇ እና በዛምቢያ መካከል ራባት በሚገኘው ኦሊምፒክ ስታዲየም በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ በይፋ ይከፈታል።
ውድድሩን ዘጠኝ ጊዜ በማሸነፍ ክብረወሰኑን የያዘችው ናይጄሪያ በምድብ ሁለት ከቱኒዝያ ትጫወታለች።
ያለፈው ውድድር አሸናፊዋ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ሰኞ ዕለት ጋናን ትገጥማለች።
ሌሎቹ ጨዋታዎችስ መቼ ይከናወናሉ? ውድድሩ በምን መልኩ ይከናወናል? ጨዋታዎቹስ የት ይከናዋናሉ?
ቢቢሲ ስለ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ዝርዝር መረጃውን እንደሚከተለው ያቀርባል።
ምድቦቹ ምን ይመስላሉ?
12ቱ ብሔራዊ ቡድኖች አራት ቡድኖችን በያዙ ሦስት ምድቦች ተደልድለዋል።
በምድብ አንድ ያለችው አዘጋጇ ሞሮኮ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ይጠብቋታል።
ለ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ማጣሪያ ያሸነፈቻት ዛምቢያ በዚሁ ምድብ ትገኛለች።
የአትላስ አናብስቱ ሴኔጋል እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎንም ያስተናግዳሉ።
በሌላ በኩል ናይጄሪያ ጥሩ የሚባል ምድብ ውስጥ ተደልድላለች። ብድኗ ከአፍሪካ አንደኛ ስትቀመጥ ከዓለም ደግሞ 36ኛ ደረጃን ይዛለች።
በዚህ ምድብ ውስጥ ቱኒዝያ፣ አልጄሪያ እና ቦትስዋና ተመድበዋል።
በምድብ ሦስት ደግሞ ያለፈው ውድድር አሸናፊዋ ደቡብ አፍሪካ እአአ ከ2018 በኋላ ወደ ውድድሩ ከተመለሱት ከጋና እና ከማሊ ጋር ተደልድላለች።
ለሁተኛ ጊዜ በውድድሩ የምትሳተፈው ታንዛኒያም በዚሁ ምድብ ውስጥ ትገኛለች።
ከምድባቸው አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡት ቡድኖች በቀጥታ ሲያልፉ ጥሩ ሦስተኛ የሆኑ ሁለት ቡድኖችም ሩብ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ።
ምድብ 1፡ ሞሮኮ፣ ዛምቢያ፣ ሴኔጋል፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
ምድብ 2፡ ናይጄሪያ፣ ቱኒዝያ፣ አልጄሪያ፣ ቦትስዋና
ምድብ 3፡ ደቡብ አፍሪካ፣ ጋና፣ ማሊ፣ ታንዛንያ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ከመክፈቻው ቀን በኋላ የምድብ ጨዋታዎች እስኪጠናቀቁ በየቀኑ ቢያንስ ሁለት ጨዋታዎች እንዲከናወኑ መርሃ ግብር ተይዞላቸዋል።
የምድብ ጨዋታዎቹ ቀን 10፡00 ሰዓት፣ ምሽት 1፡00 ሰዓት እና ምሽት 4፡00 ሰዓት ይከናወናሉ።
የመጨረሻዎቹ የምድብ እና የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች 1፡00 ሰዓት እና 4፡00 ሰዓት እንደሚከናወኑ ታውቋል።
ጨዋታዎቹ የትኛዎቹ ሜዳዎች ላይ ይከናወናሉ?
ሞሮኮ ዋፍኮንን ከሦስት ዓመታት በፊት አስተናግዳለች። ባለፈው ውድድር ጨዋታዎችን ያስተናገዱት ሜዳዎች ዘንድሮውን ውድድር እንደማያስተናግዱ ታውቋል።
አገሪቱ የ2025 የወንዶች አፍሪካ ዋንጫን እና የ2030 የዓለም ዋንጫን በጋራ ለማስተናገድ በርካታ ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ነው።
የዋፍኮንን ጨዋታዎች በአምስት ከተሞች የሚገኙ ስድስት ስታዲየሞች ያስተናግዳሉ። ሁለቱ በካዛብላንካ የሚገኙ ናቸው።
ኦሊምፒክ ስታዲየም፣ ራባት (የተመልካች የመያዝ አቅም 21 ሺህ)
ኤልባችር ስታዲየም፣ ሞሐመዲያ (የተመልካች የመያዝ አቅም 15 ሺህ)
ላርቢ ዘውሊ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (የተመልካች የመያዝ አቅም 30 ሺህ)
ፔሬ ጄጎ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (የተመልካች የመያዝ አቅም 10 ሺህ)
ሆነር ስታዲየም፣ ኦጁዳ (የተመልካች የመያዝ አቅም 19 ሺህ 800)
በርካኔ ስታዲየም፣ በርካኔ (የተመልካች የመያዝ አቅም 15 ሺህ)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ለዋንጫው የምትጠበቀው ቡድን የትኛዋ ናት?
በሞሮኮው ውድድር ከሚሳተፉት አገራት ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ብቻ ናቸው ከዚህ ቀደም ዋንጫው የማንሳት ታሪክ ያላቸው።
በአሠልጣኝ ጀስቲን ማዱጉዉ የሚሠለጥኑት ናይጄሪያዎች በርካታ ኮከቦችን ይዘው ወደ ስፍራው አቅንተዋል።
ቺያማካ ንናዶዚ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ በረኛ ተብላ ተሰይማለች። አጥቂዋ አሲሳት ኦሾአላ ደግሞ ጥራት እና የማሸነፍ ወኔን ለቡድኑ እንደምታላብስ ይጠበቃል።
የደቡብ አፍሪካ አሠልጣኝ የሆኑት ዲዛየር ኤሊስ ያለፈውን ዓመት ክብራቸውን ለማስጠበቅ ወደ ሞሮኮ አቅንተዋል።
አጥቂዋ ቴምቢ ክጋትላና በግል ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።
ዠርሜይን ሴኦፖሴንዌ ድንቅ ውድድር ዓመት ያሳለፈች ሲሆን፣ ያለፈውን የዋፍኮን የወርቅ ጫማ የተጋራችው ሂልዳ ማጋይያ የፊት መስመሩን በብቃት ትመራለች ተብሎ ይጠበቃል።
ሞሮኮ በቅርብ ዓመታት እግር ኳስ ላይ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ አፍሳለች። የሴቶቹ ቡድን ግን እንደወንዶቹ በአፍሪካ ደረጃ ገና ውጤታማ መሆን አልቻለም።
የአትላስ አናብስቱ ስፔንን ለ2023 የዓለም ዋንጫ ያበቋትን አሠልጣኝ ዮርጌ ቪልዳን ቀጥራለች።
ዛምቢያ ባለፈው ውድድር ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች። ከ2022ቱ ውድድር ውጪ ነበረችው እና ያለፈው ዓመት የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች የነበረችው ባርባራ ባንዳ የቡድኑ አባል ናት።
አጥቂዋ ከራቼል ኩንዳናንጂ ጋር ከፈጠረችው ድንቅ ጥምረት ፈጥረዋል።
ቡድኗን ኖራ ሃፕትል በአሠልጣኝነት ይመራሉ።
ቀሪዎቹ ስምንት ቡድኖች ዋንጫዋን ለማንሳት ከፍተኛ ፉክክር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ከቀሪዎቹ ቡድኖች ጋና (በ1998፣ 2002 እና 2006) ለፍጻሜ ለመብቃት ችላ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Backpage Pix
የምድብ ጨዋታዎች መርሃ ግብር
ቅዳሜ ሰኔ 28
ምድብ 1፡ ሞሮኮ ከዛምቢያ፣ ኦሊምፒክ ስታዲየም፣ ራባት (4፡00 ሰዓት)
እሑድ ሰኔ 29
ምድብ 1፡ ሴኔጋል ከ ኮንጎ፣ ኤል ባቺር ስታዲየም፣ ሞሐመዲያ (10፡00 ሰዓት)
ምድብ 2፡ ናይጄሪያ ከ ቱኒዝያ፣ ላርቢ ዛዉሊ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (1፡00 ሰዓት)
ምድብ 2፡ አልጄሪያ ከ ቦትስዋና፣ ፔሬ ጄጎ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (4፡00 ሰዓት)
ሰኞ ሰኔ 30
ምድብ 3፡ ደቡብ አፍሪካ ከ ጋና፣ ሆነር ስታዲየም፣ ኡጅዳ (1፡00 ሰዓት)
ምድብ 3፡ ማሊ ከ ታንዛንያ፣ በርካኔ ስታዲያም፣ በርካኔ (4፡00 ሰዓት)
ረቡዕ ሐምሌ 2
ምድብ 1፡ ዛምቢያ ከ ሴኔጋል፣ ሞሐመዲያ (10፡00 ሰዓት)
ምድብ 1፡ ኮንጎ ከ ሞሮኮ፣ ኦሎምፒክ ስታዲየም፣ ራባት (4፡00 ሰዓት)
ሐሙስ ሐምሌ 3
ምድብ 2፡ ቦትስዋና ከ ናይጄሪያ፣ ላርቢ ዛዉሊ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (1፡00 ሰዓት)
ምድብ 2፡ ቱኒዝያ ከ አልጄሪያ፣ ፔሬ ጄጎ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (4፡00 ሰዓት)
አርብ ሐምሌ 4
ምድብ 3፡ ጋና ከ ማሊ በርካኔ፣ ስታዲያም፣ በርካኔ (1፡00 ሰዓት)
ምድብ 3፡ ታንዛንያ ከ ደቡብ አፍሪካ፣ ሆነር ስታዲየም፣ ኡጅዳ (4፡00 ሰዓት)
ቅዳሜ ሐምሌ 5
ምድብ 1፡ ሞሮኮ ከ ሴኔጋል፣ ኦሎምፒክ ስታዲየም፣ ራባት (4፡00 ሰዓት)
ምድብ 1፡ ዛምቢያ ከ ኮንጎ፣ ኤል ባቺር ስታዲየም፣ ሞሐመዲያ (4፡00 ሰዓት)
እሑድ ሐምሌ 6
ምድብ 2፡ ናይጄሪያ ከ አልጄሪያ፣ ላርቢ ዛዉሊ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (4፡00 ሰዓት)
ምድብ 2: ቱኒዝያ ከ ቦትስዋና፣ ፔሬ ጄጎ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (4፡00 ሰዓት)
ሰኞ ሐምሌ 7
ምድብ 3፡ ደቡብ አፍሪካ ከ ማሊ፣ ሆነር ስታዲየም፣ ኡጅዳ (4፡00 ሰዓት)
ምድብ 3፡ ጋና ከ ታንዛንያ፣ በርካኔ ስታዲያም፣ በርካኔ (4፡00 ሰዓት)
የዋፍኮን የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መርሃ ግብር
አርብ ሐምሌ 11
ሩብ ፍጻሜ 1፡ የምድብ 1 አሸናፊ ከምድብ ሦስት ወይም ከምድብ ሁለት ሦስተኛ ደረጃን ከያዘ ቡድን፣ ኦሎምፒክ ስታዲየም፣ ራባት (4፡00 ሰዓት)
ሩብ ፍጻሜ 2፡ የምድብ 2 አሸናፊ ከምድብ አንድ ሁለተኛ ደረጃን ከያዘ ቡድን፣ ላርቢ ዛዉሊ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (1፡00 ሰዓት)
ቅዳሜ ሐምሌ 12
ሩብ ፍጻሜ 3፡ የምድብ 3 አሸናፊ ከምድብ አንድ ወይም ከምድብ ሁለት ሦስተኛ ደረጃን ከያዘ ቡድን፣ሆነር ስታዲየም፣ ኡጅዳ (4፡00 ሰዓት)
ሩብ ፍጻሜ 4፡ የምድብ 2 ሁለተኛ ከምድብ ሦስት ሁለተኛ ደረጃን ከያዘ ቡድን፣ በርካኔ ስታዲያም፣ በርካኔ (1፡00 ሰዓት)

የፎቶው ባለመብት, Backpage Pix
ግማሽ ፍጻሜ
ማክሰኞ ሐምሌ 15
ግማሽ ፍጻሜ 1፡ የሩብ ፍጻሜ 1 አሸናፊ ከ ሩብ ፍጻሜ 4 አሸናፊ፣ ኦሎምፒክ ስታዲየም፣ ራባት (1፡00 ሰዓት)
ግማሽ ፍጻሜ 2፡ የሩብ ፍጻሜ 2 አሸናፊ ከ ሩብ ፍጻሜ 3 አሸናፊ፣ ላርቢ ዛዉሊ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (4፡00 ሰዓት)
ለ3ኛ ደረጃ ጨዋታ
አርብ ሐምሌ 18
የግማሽ ፍጻሜ 1 ተሸናፊ ከ ግማሽ ፍጻሜ 2 ተሸናፊ፣ ላርቢ ዛዉሊ ስታዲየም፣ ካዛብላንካ (4፡00 ሰዓት)
የፍጻሜ ጨዋታ
ቅዳሜ ሐምሌ 19
የግማሽ ፍጻሜ 1 አሸናፊ ከ ግማሽ ፍጻሜ 2 አሸናፊ፣ ኦሎምፒክ ስታዲየም፣ ራባት (5፡00 ሰዓት)















