
የፎቶው ባለመብት, UGC
እሁድ ዕለት የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኝ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በፈጸሙት
ሁለተኛ ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል 11 መቁሰላቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ።
የሳዑዲ ጦር ቃል አቀባይ፣ ምንነቱ ያልታወቀ ተተኳሽ ንጉሥ ኻሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን እሁድ ዕለት መመታቱን ገልጸው በመንገደኞች ማረፊያ ውስጥ እሳት መቀስቀሱን ተናግረዋል።
የሳዑዱ አረቢያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን በኤክስ ገጹ ላይ በጥቃቱ አንድ ፓኪስታናዊ መገደሉን አስታውቋል።
በአውሮፕላን ማረፊያው ላይ ተወንጫፊ የተተኮሰው 13 ሰዎችን ገድሎ 308 ሰዎችን ያቆሰለው ጥቃት ከተፈጸመ ከአንድ ቀን በኋላ
ነው።
በየመን የሚገኙት ሁቲዎች ጥቃቶቹ መፈጸማቸውን
ገልጸው፣ አየር መንገዶች እና መንገደኞች የሳዑዲ አረቢያ
አውሮፕላን ማረፊያዎችን እና የአየር ክልልን እንዳይጠቀሙ
አስጠንቅቀዋል።
ቡድኑ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያውን በባለስቲክ እና በክሩዝ ሚሳኤሎች እንዲሁም ድሮኖች ዒላማ እንዳደረገ ተናግሯል።
በተጨማሪም በምሥራቅ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኝን የነዳጅ ተቋማት እና
የዳማም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጥቃት ፈጽመናል ሲሉ የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሪ ተናግረዋል።
"በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እየተባባሰ የመጣውን ዘመቻ ለመቀጠል” የዛቱት ቃል አቀባዩ፣ ሁሉም የሳዑዲ አውሮፕላን ማረፊያዎች
በቅዱስ ከተሞች መካ እና መዲና ውስጥ ካሉት በስተቀር ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
የሁቲ አማፂያን ሳዑዲ አረቢያ በየመን የእርስ
በርስ ጦርነት ውስጥ ለመንግሥት ኃይሎች ድጋፍ መስጠቷን
እና በሰነዓ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የአየር ጥቃት በመሰንዘሯ የተነሳ የአጸፋ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል።
እሁድ ዕለት በሳዑዲ የሚመራው
ወታደራዊ ጥምረት ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ቱርኪ አል-ማሊኪ የእሳት አደጋ ሠራተኞች በመንገደኞች አዳራሽ
ውስጥ
"ምንነቱ ባልታወቀ ተወንጫፊ" ምክንያት የተከሰተውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ
ባለበት ወቅት የአየር መቃወሚያዎቹ በሪያድ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ
አንድ ሚሳኤልን ማክሸፋቸውን ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሁቲ
አማፂያን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወይም ላለመሰንዘር
አሜሪካ "ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ" እና "በፍጥነት እርምጃ እንደምትወስድ" ተናግረዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከያ ሚኒስትር ዌስ ስትሪንግ ደግሞ ዩኬ ለሳውዲ አረቢያ የበለጠ ድጋፍ ልትሰጥ እንደምትችል ጠቁመዋል።
ቅዳሜ የተፈፀመው ጥቃት ባለፈው ዓመት የካቲት ወር በእስራኤል፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በአንድ
የባሕረ ሰላጤ አረብ አገር ላይ የደረሰው እጅግ
ከባድ
ጥቃት ነው። በሳዑዲ የሚመራው ጥምረት ድርጊቱን "የጦር ወንጀል" በማለት ጠርቶታል።
ከሟቾቹ መካከል አራት የሳዑዲ ዜጎች፣ ሁለት የባንግላዲሽ እና አንድ አንድ የአሜሪካ፣ የዮርዳኖስ፣ የፍልስጤም፣ የሶሪያ፣ የሱዳን እና የግብፅ ዜጎች እንደሚገኙበት
የሳዑዲ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ እሁድ ዕለት አንድ ሕንዳዊ በጥቃቱ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን
አስታውቋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ
ጥቃቶቹን አውግዘው አንድ የአሜሪካ ዜጋ መገደሉን አረጋግጠዋል። የዩኬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤድ ሚሊባንድ "በጣም አስደንጋጭ" ብለውታል።
የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከየመን ድንበር በ10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኙ የሳዑዲ አረቢያ ክፍሎች ዜጎቹ እንዳይጓዙ ያስጠነቀቀ ሲሆን ሌሎች የምዕራባውያን ኤምባሲዎች ደግሞ ዜጎቻቸውን ወደ አገሪቱ ስለሚያደርጉት ጉዞ አስጠንቅቀዋል።
በሁቲዎች ቁጥጥር ስር ያለው አል ማሲራህ ቲቪ
"ጠላት የሆነችው ሳዑዲ" በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ
ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን ዘግቧል። በከተማው ውስጥ ያለ መኖሪያ ቤትም ተመትቶ አንድ ሕፃን ሲገደል ስድስት ሰዎችን መቁሰላቸውን በዘገባው
ላይ ጠቅሷል።
ሳዑዲ አረቢያ ጥቃቶቹን ስለመፈጸሟ ምንም ያላለች ሲሆን ቢቢሲም ይህንን ዘገባ ማረጋገጥ አልቻለም።